Get Mystery Box with random crypto!

የእናቴ ልጅ ክፍል ሃያ ስምንት አባታችን አቤል ላይ መንገድ ዘግቶ ሲቆም ምን ሊ | አትሮኖስ

የእናቴ ልጅ
ክፍል ሃያ ስምንት

አባታችን አቤል ላይ መንገድ ዘግቶ ሲቆም ምን ሊፈጠር ነው በሚል ሁላችንም ማፍጠጣችን አልቀረም ። አቤል ፍርሐቱ እንዳለ ሆኖ የአባታችንን ሁኔታ ለመጋፈጥ አይል ለማሰባሰብ ሲሞክር አየውት እጆቹን እንደማወራጨት ብሎ  ወደክፍሉ ለመግባት አባታችንን ዘወርበልልኝ በሚል አስተያየት አየው ።
"እስካሁን ምንም አይነት የጥፋተኝነት ስሜት አላየውብህም ።ከዛ ይልቅ ስላወቅንብህ የቆጨኽ ነው የምትመስለው ፡እንዴት በአንድ ወንድምህ ላይ የዚህን ያክል በደል አድርሰህበት ምንም አይመስልህም ፡እውነት አንተ የኔ ልጅ ነህ ምን አይነት ጉድ ነህ ፡ አንተ ዛሬ አንድኛውን ልጄን አሳጥተኽኝ ነበር  አዎ እዛቦታላይ ደርሼ ነገሩን ባላስቆመው ኖሮ በጭካኔ አስገድለኽው ነበር እና ስለዚ አንተ የሚገባህ በሰላም ወደ ክፍልህ ገብተኽ መተኛት ሳይሆን መቀጣት ነው ያለብህ ፡እና የትም እንዳትሄድ እዚሁ ቁም የወንድምህን ውሳኔ እስክትሰማ "አሉት ።እናቴ በድጋሚ አለቀሰች ።እናቴ ምናልባት ዛሬ ባለቤቷን በዛ መልኩ በማግኘቷም ጭምር ግራ መጋባት ውስጥ ሳቶን አትቀርም ፡ብዙ አዘኖች ተደራርበው እየሰባበሯት ነው ምን እንደምትወስን ገና አላወቀችም ፡አቤልን ምን ማድረግ እንዳለባት ግራ ገብቷታል ። እኔ ደሞ አሳቤ ሁሉ ተምታቶብኛል ፡ የአባታችን በዚመጠን እራሱን ዝቅ አድርጎ ከኛ መደበቁንና ፡አኗኗራችንን ሲከታተል መቆየቱ በጣም ነው ያሳዘነኝ ።ጠጋብሎ ያለበትን ሁኔታ ቢነግረን ምን አለ ፡ ይሁሉ ላይፈጠር ይችል ነበር ፡እናታችን ያለአጋዥ ያሳለፈችውን ሕይወት በግልፅ ቢመጣ ያቀልላት ነበር  ።መቼም እናቴ በግልፅ ነገሮችን ስትረዳ ለይቅርታ አትሰስትም ።  ግን ያሳዝናል። እንግዲ አባታችን በራሱመንገድ እራሱን እየቀጣ ነበረ ። አቤል በአባታችን ቆፍጠን ያለ ንግግር የተደናገጠ መሰለ እናም እየተርበተበተ "እኔ ስለምትሉት ነገር አአላውቅም ሆነ ብለው እኔንና ወንድሜን ለማለያየት ያደረጉት ነው ፡ "አለ ።እኔ በጣም ተናደድኩ መናገር ግን አቃተኝ ።
"ተው ተው ቢያንስ እንኳ ከዚ በዋላ እንኳ ለመፀፀት ልብ ይኑርህ"አለው አባታችን ተቆጥቶ
"ለምን ባላረኩት ነገር እፀፀታለው ፡"አለ አቤል በድርቅና
"አንተ የማትረባ ልጅ እናትህ እንዴት አድርጋ እንዳሳደገችህ አላውቅም ፡ በጣም አስመሳይ እና ከሃዲ ነህ አንተ ልጄ አይደለህም አፈር ብላ "አለው አባታችን በንዴት ጦፎ
"እኔም ድንገት አንድ የጎዳና ሰው መጥቶ አባትህ ነኝ ቢለኝ የምቀበል ሰው አይደለውም "ሲል ለመነሳት ሞከርኩ አቅም አጣው ።እናቴ ግን ከመቅስበት ተነስታ እኔ ያሰብኩትን ፈፀመች ።አቤልን ሄዳ በጥፊ ስታጮለው ቤቱውስጥ ፍንዳታ የተከሰተ መሰለ ።ደስ ነው ያለኝ ።እራሴን ግን አልቻልኩም ፡ ህመሙ እየበረታብኝ ነው አይኖቼ ብዥዥ እያሉብኝ ነው ።የአባታችን ቁጣ ወደ አይል ተለወጠ እናቴ ከዚ በፊት የአባቱ ልጅ ብላ በስድብ መልክ የተናገረችኝ ትዝ አለኝ ፡ አባቴ የመጨረሻ ትህግስቱን ሲያጣ ማንም አይችለውም ፡ልክ እንደኔ ፡ አቤልን አንቆ ያዘው ።
"አንተ ደደብ እያናገርኩህ ያለውት ስለኔ አይደለም ስለ ምስኪኑ መልካሙ ወንድምህ ነው ፡እና እኔን ልትዋሸኝ ነው ና እንደውም ከአጋርህ ጋር ነው የምትቆየው ።እዚህማ በሰላም አታድርም እውነቱን ከሱጋር ታወራላቹ !!"ብሎ አባታችን አቤልን እየጎተተው ከትልቁቤት ይዞት ወጣ ። አቤል ለመከላከል ሲሞክር ደና ጥፊ አቀመሰው ። እናቴ ወደ እኔ አየች
"እናቴ በአቤል ተቀጥሮ ሊገለኝ የነበረው ልጅ እዚ ነው ያለው ይዘነው መጥተን ሰርፒስ ቤት ቆልፈንበታል እዛ ነው የሚወስዱት "አልኳት ።አፏን ያዘች ። ደግነሽ "ጉድ ነው ኧረዋ ጭካኔ ፡እኔ አፈር ይብላኝ ናቲዬ ወንድሜ ወንድሜ ስትል ለሱ ስትለፋ ፀባዩ ተስተካክሏል ስትል ድፍት አድርጎ ሊያስቀርህ ነበር ፡ናቲዬ መቼም አንተን ገሎ አያቆምም ነበር እናትህም አይቀርላት ፡መቼም ገንዘብ አይን ያሳውራል አብዝቶ መውደድ አያስፈልግም ኧረ ኧረ"አለች ።ባዩሽ አንገቷን ነቀነቀች ።
የጊቢያችን መጥሪያ ስታቃጭል ተሰማ  ደግነሽ "አሁን ደሞ ምንድነው "አለች
"ተረጋጊ ብሌን ትሆናለች "አልኳት
"እሺ እኔ ከፍታለው "ብላ ወጣች እናቴ ወደኔ ቀረብ ብላ"ደና ነህ ግን ልጄ አኪም ቢያይህ አይሻልም ፡ከሱጋር ስንጨቃጨቅ አንተን እረሳንህ ።"አለችኝ
"አይ ደና ነኝ እናቴ አታስቢ ትንሽ እራስምታት ነው "አልኳት እንደ እውነቱ ከሆነ ከባድ ነው  ።ብሌን ስትገባ ድንገት ተነስታ እንደመጣች ያስታውቅባታል ቢጃማዋ ላይ የሴት ካቦርት ነገር ጣል አድርጋ ነጠላ ጫማ ተጫምታ እረጅም ፀጉራ ላይ ሻሽ ሸብ አድርጋ ለች ።ሁኔታውን ወደድኩት ሁሉም ነገር የሚያምርባት ልጅ !!!!    ስታየኝ በድንጋጤ ወከክ አለች ስፍስፍ ብላ ስትነካካኝ "ደና ነኝ አትጨነቂ "አልኳት
"አይ አይ ደና አይደለህም ምንድነው እሱ በፈጣሪ "አለች አናቴላይ የተጠቀለለውን ጨርቅ በፍርሃት ነበር የምታየው
"ደና ነኝ ሳላስበውከዋላ አጠቁኝ  ሁኔታው ያስፈራ ነበር አሁን ግን ደና ነኝ "አልኳት
"ታውቆኝ ነበር እንዲ አይነት የተጨናነቀ እንቅልፍ ተኝቼ አላውቅም በጣም አስፈሪ የሚያስደነግጥ ስላንተ ብቻ ነበር የኔ ውድ በጣም ጎድተውሃል "አለችኝ ዕንባዋን እየታገለች
"እእ አዎ በእርግጥ ቅጥረኛ ነብሰ ገዳይ ነበር አመጣጡ ሊገለኝ ነበር "አልኳት ሳወራ እራሱ አቅም እያጣው ነበር
"በቃ በቃ ዝም በል ።ተነስ አሁኔ አኪም ሊያይህ ይገባል እንዳየሁት ከሆነ ደም ፈሶሃል ተነስ "አለቼ
"ብሌን የኔ ውድ አትጨነቂ ደና እሆናለው "አልኳት
"አይ እንደሱ አይደለም ስታድር ምን ሊፈጠር እንደሚችል አይታወቅም ግድ ነው ተነስ መሰፋት ያለበት ቦታ ሊኖር ይችላል "አለች ።እናቴ አሳቧን የሚጋራት በማግኘቷ ደስ ያላት ይመስላል ቀብሌን አሳብ ተስማማች እሷም ግፊት አድርጋ ።በመጨረሻ ተስማማው ።ስንወጣ አባታችን ከሰርፒስ ቤቱ ወጥተው ሲመጡ አይታ ብሌን በጥያቄ አስተዋለችኝ።
"እሳቸው ናቸው ያዳኑኝ ታሪኩን ሌላ ጊዜ እነግርሻለው "አልኳት
"እሺ "አለች ።አባታችን ወደ አኪም ቤት መሄዳችንን ስንነግረው ተስማማ ።እናቴ እና ብሌን ከኔጋር አብረን ውጪ የቆመችዋ የብሌን መኪና ውስጥ ገባን ። ቀስበቀስ አቅሜ እየተዳከመ መጣ ወደ እናቴ ዘንበል አልኩ እናቴ ሰውነቷ ይንቀጠቀጣል ።እጇን በትኩሳት ያበደ ጭንቅላቴ ላይ ጣል አድርጋ ታሻሸኝ ጀመር ....
ብሌን መኪናዋን በፍጥነት እየነዳች ስቅ የሚል ድምፅ ስታወጣ ይሰማኛል ፡የኔ ፍቅር የኔ እብድ ዛሬ በኔ እየተፈተነች ነው ምንም እንዳልሆንባት ነው የምትፈልገው ...........


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj