Get Mystery Box with random crypto!

'ህያብ ፊቴን አንብበሽ መረዳት ከቻልሽ እባክሽ አሁን ምንም ማውራት አልፈልግም.... እና ካወራሁም | አትሮኖስ

"ህያብ ፊቴን አንብበሽ መረዳት ከቻልሽ እባክሽ አሁን ምንም ማውራት አልፈልግም.... እና ካወራሁም በጣም አስከፋሻለሁ ስለዚህ እኔም ተረጋግቼ አንቺም እረፍት አድርገሽ የተለመደው ቦታ ዘጠኝ ሰዓት እንገናኝ... ቻው" መልሴን ሳይጠብቅ ትቶኝ ሄደ። ግራ እንደተጋባሁ ዶርም ገብቼ ጥቅልል ብዬ ተኛሁ ግን እንቅልፍ ከየት አባቱ ወደ ግራ ወደቀኝ እየተገላበጥኩ አሰብኩ.... አሰብኩ.... አሰብኩ... ግን ትላንትና ማታ ምን እንደተፈጠረ ማስታወስ አቃተኝ

ከቀጠሯችን አስር ደቂቃ ቀድሜ ተገኘሁ... ብዙም አላስጠበቀኝም። እንደመጣ

"በናትህ ቢኒ እኔ ምንም ማስታወስ አልቻልኩም የቀጠሯችን ሰዓት እስከሚደርስ ድረስ ሳልተኛ ብዙ አሰብኩ ግን ምንም ትዝ አይለኝም"

"የእውነት ምንም አታስታውሺም"

" እነሱን አይቼ ተናድጄ ካንተ ጋር እየጠጣሁ ነበር ከዛ እነሱ ወደተቀመጡበት እንደሄድኩ ትዝ ይለኛል ከዛ ውጪ አዎ ምንም አላስታውስም"

"እሺ ጥሩ እንደዛ ከሆነ እኔ ላስታውስሻ....
በጣም ሰክረሽ ነበር ጠርሙሱን ቀምቼሽ ወደ ዶርም እንሂድ ስልሽ  አልሰማሺኝም ተቀብለሽኝ እየተንገዳገድሽ ዮናታንና የትናዬት ወደተቀመጡበት ቦታ ሄድሽ። ሁኔታሽ ስላላማረኝ ተከተልኩሽ... ከዮናታን ውጪ ማንም አልነበረም እናም አንዴ እየሳቅሽ ሲልሽ እያለቀሽ እንዴት እንደምትወጂው ለእናትሽና ለአላማሽ ብለሽ ከሱ እንደራቅሽ ነግረሽው የየትናዬትን ተንኮል እየነገርሺው እያለ ከየት መጣች ሳትባል ፀጉርሺን ጨምድዳ ይዛ በጥፊ መሬት አነጠፈችሽ..."

"ምን ጭራሽ ተደባድቤም ነበር" አሁን የተመታሁ ይመስል ጉንጬን በእጄ ዳበስኩት

"አዎ.... ያም ብቻ ሳይሆን በወደቅሽበት ትንሽ መታሻለች... ብዙም ሳይቆይ ሰዎች አገላገሏችሁ እና እኔ አንቺን ይዤሽ ከዛ ወጣን እና አልጋ ፈልጌ ያዝኩ አንቺን አስተኝቼሽ ትንሽ ቆዬት እንዳልኩ የክፍሉ በር ተንኳኳ ሄጄ ስከፍት ዮናታን በር ላይ ቆሟል..."

"ምን...... ማለት ለምን ነበር የመጣው" ወይኔ ነገሩን ሀሉ በአንድ ቀን ስካር አበላሸሁት ማለት ነው። ቢኒ ለመናገር ሲታሽ አየሁት

"ምንድነው እሱ ቢኒ ንገረኝ እንጂ..."

"ይሄ እኔን ይጎዳኝ ይሆናል አንቺን ስለሚጠቅምሽ ግን ልንገርሽ"ለአፍታ ዝምምም አለ

"ምን ቢኒ" ልቤ ስቅል አለ

"ዮናታን እንደምናስበው አይነት ሰው አይደለም"

"ማለት" አልኩት ግራ ተጋብቼ

"ማለትማ ከየትናዬት ጋር ያላቸው ግንኙነት እኛ እንደምናስበው አይደለም...."

ይቀጥላል