Get Mystery Box with random crypto!

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_media_center — አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center
የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_media_center — አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center
የሰርጥ አድራሻ: @amhara_media_center
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.55K

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-16 18:55:37
2.3K views15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 18:55:36 በባሕርዳር ለ150 ሰዎች የትንሳኤን ምክንያት በማድረግ ልዩ ድጋፍ ተደረገ

የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ150 ሰዎች ልዩ ድጋፍ በባሕርዳር ያደረገው ከተለያዩ አካላት ድጋፍ በማሰባሰብ የባሕር ዳር ልጆች አረጋውያን ማሕበር ነው።

ማህበሩ በተለያዩ የበዓል ቀናት አቅመ ደካማለሆኑ የከተማዋ ኗሪዎችድጋፍ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ የትንሳኤ በዓልንና ቀጣዩን የረመዳና በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ ድጋፍ አደርጓል።

በዚህም አቅም የሌላቸው ወገኖችን በዓሉን ከማጣት ተላቀው እንዲያሳልፉ ማድረግ የተቻለ ሲሆን በዚህም ታላቅ የባህርዳር ወጣቶች : ባለሀብቶች ፣ የጽዋ ማህበራት ና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያን ተሳትፎ አድርገዋል።


ዛሬ ከ150 በላይ የሚሆኑ ጧሪ ያጡ አረጋዊያንን እንደተለመደው የማግደፍና የከብት ቅርጫ ስጋ በማደል አቅም ካላቸው ጎረቤቶቻቸው እኩል መዋል እንዲችሉ ተደርጓል ያለው ማሕበሩ በተጨማሪም ለ9 የእስልምና እምነት ተከታይ አረጋዊያን ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል።

የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ150 ሰዎች ልዩ ድጋፍ በባሕርዳር ያደረገው ከተለያዩ አካላት ድጋፍ በማሰባሰብ የባሕር ዳር ልጆች አረጋውያን ማሕበር ነው።

ማህበሩ በተለያዩ የበዓል ቀናት አቅመ ደካማለሆኑ የከተማዋ ኗሪዎችድጋፍ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ የትንሳኤ በዓልንና ቀጣዩን የረመዳና በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ ድጋፍ አደርጓል።

በዚህም አቅም የሌላቸው ወገኖችን በዓሉን ከማጣት ተላቀው እንዲያሳልፉ ማድረግ የተቻለ ሲሆን በዚህም ታላቅ የባህርዳር ወጣቶች : ባለሀብቶች ፣ የጽዋ ማህበራት ና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያን ተሳትፎ አድርገዋል።


ዛሬ ከ150 በላይ የሚሆኑ ጧሪ ያጡ አረጋዊያንን እንደተለመደው የማግደፍና የከብት ቅርጫ ስጋ በማደል አቅም ካላቸው ጎረቤቶቻቸው እኩል መዋል እንዲችሉ ተደርጓል ያለው ማሕበሩ በተጨማሪም ለ9 የእስልምና እምነት ተከታይ አረጋዊያን ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል።

በዝግጁቱ ላይ የተገኙት የከተማዋ ከንቲባዶክተር ድረስ ሳህሉ በዓልን ከተቸገሩ ወገኖች ጋር በጋራና በፍቅር ተካፍሎ ማሳለፍ የቆየ ባህላችን በመሆኑ ሊቀጥል የሚገባው ልዩ እሴት ነው ብለዋል።

ዶክተር ድረስ ይህ በጎ ተግባር በከተማዋ እያደገና እየሰፋ ምጣት አለበት ያሉ ሲሆን ለትብብር ለአብሮነትና ለመረዳዲት የሚደረጉ ጥረቶችን ሁሉ እንደግፋለን ከጎናችሁ እንቆማለን በማለት ተናግረዋል።

በእለቱ የተለያዩ የከተማዋ ኗሪዎችና የባሕርዳር ከተማ አመራሮች በቦታወ ተገኝተው ከአረጋውያኑ ጋር በዓሉን ያከበሩ ሲሆን በማሕበሩ ልዩ ምስጋና ተደርጎላቸዋል።
2.3K views15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 14:31:10
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በመሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ጋዜጠኛችን ዓባይ ዘውዱን ጨምሮ በህሊና እስር ውስጥ ለምትገኙ በሙሉ የነፃነት ትንሳኤን ያቅርብልን፥ በያላችሁበት እንኳን አደረሳችሁ።

መልካም በዓል

ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት እና አማራ ሚዲያ ማዕከል
2.7K views11:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 19:42:38
‹‹በሚዲያ የአማራ ሕዝብ ግፍ ደርሶበታል ብለህ ሕዝቡን አነሳስተሀል›› ሲል ፖሊስ ወነጀለ!

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርቧል። ጋዜጠኛው የአማራ ሕዝብ ግፍ ደርሶበታል በማለት መንግስትን አስገድዶ ከስልጣን ለማውረድ በሚዲያ ሲንቀሳቀስ ነበር። ተከባብሮ የሚኖርን ሕዝብ ለመለያት ሲሰራ ነበር የሚል ክስ የቀረበበት ሲሆን፤ ለተጨማሪ ማጣራት 14 የምርመራ ቀን ታስሮ ይቆይልን ሲል ፖሊስ ጠይቋል።

የጋዜጠኛው ጠበቆች በበኩላቸው ፤ የሚዲያ ባለሙያ ታስሮ የሚጣራበት የሕግ አግባብ የለም ስለዚህ የዋስትና መብቱ ተከብሮ በዋስ ይለቀቅ›› ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። አክለውም -ደንበኛችን ከሕግ አግባብ ውጪ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ 48 ሰዓት አልፎታል፤ የመብት ጥሰት ተከናውኖበታል ሲሉ ፖሊስን ከሰዋል። ፖሊስም ‹‹ከባህርዳር መከላከያ ነው የያዘው፤ ከእነሱ እስክንረከብ ነው ጊዜ የሄደብን›› የሚል ምላሽ ለፍርድ ቤቱ ሰጥተዋል።

በመጨረሻ፣ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ በጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ላይ የ10 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በተያያዘ ዜና የኢትዮ ሰላም ሚዲያ ባለቤት የሆነውና ከጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ጋር በአንድ መዝገብ የተከሰሰው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው፤ በተመሳሳይ ክስ የተከሰሰ ሲሆን፤ የአስር ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶበታል። ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በአሁኑ ሰዓት ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ጊዜያዊ እስረኛ ማቆያ በእስር ላይ ይገኛል፡
ዘገባው የኢትዮ 251 ነው
3.4K views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 19:40:58
ሱዳን ዛሬ
3.2K views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 21:16:34
አርቲስት ዮርዳኖስ አለሜ ከበደ የሰሞኑ መንግስት መር አማራ ተኮር የ አፈና ዘመቻ ሰለባ ሆኗል።

የአማራ ልዩ ኃይልን የማፍረስ እቅዱን ተከትሎ ድምፅ ይሆናሉ ለአማራ ይቆማሉ ተብለው መንግስት ላይ ስጋት ያሳደሩ አማራዊያን እየታሰሩ መሆኑን ይታወቃል።

አርቲስት ዮርዳኖስ አለሜ “ሁከት እና ብጥብጥ ” በሚል የህሊና እስር ላይ ይገኛል።

አማራ ከገጠመው የህልውና ፈተና ለመውጣት ትግል የሚያደርጉ የነቁ የአማራ ልሂቃን: ጋዜጠኞች እና ታዋቂ አማራዎችን በማፈን የሚቆም ትግል የለም።
693 views18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 03:12:03 #ሰበር
ትጥቅ በፈቱ በአማራ ልዩ ኃይል አባላት ላይ ጥቃት ተፈፀመ።

ከደሴ ወደ ሸዋሮቢት በሁለት መኪና ተጭነው ይጓዙ በነበሩ ትጥቅ የፈቱ የልዩ ኃይል አባላት ላይ ጥቃት የከፈተው ኦነግ ሸኔ መሆኑን ለኢትዮ 251 ሚዲያ መረጃውን ያደረሱ ምንጮች ገልጸዋል። እንደምንጮቻችን መረጃ ከሆነ ጥቃቱ የተከፈተባቸው፤ ገርቢና ባልጪ በተባለ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ውስጥ ነው።

የጥቃቱንና የተጎጂዎችን መጠን ለማወቅ ከሚመለከተው የክልሉ ቢሮ ደጋግመን ያደረግነው ሙከራ ሊሳካልን አልቻለም። ሆኖም እንደመረጃ ምንጮቻችን ከሆነ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የአማራ ልዩሀይል የህይወት መስዋዕት መክፈላቸውን ለማወቅ ችለናል።

በተያያዘ ዜና በወልቃይትና በራያ አላማጣ እና በኮረም በኩል ህወሓት ወረራ ለመፈፀም እየተዘጋጀ ሲሆን፤ በመተማ ዮሀንስ ሰፈር 4 የልማት ቦታ ደግሞ የሱዳን ጦር ዘልቆ መግባቱን ምንጮቻችን አስታውቀዋል።

ምንጭ ኢትዮ 251
3.3K views00:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 00:12:52
ምን አይነት ዘመን ነው??!
447 views21:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 18:43:11 ልዩ ሀይሉን ወደ መረጠውና ወደ ተመደበበት እያንቀሳቀስን ነው -ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ

የአማራ ክልል “ወደ መደበኛ የክልል ፖሊስ ስራ እንገባለን” ያሉ የአማራ ልዩ ኃይል አባላትን፤ በክልሉ ወደሚገኙ ዞኖች መድቦ እያንቀሳቀሰ መሆኑን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የአስተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ ተናገሩ። “በመደናገር” ወደ ተለያዩ አካባቢዎች “የተበተኑ” የልዩ ኃይል አባላትን የሚያሰባስቡ ግብረ ኃይሎች በዞን እና ወረዳ ደረጃ መቋቋማቸውን አስተባባሪው ገልጸዋል።

ዶ/ር ሰማ ይህን የገለጹት፤ በአማራ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ትላንት ረቡዕ ሚያዚያ 4፤ 2015 በሰጡት መግለጫ ነው። የትላንቱ የዶ/ር ሰማ ማብራሪያ፤ የክልል ልዩ ኃይሎችን “እንደገና ለማደራጀት” በፌደራል መንግስቱ የተወሰነው ውሳኔ እና የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ዋና ትኩረቱን ያደረገ ነበር።

የክልል ልዩ ኃይሎችን በተመለከተ የተላለፈው ውሳኔ “በሁሉም ክልሎች እየተፈጸመ ነው” ያሉት ዶ/ር ሰማ፤ “ይሄ ባለበት ሁኔታ የአማራ ክልልን ልዩ ኃይል ብቻ ባለበት እንዲቆይ ማድረግ፣ ወደ ፌደራል ጸጥታ ተቋማት እንዳይገባ መከልከል የሚቻል አይደለም” ሲሉ ተደምጠዋል።

የአማራ ክልል ይህን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ ባደረገበት ወቅት፤ በሁለት ምክንያቶች “ችግሮች” ማጋጠማቸውን ዶ/ር ሰማ በትላንቱ ማብራሪያቸው አንስተዋል። ዶ/ር ሰማ ለችግሮቹ መፈጠር በቀዳሚነት የጠቀሱት፤ ከክልሉ ልዩ ኃይል አባላት ጋር “ቀድሞ ውይይት ተደርጎ፣ በቂ መግባባት በማድረግ ረገድ፣ የተፈጠረ ክፍተትን” ነው። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ፤ ዶ/ር ሰማ “ብጥብጥ እና አመጽ በማስነሳት ስርዓት የመቀየር ፍላጎት ያላቸው” ሲሉ የገለጿቸው “ኃይሎች” ፈጠሩት ያሉት “የውሸት ፕሮፓጋንዳ” ነው።

በዚህ ፕሮፓጋንዳ ምክንያት “የተበተኑ” የልዩ ኃይል አባላት መኖራቸውን የአማራ ክልል የአስተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪው ገልጸዋል። እነዚህን “ተደናግጠው” እና “በመደናገር” ተበተኑ የተባሉትን የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላት የሚያሰባስብ ግብረ ኃይል፤ በክልሉ ስር በሚገኙ ወረዳ እና ዞኖች እንዲቋቋም መደረጉን ዶ/ር ሰማ በትላንቱ ማብራሪያቸው አስታውቀዋል።
2.1K views15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 18:43:11
2.0K views15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ