Get Mystery Box with random crypto!

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_media_center — አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center
የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_media_center — አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center
የሰርጥ አድራሻ: @amhara_media_center
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.55K

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-03 14:32:54
2.6K views11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 14:32:49 በደብረ ብርሃን ከተማ አለም ዓቀፍ ህግን በጣሰ መልኩ በመጠለያ ካሉ በሽህ የሚቆጠሩ ተፈናቃይ ወገኖች በ50 ሜትር ርቀት ላይ ሰፍሮ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ከአካባቢው እንዲነሳ ተጠየቀ፤ በመጠለያ ባሉ ሴቶች ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸሙ አባላት ስለመኖራቸውም የአማራ ማህበር በአሜሪካ አስታውቋል።

የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ሚያዚያ 25/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በደብረ ብርሃን ከተማ አለም ዓቀፍ ህግን በጣሰ መልኩ በመጠለያ ካሉ በሽህ የሚቆጠሩ ተፈናቃይ ወገኖች በ50 ሜትር ርቀት ላይ ሰፍሮ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ከአካባቢው እንዲነሳ ተጠይቋል።

በደብረ ብርሃን መጠለያ ባሉ ሴቶች ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸሙ እና ልጃገረዶችን ለወሲባዊ ጥቃት እያስገደዱ ያሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ስለመኖራቸው ማረጋገጡን የአማራ ማህበር በአሜሪካ አስታውቋል።

ከዚህም በተጨማሪ በለጋሽ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ስራ ጣልቃ በመግባትም እርዳታ የሚያገኙበትን ሂደት እያስተጓጎሉ መሆኑ ተገልጧል።

እንደአብነትም ኢንተርናሽናል ሜዲካል ኮርፖስ (IMC) እና
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶቤተ ክርስቲያን የልማት ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በተባሉ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች ላይ የዛቻ ድርጊት እየተፈጸመ ስለመሆኑ ማረጋገጡን ማህበሩ ገልጣል።

በተመሳሳይ በቆቦና አካባቢዋ የገባው አብይ አህመድ ያሰማራው ጦር ሚያዝያ 22/2015 ቤት ለቤት እየዞረ በፈተሸበት ወቅት ሴቶችን አስገድዶ የደፈረ ስለመኖሩ አማራ ሚዲያ ኔት ወርክ የተባለ የዩቱብ ሚዲያ ያጋራው መረጃ አመልክቷል።

ከሚያዚያ 19/ 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቆቦና አካባቢዋ የሚገኙ ዋና ዋና መንገዶችን በመዝጋት ቤት ለቤት በማሰስ ፋኖ ምሬ ወዳጆ ያለበትን ጠቁሙ እንዲሁም የደበቃችሁትን መሳሪያ አዉጡ በማለት ህዝቡን እያሸበሩት እንደሆነ ተገልጧል።

በእነዚህ የመንግስት ሀይሎች እድሜዋ በግምት ከ20 አስከ 25 የሚሆናት ከቆቦ ወጣ ብላ የምትገኝ የገጠር ቀበሌ ነዋሪ የሆነች ታዳጊ ወጣትን 3 አባላት የተደበቀ መሳሪያ አለ አዉጭ በማለት ቢጠይቋትም እሷም ምንም መሳሪያ እንደሌለ ከፈለጉ ገብተዉ እንዲፈትሹ በመፍቀዷ እኝህ ሀይሎች ቤቷን በመፈተሽ ምንም አይነት መሳሪያ ማግኜት አልቻሉም በመጨረሻም በሚያሳዝን ሁኔታ በንዴት በመሳሪያ አንገራግረዉ እንደደፈሯት እንዲሁም የደፈሯት 3ቱም ከአማረኛ ቋንቋ ዉጭ ሌላ የማታዉቀዉ ቋንቋ ጭምር ሲነጋገሩ እንደነበር መናገሯ ተገልጧል።

ተጎጅዋ ወጣት በዚህ ሰዓት በአስቸኳይ ህክምና ማግኜት እንዳለባት ነገር ግን በመንግስት ሀይሎች ምክንያት በአካባቢዉ ሙሉ ለሙሉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ስለቆመ ተጎጅዋ የህክምና እርዳታ ማግኜት እንዳልቻለች ተዘግቧል።
2.6K views11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 14:21:36
2.4K views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 14:21:32 ሰበር ዜና

#ሸዋሮቢት ነፃነቷን አወጀች

የአማራ ሚዲያ ማእከል
ሚያዚያ 25 2015 አ/ም
አዲስ አበባ

ሸዋ ሮቢት ከተማ ከትናንት ከሰዓት ጀምሮ በህዝባዊ ኃይሉ ቁጥጥር ሰር ገባች

ላለፉት ሶስት ቀናት ከኦህዴድ ሠራዊት ጋር ከፍተኛ ትንቅንቅ ሲያደርግ የነበረው የሸዋ ህዝብ እና ጀግናው የአማራ ፋኖ አንድነት በሸዋ አካባቢውን በመቆጣጠር ከትናንት ከሰዕት ጀምሮ ህዝቡ ራሱን ማስተዳደር ጀምሯል።

የከተማ አስተዳደሩ፣የብልፅግና ፅ/ቤት እና የፀጥታ ተቋማት በሙሉ በህዝብ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

የሸዋ ህዝብ ከተማዉ በህዝባዊ ሠራዊቱ ቁጥጥር ስር እንድትወድቅ ስንቅ በማቀበል፣መንገድ በመዝጋት፣ህዝቡን ሊጨፈጭፍ የገባውን ሠራዊት በመመከት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።

ህዝቡ ከጨፍጫፊው የብልፅግና አገዛዝ ወጥቶ እራሱን ማስተዳደር ለዓመታት ሲፈልገው እና ሲመኘው የነበረ መሆኑን በሀሴት ገልጿል።

የሸዋሮቢት ከተማ ህዝብ እና የአማራ ፋኖ አንድነት በሸዋ አካባቢውን ተቆጣጥሮ ማስተዳደሩን መጀመሩን ተከትሎ ብስጭት ውስጥ የወደቀው ኦህዴድ ብልፅግና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት ወደ ከተማዋ እንዲላክ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ከደብረብርሃን መስመር ተነስቶ "ቀይት፤ጉዶ በረት" የሚባሉ አካባቢዎች ለይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦህዴድ ሠራዊት ወደ ሽዋ ሮቢት ከተማ ለመግባት ሲርመሰመስ ተስተውሏል።

የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ጨምሮ ሁሉም የአገር ውስጥ እና የውጭ የሲቪክ ተቋማት እንዲሁም ሚዲያዎች የኦህዴድ ሠራዊት አካባቢውን ከቦ በሶስት ቀናት ውስጥ ካደረሰው የንፁሃን ጭፍጨፋ በባሰ መልኩ ሊፈፅም ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን እንድታውቁልን ጥሪ እናቀርባለን ሲል ህዝባዊ ኃይሉ አስተዋቋል።ድያስፖራው ማህበረሰብም በዲፖሎማሲ እና በፋይናንስ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

"ከዚህ በኋላ የሸዋን ህዝብ የኦህዴድ ሠራዊትም ይሁን የኦህዴድ ብልፅግና መዋቅር በጉልበት ሊገዛ አይችልም፤በቃን፤ነፃነታችንን በክንዳችን አስመልሰናል፤ በኦህዴድ ብልፅግና መዋቅር መገደል፣መፈናቀል፣መራብ እና መጨቆን በቅቶናል፤ሁሉም የአማራ ህዝብ የራሱን ህዝባዊ አስተዳደራዊ መዋቅር ልክ እንደ ሸዋ ህዝብ ይፈጠር"ሲሉ ለተቀረው የአማራ ክፍል አስቸኳይ ጥሪ አቅርበዋል።

በስተመጨረሻ ለኦህዴድ ሠራዊት አባላት የአማራ ፋኖ አንድነት በሸዋ እና የሸዋ ህዝብ እንዲህ ሲል ጥሪ አቅርቧል"...ለወንድም የአማራ እና የደቡብ ተወላጅ የሠራዊቱ አባላት እንዲሁም ለሚመለከተው የሠራዊቱ አባላት በሙሉ ትናንት በነበረ የዕርስ በርስ ጦርነት ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ረግፈዋል፤ከነዚህ መካከል በመቶሽዎች የሚቆጠረው ምስኪኑ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ነው።በየጥሻው ያለቀው ሠራዊት ደም እንኳን ሳይደርቅ፣ሲያጋድሉ የነበሩ አካላት ውስኪያቸውን መራጨት ጀምረዋል፤ዛሬም ምስኪኑ የሠራዊት አባላት ለዐብይ አህመድ ሥልጣን መቆየት ብቻ ሲባል ከተደገሰለት ዳግም ዕልቂት እራሱን ሊጠብቅ ይገባል።በህዝብ ላይ አልተኩስም በማለት ህዝባዊነቱን ሊያስመሰክር ይገባል።እየከዳ ቢወጣ ልንቀበለው ዝግጅት ጨርሰናል"ብሏል።
2.5K views11:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 18:45:51
3.6K views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 18:45:51 "የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመጥነውን የፖለቲካ መሪ በማጣቱ፣ አካታችና ሁሉን አቀፍ ሥርዓት በመነፈጉ እንዲሁም በመከዳቱ ባለፉት አምስት ዓመታት በታሪኩ አይቶት የማያውቀውን አስቸጋሪ ጊዜ በማሳለፍ ላይ ይገኛል።"

እናት ፓርቲ

የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ሚያዚያ 24/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በወቅታዊ ጉዳይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ:-

"ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ..." ይገባል!

የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመጥነውን የፖለቲካ መሪ በማጣቱ፣ አካታችና ሁሉን አቀፍ ሥርዓት በመነፈጉ እንዲሁም በመከዳቱ ባለፉት አምስት ዓመታት በታሪኩ አይቶት የማያውቀውን አስቸጋሪ ጊዜ በማሳለፍ ላይ ይገኛል።

የፖለቲካው መስመር መሳትና ተለዋዋጭነት፣ የውስጥና የውጭ ኃይሎች ቀጠናዊ ፍላጎት፣ ስሁት የጎሰኝነት ትርክቶች፣ መዋቅራዊና ሥርዓታዊ ችግሮች ወዘተ. ህዝባችንን ማብቂያ በሌለው መከራ ውስጥ እንዲኖር አድርጎታል።

በተለይም ባለፉት ሁለት ዓመታት በሕወሓት እና በፌደራል መንግስቱ መካከል የተደረገው ደም አፋሳሽ ጦርነት እና በምዕራብና ማእከላዊ ኦሮሚያ መንግሥት “ኦነግ ሸኔ” ብሎ በሚጠራው ቡድን በንጹሐን ላይ ሲፈፀም የዘለቀው ጅምላ ጭፍጨፋ ኢትዮጵያዊያንን በማይሽር ጥልቅ ሐዘን ውስጥ እንዲወድቁ አድርጓቸዋል።

ከላይ የጠቀስነውና ብዙ ሺህዎች ውድ ሕይወታቸውን ያጡበት የግድያ አዙሪት ቀጥሎ በቅርብ ጊዜያት በምሥራቅ ወለጋ ነቀምቴ፣ በሰሜን ሸዋ ጓሳ እንዲሁም በደቡብ ኦሞ የገዥው ፓርቲ አመራሮች፣ የመንግሥት ተሿሚዎች እና አጃቢዎቻቸው ሕይወታቸውን አጥተዋል።

እነዚህ ግድያዎች በዓላማም ይሁን በሴራ ይፈጸሙ የዜጎች ሕይወት ጠፍቷል።

ግድያውን ተከትሎ አስቀድሞ ጣት የመቀሳሰር ሁኔታዎችን በማቆም ተገቢው ምርመራ ተደርጎ እንደ ዜጋ ፍትህ ሊሰጣቸው እንደሚገባ እናት ፓርቲ በጽኑ ያምናል፡፡ ለሟች ቤተሰቦችም መጽናናትን ይመኛል።

ከዚህ ውጭ ምርመራ ባልተካሄደበትና ጥፋተኞች በአግባቡ ባልተለዩበት ሁኔታ የሚደረጉ ፍረጃዎች የፍትህ አሰጣጡን በእጅጉ እንደሚያዛቡ መረዳት ያስፈልጋል።

መንግስት በቅርቡ የፕሪቶሪያን ስምምነት መሠረት አድርጎ (ምንም እንኳ በስምምነቱ የተጠቀሱት ነጥቦች ባይሟሉም) ከሕወሓት ጋር የሰላም ስምምነት ላይ መድረሱን አሳውቋል።

በጦርነቱ ውድ ሕይወታቸውን ያጡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እንደዋዛ ተረስተው የግጭቱ ዋና መሐንዲሶች ሲሸለሙ አገርም ዓለምም ታዝቧል።

ከዚህ በተጨማሪ ችግሮች የከፋ አደጋ ሳያደርሱ በፊት እንደ አግባቡ በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት ባለመቻሉ እንደ አገር ከላይ የጠቀስናቸውን ኪሳራዎች አስተናግደናል። ይህም መንግስት ምን ያህል አክሳሪ የፖለቲካ አካሄድ እየተከተለ እንደሚገኝ ያሳያል።

የውይይት ሂደቱ ያለበት ደረጃ ባይታወቅም፤ መንግስት ሚያዚያ ፲፯/፳፻፲፭ ዓ.ም ከ"ሸኔ" አሸባሪ ቡድን ጋር ድርድር ለማድረግ ታንዛኒያ (ዛንዚባር) ላይ ቀጠሮ መያዙንና ድርድር መጀመሩም ይፋ ከሆነ ሰንብቷል።

ስለሆነም፡-

፩. ካለ ፍትሕ ሰላምን ማስፈን አስቸጋሪ መሆኑን ብናምንም ድርድሩ ከተለመደው የሴራ ፖለቲካ በጸዳ መልኩ ተከናውኖ በስቃይ ውስጥ የሚገኘውን ሕዝባችንን ሊታደግ በሚችል መልኩ እንዲቋጭ እንመኛለን፡፡

መንግስት ለሀገራችን ኢትዮጵያ የሚጠቅም ሀሳብ ካላቸው ፓርቲዎች ጋርም የጋራ መግባባትን ለማስፈን የሚያስችል ውይይት እንዲያደርግም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

፪. የአማራ ክልል ብልጽግና ኃላፊ ግድያን ተከትሎ መንግስት አሁንም "ኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች"ን ትጥቅ በማስፈታት "ሰላም አስከብራለሁ" በሚል በአማራ ክልል የጀመረው እንቅስቃሴ ከሕወሓትና “ኦነግ ሸኔ” ጋር የታለፈበትንና አገርን ውድ ዋጋ ያስከፈለ አካሄድ የሚደግም ነው፡፡

መንግስት ካለፈ ስህተቱ መማር ሲገባው ወደ ሌላ የግጭት አዙሪት አገርንና ሕዝብን የሚከት፤ የክልሉን ወጣት ለአመጽ የሚጋብዝ፣ በዚህም ከቀደሙት መደበኛ ጦርነትና የሽምቅ ውጊያ ሂደቶች ትምህርት ያልወሰደ፣ የሚያስከትለውንም መጠነ ሰፊ ጉዳት እና መዘዝ በአግባቡ ያላገናዘበ አደገኛ የማንአለብኝነት አካሄድ እየተከተለ መሆኑን እናት ፓርቲ ያምናል።

ስለዚህ ከጀመረው የጅምላ እስር፣ የትጥቅ ማስፈታት ዘመቻ፣ የድርጅቶችን የንግድና የገንዘብ እንቅስቃሴ የማገድ ሂደት ወዘተ. በእሳት ላይ ቤንዚን የማርከፍከፍ አካሄዶች ራሱን አቅቦ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ሊፈቱ በሚችሉበት ሁኔታዎች ላይ ብቻ እንዲያተኩር አጽንዖት ሰጥተን እናሳስባለን።

፫. አበው "ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ…" እንዲሉ ከዚህ ውጭ የድርድርና የውይይት ፍኖትን ባለመሻት መንግሥት በማንአለብኝነት አካሄዱ ቀጥሎ በአገርና በሕዝብ ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ዓይነት ጥፋትና ውድመት ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ እናት ፓርቲ በጽኑ ያምናል።
3.5K views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 18:45:20
3.0K views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 18:45:15 "የአብይ አህመድ ፋሽስታዊ አገዛዝ አማራን የማጥፋት ዘመቻውን በይፋ አውጇል፤ አማራ! በተደራጀ ሁኔታ በአንድነት ቆመህ ህልውናውን አስጠብቅ!"

ዓለምአቀፍ የአማራ ንቅናቄ

የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ሚያዚያ 24/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ከዓለምአቀፍ የአማራ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ:-

የአብይ አህመድ አገዛዝ ይዞት የተነሳውን አማራን የማጥፋት ኦነጋዊ ተልዕኮ ለመፈጸም “የማያዳግም እርምጃ” ያለውን ፋሽስታዊ ጥቃት የአማራው
ንቅናቄ መሠረት በሆነው የአማራ ክልል ሕዝብ ላይ በይፋ አውጇል።

በኢትዮጵያ መንግሥት ስም የሚያዝበትን በሙሉ ኃይል የተደራጀ የአገሪቱን የመከላከያ ሠራዊት አዝምቶ፣ የክልል ልዩ ኃይል ተብለው የታጠቁ የአማራ ወጣቶችን ትጥቅ ሲያስፈታ፣ የፋኖ አባላትን ሲያሳድድና ነቅተው
የሚያነቁና የሚያደራጁ አማራዎችን ሲያፍን ቆይቶ፣ አማራውን ምንም ዓይነት የመከላከል አቅም እንዳይኖረው በማድረግ ለሁለገብ ጥቃት
ለማጋለጥ የጀመረውን ዘመቻ “የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል” በሚለው መዋቅሩ በኩል ገልጿል።

ይህን ጦርነት ያወጀው፣ በቅድሚያ የአገር ህልውና ስጋት ነው ብሎ፣ የአማራውን ልዩ ኃይልና ሕዝባዊ ሠራዊት እንዲሁም ፋኖን ከአገሪቱ
መከላከያ ኃይል ጋር አሰልፎ ሲዋጋው የነበረውን የወያኔን ኃይል፣ ተመልሶ እንዲጠናከር ጊዜ ሰጥቶ፣ በሠላም ስምምነት ስም አማራን የማጥፋት
የጋራ ቃል ኪዳናቸውን ዳግም ባደሱበት፤ እንዲሁም “ኦሮሚያ” በሚሉት ምድር እስከትጥቁ አስገብቶ በሠራዊትና በጦር መሣሪያ እያደረጀ
ባለፉት 5 ዓመታት የአማራን ዘር ሲያስፈጅበት የቆየውን የኦነግን ሠራዊት በዓለም አቀፍ መድረክ በሚተወን “የእርቅ ድርድር” ከወንጀሉ አጽድቶ
በግላጭ የኦነጋዊው ኃይሉ አካል ለማድረግ በሚዘጋጅበት ጊዜ ነው።

ለ27 ዓመታት በደረሰበት በደል የተነሳ በፀረ ወያኔ አቋም ተጀምሮ፣ የወያኔ ወረራ በፈጠረው አስገዳጅ ሁኔታ ተደራጅቶና ታጥቆ ራስን
ወደመከላከል ያመራውን የአማራ ንቅናቄ አብይ አሕመድ ከጅምሩ በስጋት ሲመለከተው ቆይቷል። “ይች ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም” በሚል
ዘይቤ፣ የአማራን ታጥቆ የመመከት አቅም ለማመንመን የሚከተለው የተጋለጠ ብልሃት በአገልጋዩ በብአዴን መንደር ሽብር መፍጠር ነው።

“ገድሎ ማልቀስ” በሚባለው በዚህ ዘዴ ታግዞ አገልጋይ የብአዴን ታማኞቹን በጭካኔ በማስገደል በሚቆጣጠረው የአገሪቱ የብዙኃን መገናኛ በፈጠረው
ሽብር፣ የአማራው ንቅናቄ አካል የሆነውን ወታደራዊ አቅም ለማዳከም አልሞ፣ ትናንት አምባቸው መኮንንና ጓዶቹን ገድሎ ጀነራል አሳምነው ጽጌ
በአማራ ልዩ ኃይል ስም የመለመላቸውን የበቁ የአማራ አዋጊ መኮንኖች በመፍጀት የአማራውን ኃይል የተዋጊነት ብቃት ለማዳከም ሞክሯል።

ዛሬ ደግሞ በሠራዊት ብዛትና በጦር መሣሪያ የደረጀ ጦሩን በመላው የአማራ ክልል አሰማርቶ ፋኖን ሊያሳድድና አማራን ሊፈጅ ዝግጅቱን በጨረሰበት
ጊዜ፣ እንደለመደው ግርማ የሺጥላን አስገድሎ ሁከት በማወጅ ለሠራዊቱ የጭፍጨፋ ትዕዛዙን ሰጥቷል።
በዚህ ዘመቻ ብዙ የአማራ ክልል ከተሞች በአብይ አሕመድ ወታደሮች ተወርረዋል፤ የቤት ለቤት አሰሳ እየተደረገ ሰዎች ይታፈናሉ፤ ይገደላሉ፤
የተፈላጊ ሰዎች ቤተሰብ፣ ሕጻናት፣ ነፍሰጡር ሴቶችና አረጋውያን ሳይቀሩ ታፍነው ይወሰዳሉ፤ ኗሪዎች በነጻነት መዘዋወር የእለት ኑሯቸውን
መምራት አይችሉም።

ይህ ውጥረት እስካሁን ካለፈባቸው አስከፊ ሁኔታዎች ጋር ተዳምሮ አማራውን አማራጭ በማሳጣት ወደመረረ ጦርነት
ሊያስገባው እንደሚችል ይታመናል።

የአማራ ህዝብ ሆይ፣
በህልውናህ ላይ ከመቸውም ጊዜ የከፋ አደጋ አንዣብቧል። ራስን መከላከል ሰጪና ነሺ የሌለበት ተፈጥሯዊ መብት ነው። አያት ቅድም
አያቶቻቸው ደማቸውን አፍስሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው ባወረሷቸው አገር ላይ የወገናቸው መጨፍጨፍ ላስከፋቸውና በነገዳዊው አገዛዝ
ምክንያት የባለአገርነት መብት ማጣትን እምቢ ብለው ለተነሱ ፋኖዎችህ ከለላ መሆን ራስህን ለማዳን የምታደርገው ትንሹ ተግባር ነው።

ትናንት በወያኔ ወረራ እንዳየኸው የቤተሰብህ፣ የመንደርህና የከተማህ ደኅንነት በገዛ ልጆችህ እንጂ አብይ አሕመድ በሚያዘምትብህ ወታደርና ከውስጥህ
በበቀሉ ከሃዲ አገልጋዮች ሊጠበቅ አይችልም።

ስለዚህ፣ ዓለምአቀፍ የአማራ ንቅናቄ፣ መላው አማራ በአንድነት በአብይ አሕመድና በአገልጋዮቹ
ዛቻ እና ማደናገሪያ ሳይረታ፣ በክልሉ የተሰማራው ጦር ለቅቆ እስከሚወጣ እምቢታውን እንዲቀጥልና የሚሳደዱ ልጆቹን እንዲደግፍ እያሳሰበ፣
አማራው ህልውናውን ለማስከበር በሚያደርገው በማናቸውም የትግል ዘርፍ ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ አብሮት የሚቆም መሆኑን ዳግም
ያረጋግጣል።

ህልውናችን በትግላችን!
ዓለምአቀፍ የአማራ ንቅናቄ።
3.2K views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 16:35:54
እነዚህ “ሽማግሌ” ነን የሚሉ ስብሰቦች የአማራ ህዝብ በማንነቱ ሲጨፈጨፍ: በማንነቱ በጅምላ ሲታሰር: አማራ በመሆኑ ቤቱ እየፈረሰ ሜዳ ላይ ሲወድቅ: በማንነቱ ከስራ ሲታገድ: የንግድ ተቋማቱ ሲታገዱበት : ህልውናው አደጋ ላይ ሲወድቅበት በሀገሩ እንደሌለ እንዳልሰማ ዝም ይላሉ።

አማራ በህልውናው መጥተውበት ራሴን ልከላከል ሲል በአገዛዙ እየተላኩ በሀይማኖቱ እና እሴት አክባሪነቱ ምክንያት አሳልፈው ይሰጡታል። የአማራ ህዝብ መታለል ማቆም አለበት። ህዝቡም ከአገዛዙ ጋር እየተሻረኩ ዋናዎቹን አሳልፈው የሚሰጡ ሽማግሌዎችን ተው ሊላቸው ይገባል።
3.5K views13:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 18:13:35
መረጃ
ሚያዚያ 23 2015 አ/ም

በዛሬው ዕለት በአማራ ክልል በተለያዮ ከተሞች ወጣቶች እየታፈሱ ነው

በምዕራብ ጎጃም በቡሬ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች እየታፈሱ መሆኑ የአካባቢው ህዝብ ገልጿል።

"ልጆቻችን ሰልፉን መርታችኋል፣ብልፅግናን አትደግፉም፣ፋኖ ናችሁ ወ.ዘ.ተ እየተባለ ዛሬ ሲታፈሱ መዋላቸው ተገልጿል።ሰልፉን ስትደግፉ ነበራችሁ የተባሉ የፖሊስ አባላትም ከፍተኛ ስድብ እና ማሳደድ እየደረሰባቸው እንደሆነ የመረጃ ምንጫችን ገልጿል።

በቡሬ ከተማ ወጣቱን፣ፋኖን፣የፖሊስ አባላትን እና ሙሁራንን እየጠቁሙ የሚያሳፋሱ የኦህዴድ የብልፅገ አሽከሮች:-

1ኛ)አበጀ ሙላት የከተማው ከንቲባ

2ኛ) ኮማንደር አዱኛ ምትኬ የአንደኛ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ

3ኛ) ሻለቃ ጌታነህ የቡሬ ከተማ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ

4ኛ) ጌታቸው አላምር የሚኒሻ ፅቤት ኃላፊ

5ኛ) አንተነህ ደህንነት የከተማው ዋና ሰላይ እና

6ኛ) ኮማንደር አዳምጥ በዋናነት ይገኙበታል ስትል የመረጃ ምንጫችን ገልፅለች።
4.2K views15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ