Get Mystery Box with random crypto!

የእናቴ ልጅ ክፍል ሠላሳ ሁለት የመጨረሻ ቀን ቀንን እየተካ በሄደ ቁጥር | አትሮኖስ

የእናቴ ልጅ
ክፍል ሠላሳ ሁለት
የመጨረሻ

ቀን ቀንን እየተካ በሄደ ቁጥር በወንድሜ ላይ የነበረኝ የመረረ ጥላቻ እና ቂም እየደበዘዘ ሲመጣ ይታወቀኛል  ይህን ስሜት ወደድኩት ምክንያቱም እኔ ቂመኝነት በውስጤ ሰርፆ ቤቱን እንዲሰራብኝ የምፈልግ ሰው አይደለውም ። መጥፎ እና ልክ ያልሆኑ ጉዳዮች ጭንቅላቴ ውስጥ ጊዜ ወስደው በቁዩ ቁጥር እታመማለው ፡መረጋጋት አልችልም ። ያንን ስሜት ለማስታገስ ስል ነውጠኛ ነው የምሆነው ፡ከዚበፊት የእናቴን ጥላቻ እና የሰፈሬን ሰው ግልምጫ ለመወጣት ስል ንዴቴን ካገኘውት ሰው ጋር ሁሉ ነገር ፈልጌ እጣላ ነበር ። አሁን ላይ ከጉርምስናውም እየወጣው ነው እና ያ ስሜት እንዲቆጣጠረኝ አልፈልግም ። ስለዚ በወንድሜላይ ያለኝ ብስጭት እየቀነሰልኝ ሲመጣ ተጠቃሚ ነኝና ደስታ እየተሰማኝ ነው ። እሱ በሰው አገር ላይ ምን እያሳለፈ እንዳለ የምናውቀው ነገር የለም ። ሲዊዲን መድረሱን ከተቀባዮቹ ጋር ሆኖ ለእናቴ ደውሎ ከነገራት በዋላ ።ድጋሚ ደውሎም አያውቅም ። እናቴም ብትሆን ጨከን ብላበታለች ። 'ከአሁን በዋላ ቤተሰብ አለኝ ብለህ ወደእኛ እንዳታስብ 'ብላ እንደተናገረቸው አባቴ ነግሮኛል ። በእርግጥ ምንእንደሚሰማት  እሷው ነው የምታውቀው ።የእናት አንጀት እንዲ በቀላሉ ይቆርጣል ማለት ዘበት ነው ። አባታችንም ቢሆን ስሙን ለማንሳት ድፍረቱ ባይኖረውም አንዳንዴ በጨዋታችን መሃል ተክዞ ተክዞ በረጅሙ ሲተነፍስ አጋጥሞኛል ።ምን አልባት ስለ አቤል እያሰበ ይሆናል ብዬ እጠረጥራለው  ።
እኔ እራሱ ሳስበው ለአቤል እንዲመሆን ጥፋተኛው ማነው ? ብዬ አስባለው ። ያለ አባት አድገናል ፣እናታችን የሌለ አቅርባው አቅብጣውም ነበር ። የራሱስ አስተዋፆ ? እኔስ ብሆን ጥፋቶቹን በኔ ሲያላክክ የረዘመ ዝምታ አሳይቼስ አልነበረ ? ብቻ አንዳንዴ ሳስበው አቤል እንዲ እንዲሆን ትንሽ አስተዋፅዖ ሳይኖረን አይቀርም እላለው !!!!
እሁድ ቀን  ተሰብስበን እንደተለመደው እየተጨዋወትን ፡ ቤቱን ሞቅ ደመቅ አድርገነዋል ፣ አባታችን እናቴን እየቀለደባት ያስቀናል ማማ በእናቴ ዙሪያ እየዞረች ባልገባት ነገር ትፈነድቃለች የኛ ሳቅ ሳይጋባባት አይቀርም ፣ እናቴ  ስለተሳቀባት አልከፋትም በጣም ደስተኛ ትመስላለች በባሏ ጎኗ መሆን ሙሉነት ሳይሰማት አይቀርም ልዩ ሆናለች ፡ በዛላይ ትላንትና የማማን እናት በማግኘቷ እፎይታ ተሰምቷታል ፡ የአቤልን ትልቅ ስህተት እንዳረመች ሳይሰማት አይቀርም ፡ የማማን እናት ይዛት መጥታ በማንኛውም ሰአት ልጇን የማየት መብት እንዳላት ነግራ ፡ ነገር ግን እፃኗ ከኛጋር መኖር እንዳለባት አስረግጣ አስረድታታለች እሷም ብትሆን ለልጇ ያን ያክል የምትጓጓ መስላ አልታየችም ።እንዲ መሆኑን የፈለገች ነው የምትመስለው ይሄ በራሱ ለኔም እንደ ግልግል ነው ።በአራስነቷ የተረከብኳትን ስንት ነገር ያየውባትን ልጅ ልውሰድ ብትል ምን እንደሚሰማኝ አላውቅም ።  ማማ ለኔ ትምህርት ቤቴ ናት በሷ የተነሳ እራሴን ገዝቻለው  ስለ ዓለም ክፋት ደግነት አይቻለው  ማጣት ምን ያክል እንደሚፈትን ገብቶኛል ። ብቻ ብዙ ብዙ ,,,,,
ዛሬ ላይ ግን በዛ ሂደት ውስጥ ስንት የምወዳቸውን ሰው አውቄ አለው ።ለየት ባለ መልኩ ባዩሽን የክፉ ቀኔ ። ብሌኔን ፍቅሬን የወደፊት ሚስቴ የአይኔን ማረፊያ ፡የልብ ምቴ የሕይወቴ ቅመም ማጣፈጫዬን ፡ ብሌኔ ውዴን ብሌኔ ብሌኔ ፡ስሟን እንኳ ስጠራው የሆነ መሃዛ ከአፌ ወጥቶ አብሮ ያውደኛል  ብሌኔ ብሌኔ ......
እረፋዱ ላይ አንዳችን በአንዳች እየሳቅን ጨወታችን ደርቶ ፡  ሳለ የእናቴ ስልክ ጮኽች ።እናቴ እንደሌላው ጊዜ አልፈጠነችም ታነሳዋለች ብለን ስንጠብቅ ፡ወደኛ ማየት ሆነ ። ስትዘገይብኝ ስልኳን አንስቼ ቁጥሩን አየውት የውጪ ለጠ ር ነው ደንገጥ አልኩ ። እናቴ በፍርሃት ስታየኝ
"የውጪ ስልክ ነው አንሺው አልኳት "
"አንተአንሳው "አለች እንደፈራች ስለገባኝ ፡ እኔው አነሳሁት
"ሄሎ "
"ሄሎ የወይዘሮ ዘውድነሽ ስልክ አይደለም "አለኝ የሴት ድምፅ ድንጋጤዬ ጨመረ አቤል ምን ሆኖ ነው
"ነው ማን ልበል አንቺን"አልኳት
"ዲና እባላለው እእ ከሲዊዲን ነው የምደውለው "አለች
"እሺ ምምን የየተፈጠረ ችግር አለ ወንድሜ ምን ሆኖ ነው "አልኳት እየተርበተበትኩ ።እናቴ ስታቃስት ሰማው ዞሬ ሳይ ዕንባዋ ቀድሟል ።
"ኧረ ተረጋጋ እሱ ምንም አልሆነም እኔ ፍቅረኛው ነኝ ያው ብቻ ስለ እናንተ ብዙጊዜ ያወራኛል እና ዛሬ አበረታትቼው አብረን እናወራቸዋለን ብዬ ነው በስንት መከራ የደወልኩት "አለች ፈጠን ፈጠን ብላ
"ድምፁን መስማት እንችላለን "አልኳት
"አዎ እባክህ አንተ ወንድሙ ከሆንክ በጣም ተፀፅቷል እና ይቅር በለው  "አለች
"ችግር የለም ይቅር ብዬዋለው አጠገብሽ ካለ ስልኩን ለሱ ስጪው እናቱን ያናግራት "አልኳት
"እሺ "ብላ ስታስተላልፍ እኔም ስልኩን ለእናቴ ሰጠዋት ።እናቴ ልትደብቀው የማትችለው የልጇ ፍቅር ገንፍሎ ወጣ ፡ በቃ ከአቤል ጋር በናፍቆት አወሩ በተደጋጋሚ ይቅር በይኝ ሲላት ይሰማል ልቡ የተሰበረ ይመስላል ፡ ከአባታችንም ጋር አወራ ፡አባታችንም አለቀሰ ፡ብዙ ነገር ተናገረው እንደዚ አይነት ክፋት ከገዛ ልጁ ስላልጠበቀ እስካሁንም ድረስ እየተሰቃየ እንደሆነ ነገረው አቤል ስቅስቅ ብሎ ሲያለቅስ ይሰማል ፡ጓደኛው ነኝ ያለችው ሴት ታባብለዋለች ፡ላውድ አድርገነው ስለሆነ የምናዳምጠው ፡አክስቴ ደግነሽም ባዩሽም ማልቀሳቸው አልቀረም ፡ አክስቴ ደግነሽ ወደኔ እያየች "ይቅር በለው ልጅነት ነው አውሬ ያደረገው "አለችኝ ሆደባሻነቷ አይሎ ፡  እኔ ውስጤ ተረጋግቷል ሞተ የምባል መስሎኝ ስለነበር ክፉ ነገር ስላልሰማው ሰላም ሰፍኖብኛል ። ዓለም እንግዴ እንደዚ ናት እንደ ዥዋዥዌ ነው ነገሯ ወደዚ ወደዚያ ፣ እንደ ፈለገች አንተ ጠንክረ ገመዷን ይዘህ እየተቆጣጠርክ ካልተጫወጥክ ፈንግላ ልትጥልህ ትችላለች ፡ እራስህን ከማንም ጋር ሳታወዳድር የማንንም ንዋይ ሳትመኝ የሕይወት መንገድህን በራስህ በንፁ ሕሊናህ ታግዘህ አስምር መስመሩ ሲበላሽ በትህግስት እያስተካከልክ  ወደፊት ቀጥል ። ለሌሎች የደስታ የሰላም ምንጭ እንጂ ፣የስቃይ የመከራ ምንጭ አትሁን ፣ አንተ ደስተኛ የምትሆነው በዙሪያህ ደስተኞች ሲኖሩነው ፡ 'ብቻህን በሚያለቅሱ ሰዎች መሃል ብትስቅ እብድ ነው የምትባለው'
             ,
                  ተፈፀመ
ደራሲ Unknown

    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj