Get Mystery Box with random crypto!

የእናቴ ልጅ   ክፍል ሃያ ሰባት ያልጠበኩት ነገር ነበር የተፈጠረው ነገሩሁሉ ተ | አትሮኖስ

የእናቴ ልጅ
  ክፍል ሃያ ሰባት

ያልጠበኩት ነገር ነበር የተፈጠረው ነገሩሁሉ ተምታታብኝ እናቴ የነገረችኝ የአባቴ ሁነታ እና እያየው ያለውት የተለየ ነው ።ሽማግሌው የኔ አባት ?ለማመን ተቸገርኩ ፡ እኛን ለማግኘት ያን ያክል ከባድ አልነበረም እንዴት ለሃያ ሦስት አመት ሳያየን ቆየ?
የት ነበር እስከዛሬ ለምን ሕይወቱን በዚ መልኩ ለመኖር ወሰነ የተሻለ ነገር ለማሰብ ለምን አልሞከረም ? አብታምና ምንም ነገር እንደማይሳነው አድርጋ ነበር እናቴ ስለ አባቴ የነገረችኝ ።አሁን የማየው ሰው ግን የተጎሳቆለ እና መንገድ ላይ ላስቲክ ወጥሮ የሚኖር የዋህ ሽማግሌ ነው ። ለምን አይምታታብኝ !
እናቴ በስንት ማባበል ጩኽቷንና ለቅሶዋን አቆመች እነባዩሽ አብረዋት አንብተው ዝም ስትል አብረው ዝም አሉ እኔግን ብዙ ጥያቄዎች ነበሩኝ ለዛውም ቁጣን ያዘሉ ጥያቄዎች ። አቤል የሚገባበት ቀዳዳ የሚፈልግ ነው የሚመስለው ፡ሽማግሌው አባታችን መሆኑን ካወቀ ሰአት አንስቶ ምንም አይነት ነገር አልተናገረም ነገርግን ለአንዴ እንኳ ቀና አላለም አንገቱን እንደደፋ ነው ፊቱላይ ያለውን ለውጥ ለማየት እንኳ አልቻልኩም ።  እናቴ በቀስታ "ለምን?"ስትል ሰማዋት ።የኔም ጥያቄ ስለነበር ወደ ሽማግሌው አባቴ ዞርኩ
"ለምን ?ለምንድነው እስከዛሬ ድረስ በሕይወት እያለህ አንዴ እንኳን ተሳስተህ መጥተህ ያላየኽን ? እኛ ለማግኘት እንደማይከብድህ እርግጠኛ ነኝ !እንኳን አንተ ቀርቶ አክስቴ ደግነሽ እንኳ የቀድሞ ሰራተኛህን አግኝታ ያለንበትን አውቃ መጥታለች ። እና አንተስ ? "ብዬ ዝም አልኩ ።እናቴም ቀና ብላ መልሱን ጠበቀች ።
"ይቅርታ አድርጉልኝ እኔ ለእናንተ የምገባ ሰው አይደለውም ጥሩ ሰው አልነበርኩም ።በተለይ ለባለቤቴ ዘውድነሽ አልገባትም ነበር እሷ የዋሕና ገና ታዳጊ ልጅ ነበረች በዛች ትንሽዬ ልጅ ላይ የሕይወትን ሸክም አሸክሜያታለው።  ግን እንደዛ መሆን ነበረበት እንደሱ ባላደርግ ኖሮ ሁላችሁንም በኔ የተነሳ ያጠፏቹ ነበር ። ጓደኞቼ ካልኳቸው ሰዎች ጋር በድንገት በተፈጠረ አለመግባባት ተቃቅረን ነበር ሲያጣላን የነበረው ደሞ በጋራ የሰራነው ስራ ነበር ስራው እገወጥ ነው  ስራውን ሰርተን ስንጨርስ በምንከፋፈለው ድርሻ ምክንያት አለመስማማት ተፈጠረ  እቃውን ያስገባውት እኔነኝ  ነገርግን በስራው ላይ አነስተኛ ድርሻ የነበራቸው ሰዎች እኩል ክፍፍል ሲፈልጉ አይገባችሁም አልኳቸው ፡በወቅቱ የኔን አቅም ስለሚያውቁ የተስማሙ መሰሉ ።በዋላ ላይ ግን በሴራ ጠልፈው ሊጥሉኝ ተስማሙ ፡ከዛ ባላደረኩት ነገር እንድከሰስ አደረጉኝ ፡  ከዛ ምንም አይነት መፈናፈኛ እንዳላገኝ አዋከቡኝ ይህን ልቋቋም አልቻልኩም ክሴን እየተከታተልኩ ። እነሱን ደሞ በሌላ መልኩ ልበቀላቸው ወጥመድ መዘርጋት ጀመርኩ ፡ እና ይህን ፍላጎቴን ለማሳካት ደሞ እናታችሁን እና እናንተን እንዳይነኩብኝ ማራቅ ነበረብኝ ።እናንተ እንዳትቸገሩ ያለኝን በሙሉ ለዘውድነሽ አስተላለፍኩ ቤት ገዛው  ።ምክንያቱም እናንተ ለኔ አይኖቼ ነበራቹ ስጦታዎቼ ....."ብለው ዝም አሉ እኔ ደሞ እገወጥ ስራ ስላሉ ደስ የሚል ስሜት አልተሰማኝም ፡በዛላይ እነዛን ጓደኞቻቸውን ምን አድርገዋቸው ነው ብዬ ተሰቀቅኩ ።የወንጀለኛ ልጅ መሆን ይከብዳል
"እሺ አሳጥረው የት እንደነበሩ ይንገሩን "አልኩ
"ከዛማ እነሱን ለመበቀል የኔን ሰዎች አሰማራው ነገር ግን ሳይሆን ቀረ እኔ አንድ ጉዳት ከማድረሴ በፊት ከኔ የሆነሰው ለነሱ የሚወግን ሆኖ ተገኝቶ እኔን ከዳኝ እናም  ። በላሰብኩት ሁኔታ አሳልፎ ሰጠኝ እነሱም ያልሰራውትን ሁሉ እንደሰራው አድርገው ከሰሱኝ በወቅቱ የነበሩት ከፍተኛ ቦታላይ ያሉትን ሰዎች ሁሉ በገንዘብ ገዝተው ኖሮ ።በጮህ ብለፈልፍ ሰሚ አጣው እና በቁጥጥር ስር አዋሉኝ ። ከዛ በዋላ እስርቤት ወረወሩኝ ያለምንም ፍርድ ለሃያ አመት እዛው ነበርኩ ፡ልጄ ቅስሜ ሁሉ ተሰባብሮ ።ሰው መሆኔን እስክጠላ ነበር ጉዳዩ  ።ብቻ እንደው ስለጠየከኝ እንጂ ማውራትም አልፈልግም ነበር ባጭሩ ግን ለሃያ አመት ያለፍርድ ታስሬ አለው ስፈታ ወደ እናንተ ነበር የመጣውት ግን ከፍለጋ በዋላ የዘውድነሽን አድራሻ ባውቅም ግን ወደእናንተ መቅረብ አቃተኝ ለምን እንደው ፈራው  "አሉ አይናቸውን ሰበር አድርገው ። ድጋሚ ሌላ ጥያቄ ልጠይቃቸው ልናገርስል ስልኬ ጮኽ ብሌን ነበረች
"ሃሉ "አልኩኝ ለምን በፍጥነትእንዳነሳውት ለራሴም ገረመኝ ምን አልባት ዛሬ የሕይወቴ ፍፃሜ ሊሆን ስለነበር ከሷ መለየቴን ፈርቼው ነበር
"ናቲ የኔውድ ሰላም ነህ በጣም ፈርቻለው"አለች
"ምነው ብሌኔ ደና ነኝ ለምንፈራሽ "አልኳት
"እኔ እንጃ ብቻ በጊዜ ነበር የተኛውት እና ደስ የማይል ህልም አየው ስለ አንተ ደና ነህ አይደል እኔ በህልም ምናምን አላምንም ግን ይሄ ያስፈራል "አለች
"ደና ነኝ ብሌኔ ህልም ህልም በይ በቃ "አልኳት ሳላስበው አቃሰትኩ ። ጭንቅላቴን አመም አደረገኝ
"ምንድነው እየዋሸህ ነው አይደል አንድ ነገር ሆነሃል ?መጣው በቃ "አለች ።
"አይ አይ እኔ ....."ስል ስልኩን ዘጋችብኝ ደግሜ ስደውል ይዘጋል ስልኩ ።ተናደድኩ እንዲ ሆኜ እንድታየኝ አልፈለኩም ።በዛ ላይ የአባቴን ታሪክ እውነተኛውን በትክክል ለመስማት ፈልጌያለው ገና የአቤልም ጉዳይ አልተቋጨም ።ብሌን ተጨማሪ ጭንቀት እንድትሆንብኝ አልፈለኩም ።እሷን ደሞ ንነዲነው እንዲያነው እያሉ ለማስረዳት ተጨማሪ አቅም ከየት ላምጣ ።ጭንቅንቅ ስል እናቴ አይታ ።ወደአቤል በመዞር ወደመኝታ ክፍል እንዲገባ ጠቆመችው ፍፁም ተኮሳትራ ነበር ።አባታችን ግን የትም አይሄድም ብሎ ያዘው .......
የአቤል አይን ተቁለጨለጨ ወደሄትም ማምለጥ እንደማይችል ገባው ከአባታችን ጋር ተፋጠጠ.......


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj