Get Mystery Box with random crypto!

በባሕርዳር ለ150 ሰዎች የትንሳኤን ምክንያት በማድረግ ልዩ ድጋፍ ተደረገ የትንሳኤ በዓልን ምክ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

በባሕርዳር ለ150 ሰዎች የትንሳኤን ምክንያት በማድረግ ልዩ ድጋፍ ተደረገ

የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ150 ሰዎች ልዩ ድጋፍ በባሕርዳር ያደረገው ከተለያዩ አካላት ድጋፍ በማሰባሰብ የባሕር ዳር ልጆች አረጋውያን ማሕበር ነው።

ማህበሩ በተለያዩ የበዓል ቀናት አቅመ ደካማለሆኑ የከተማዋ ኗሪዎችድጋፍ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ የትንሳኤ በዓልንና ቀጣዩን የረመዳና በዓል ምክንያት በማድረግ ልዩ ድጋፍ አደርጓል።

በዚህም አቅም የሌላቸው ወገኖችን በዓሉን ከማጣት ተላቀው እንዲያሳልፉ ማድረግ የተቻለ ሲሆን በዚህም ታላቅ የባህርዳር ወጣቶች : ባለሀብቶች ፣ የጽዋ ማህበራት ና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያን ተሳትፎ አድርገዋል።

ዛሬ ከ150 በላይ የሚሆኑ ጧሪ ያጡ አረጋዊያንን እንደተለመደው የማግደፍና የከብት ቅርጫ ስጋ በማደል አቅም ካላቸው ጎረቤቶቻቸው እኩል መዋል እንዲችሉ ተደርጓል ያለው ማሕበሩ በተጨማሪም ለ9 የእስልምና እምነት ተከታይ አረጋዊያን ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል።

በዝግጁቱ ላይ የተገኙት የከተማዋ ከንቲባዶክተር ድረስ ሳህሉ በዓልን ከተቸገሩ ወገኖች ጋር በጋራና በፍቅር ተካፍሎ ማሳለፍ የቆየ ባህላችን በመሆኑ ሊቀጥል የሚገባው ልዩ እሴት ነው ብለዋል።

ዶክተር ድረስ ይህ በጎ ተግባር በከተማዋ እያደገና እየሰፋ ምጣት አለበት ያሉ ሲሆን ለትብብር ለአብሮነትና ለመረዳዲት የሚደረጉ ጥረቶችን ሁሉ እንደግፋለን ከጎናችሁ እንቆማለን በማለት ተናግረዋል።

በእለቱ የተለያዩ የከተማዋ ኗሪዎችና የባሕርዳር ከተማ አመራሮች በቦታወ ተገኝተው ከአረጋውያኑ ጋር በዓሉን ያከበሩ ሲሆን በማሕበሩ ልዩ ምስጋና ተደርጎላቸዋል።