Get Mystery Box with random crypto!

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_media_center — አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center
የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_media_center — አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center
የሰርጥ አድራሻ: @amhara_media_center
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.55K

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-13 17:52:30
2.1K views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 17:52:24 2. የውያኔ ወራሪ ኃይል ትጥቅ ባለፈታበትና አማራው መልሶ በመስዋእትነቱ ያስከበራቸውን አፅም እርስቶቹን ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጸለምትና ራያን በምእራብውያን ተፅእኖ መልሶ ለመቆጣጠር ጥረት በሚያደርግበት በአሁኑ ግዜ፤ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና የአማራ ሚሊሺያ በአማራው ህዝባዊ እምቢተኛነት እየታገዘ በተጠንቀቅ በመቆም የአብይ አህመድን
ትጥቅ የማስፈታትና የአማራን ህልወና የመግሰስ ዘመቻ ሊያኮላሹ ይገባል። አገር እያፈረስ ያለውን አገዛዝ በህዝባዊ እምቢተኝነት የታገዘ ትግል ለማድረግ የተጠናከሩ አደረጃጀቶችና መሪዎችን በመፍጠር፤ የችግሩን ምንጭ ከአራት ኪሎ ማስወገድ ካልተቻለ የአማራ ህዝብ በታሪኩ ያላየውና ያልደረስበት ግፍና መከራ ከፊታችን እንደተጋረጠ በመገንዘብ
ህዝባዊ ትግሉን በስፋትና በጥልቀት በማሳደግ እንድታቀጣጠሉ ጋሻ የአማራ ድርጅት አስቸካይ ጥሪ ያቀርባል።

3. በኢትዬጵያ ውስጥ የምትንቀሳቀሱ የፓለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የወጣት አደረጃጀቶች፣ የሙያ ማህበራት፣የሴቶችና የእናቶች አደረጃጀቶች፣ የዩኒቨርስት ተማሪዎችና አስተማሪዎች፣ የነጋዴ ማህበራቶች በአጠቃላይ በመላው ሀገሪቱ የተደራጃችሁ አደረጃጀቶች በሙሉ፤ ይህንን አገር አፍራሽ፣ ህዝብ ገዳይና ጨፍጫፊ የኦህዴድ የብልፅግና መንግስት መግለጫ በማውጣት ብቻ የማናስወግደው መሆኑን ተገንዘበን የመረረ ህዝባዊ ትግል በማድረግ አገርን ከማፍረስ ህዝብን ከመፍለስ እንድትታደጉ አስቸኳይ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

4. በመጭረሻም የአማራ የትግል አብሪ የሆነውን እርበኛ ዘመነ ካሴንና ሌሎች ለአማራው ህዝባችንና ለኢትዮጵያ የተዋደቁ ጀግኖቻችንን ከማክበርና ከመሽለም ይልቅ በማዋረድና አንገት በማስደፈት እስር ቤት የተወረወሩ ወገኖቻችንን በመንግስት ልምምጥና ልመና ሳይሆን ህዝቡ በራሱ ትግል እንዲይልስፈታቸው የመጨረሻ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

አማራው በረዥሙ ያሽንፋል!!!
ጋሻ የአማራ ድርጅት
2.1K views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 17:52:24 የአማራ ልዩ ኃይልን ማፍረስ፣ አማራን በከበባ የማጥፋት የአብይ/ኦሮሚማ ሴራ ነው!
ከጋሻ የአማራ ድርጅት የአቋም መግለጫ

የአማራ ሚዲያ ማዕከል
ሚያዚያ 5 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የአማራ ህዝብ ላለፈው 27 አመት በዘረኛው የህዋት የመንግስት ዘመን ሲገደል ሲታስር ሲፈናቀል የኖረ ማህበረስብ ሲሆን በወልቃይትና በጉራ ፈርዳ፣ በወተር፣ በበደኖ፣ በአርባ ጉጉ፣ በሐረር፣ በአሩሲና አሁን ደግሞ በቅርቡ በማይካድራ የዘር ማጥፍት ወንጀል የተፈጸመበት ሲሆን ባለፉት 5 አመታት ደግሞ በጨፍጫፊውና በገዳዩ በአብይ መንግስት ስር በተቃቃሙ የገዳይ
ቡዱኖች በኦነግ፣ ኦነግ ሽኔና በኦሮሞ ልዩ ሃይል በቤንሻንጉል፣ ጉምዝ በወለጋ አራቱም ዞኖች፤ በአጣዬ ከአስራ አንድ ግዜ በላይ ግድያና ጭፍጨፍ በመፈፅም በጅምላ በመቅበር በአማራ ህዝብ ላይ ከፍተኛ የዘር ማጥፍት ወንጀል የፈጸሙ ሲሆን እስካሁን ድረስ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የአማራ ተወላጆችን ከወለጋ፣ ከቤንሻንጉል፣ ከአጣዬና ከአዲስ አበባ ዙሪያ በማፈናቀል ከዘር ማጥፍት፣ ግድያና ጭፍጨፍ የተረፈው ደግሞ በረሃብ፣ በእርዛትና በበሽታ እንዲያልቅ በአማራ ህዝብ ላይ አብይ የሚመራው የኦህዴዱ-ብልፅግናው/የኦሮሙማ መንግስት ከፍተኛ ወንጀል ፈፅሟል።

ባለፍት ሁለት አመታት ደግሞ ትግራይ ውስጥ የነበረውን ጦርነት በአሻጥር ወደ አማራ ክልል መልሶ በማምጣት የአማራ ህዝብ የኢኮነሚ ተቋማት፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ ሆስፒታሎች፣ ትህምርት ቤቶች፣ መንገዶች፣ የንግድና የኢንቨስትመንት ተቋሞች እንዲወድሙ በማድረግ የአማራን ክልል ኢኮኖሚ አርባ አመታት ወደ ሃላ የመለሰ ሲሆን በገንዘብም ከ40 ቢሊዮን ብር በላይ በክልሉ ላይ ኪሳራ እንዲደርስ አድርጓል ።

በጦርነቱም ወቅት በህዝብ ከተስበስበ ግብርና ቀረጥ ደመወዝ የሚከፈለው የመከላከያው ስራዊት ሆን ተብሎ እንዲሽሽ በማድረግ የአማራ ገበሬዎችና ወጣቶች በከፍተኛ ቁጥር የተገደሉ ሲሆን እናቶችና ህፃናት በወራሪው ሃይል እንዲደፈሩ አድርጓል።

የመከላከያው ጦሩ በዚህ መልኩ ህዝቡን ለህዋት ወራሪዎች ለአደጋ እያጋለጠ በሚሽሽብት ግዜ የአማራው የቁርጥ ቀን ልጆች የሆኑት የአማራ ልዩ ሃይልና፣ፋኖ እንዲሁም ሚሊሺያ በከፈሉት የላቀ መስዋእትነት የወራሪው የህዋት ኃይል ተሽንፈው ከአማራ ክልል እንዲወጡ ተደርጋል።

ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ ይህንን የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች የሆኑትን የአማራ ልዩ ኃይል ጨካኙ የአብይ መንግስት ያለምንም ምክንያት ወይም አሳማኝ ነገር በሌለበት የአማራን ክልል ለማፈረራስ የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ማስፈታት አለብን ብሎ የአብይ ኦሆዲድ ብልፅግና ፓርቲ በወስነው መስረት ዛሬ ላይ የመከላከያ ልብስ የለበሱ የኦሮሞ ልዩ ኃይሎችን በገፍ በማስገባት የአማራ ወጣቶችን፣ የአማራ ፍኖዎችንና ልዩ ኃይሎችን እየገደሉ ሲሆን ለተቃውሞ የወጣውን የአማራ ህዝብ ግንባሩ ላይ እየተኮሱ ገድለዋል። ምንም እንኳን የክልል ኃይል የሚባል አደረጃጀት አሁን ባለው አማራን ባገለለው ሕገመንግስት ውስጥ ባይካተትም
የአማራን ልዩ ኃይል በዚህ ወቅትና ስዓት ለማፍረስ መወስኑ ከላይ እንደጠቀስነው ወቅቱን ያላገናዘበና ሆን ተብሎ አማራውን ያለጠባቂ ለማስቀረት የተወስነ ውሳኔ ነው። የውሳኔውም ዋና አላማ በእብሪተኝነት አብይ የሚከተለው የዘረኝነት ፓሊሲ ሁሉንም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኃይሎችን ተራ በተራ በመደፍጠጥ እሱ የሚመራው የኦህዲድ ብልጽግና ፓርቲ በጥናት እያራመዱ ያለውን ኢትዮጵያን የማፈራረስ እንቅስቅሴ እቅድ ለማስፈፅም የሚቻለው ያስጉኛል የሚላቸውን ኃይሎች በማጥፍት ኦሮሙማና በኢትዮጵያ መቃብር ላይ ለመመስረት እንደሆነ ለሁልም ግልፅ ነው።

በሌላ በኩል በህዋትና በብልፅግና መካከል ፕሪቶርያ ላይ ተደረገው በተባለ ሚስጥራዊ ስምምነት መሰረት ህወሀት ትጥቅ መፍታት ሲገባው ይህ ሙሉ በሙሉ ተጥሶ ባለበት፤ እንዲያም ህወሀት ለተጭማሪ ወረራ እየተዘጋጀ ባለበት፣ ሌሎች ክልሎች ትጥቅ ባልፈቱበት ሁኔታ የአማራ ልዩ ኃይልን ብቻ አፋጥኖ በተናጠል ትጥቅ ማስፈታት ፈፅሞ የማይቻል መሆኑን የብልፅግና አገዛዝ
ሊገነዝበው ይገባል። በተቃራኒው ደግሞ የኦሮሞ ልዩ ኃይል ቱርክ ሰራሽ መሳሪያዎችን በመንግስት ወጪ እንዲታጠቁ መደረጉ የብልፅግናን የተስፉፊነት ፓሊስ በግልፅ የሚያሳይ ሲሆን አሁንም የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ለማስፈታት እነዚህኑ ኃይሎች ወደ
አማራ ክልል በመከላከያ ዩኒፎርም ሽፋን ማስገባቱ በከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ መልስ ሊሰጠው ይገባል ብሎ ድርጅታችን ያምናል።

በአጠቃላይ የብልጽግና አገዛዝ በኦሮሚማ ሙሉ ቁጥጥር ያለው የመከላከያ ኃይል፣ አብይ በሚያወርደው የሃገር ማፍረስ ትእዛዝ መሰረት የሀገሪቱ ሉአላዊንት ተደፍሮ በጎንደር ለሱዳን የተስጠው መሬታችን በተያዘበት፤ በደቡብ ሱዳን የጋምቤላ መሬት ሆነ ተብሎ እንዲወረር በተደረገበት ወቅት፤ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለመውረር ምቹ ግዜ አግኝተናል እያሉ ከበባበሚፈፅሙበት ስአት፤ በብዙ አቅጣጫ የተከበበው እና መዋከብ የበዛበት አማራው ወገናችን ህልውናው ከፍተኛ አደጋ ውስጥ እያለ፣ መላው ህዝብ ከአማራው ልዩ ኃይልና ከፍኖዎች ጎን ቆሞ የኦሆዲድ ብልፅግናን ወረራ ብቻ ሳይሆን በሱዳን በኩል ሊቃጣብን የሚችለውን የሐይማኖትና ባህል የማጥፍት ጦርነት መቋቋም ብቻ ሳይሆን ማሸነፍ እንዲቻል በህዝባዊ እንቢተኝነትና ጽናት ድጋፍ እንዲአደርግ ድርጅታችን በፅኑ ያስገነዝባል።

የአማራ ህዝብ በአሁኑ ስአት መሪ የሌለው ሲሆን መሪ ነን ባዮች የቀድሞ የብአዴን፣ የአሁኑ የአማራ ብልፅግና አመራሮች ህዝባችንን ላለፈው 32 አመት እጅና እግሩን አስረው እያሳረዱትና እያስጨፈጨፉት፤ የራሱ በተባለለት ክልል ውስጥ እንኳን ተሳዳጅ ሲሆን በአዲስ አበባና በየክልሉ ቤታቸው ፈርሶ፣ ሃብታቸው ተነጥቆ፣ በየመንገዱ የወደቁትን የአማራ ወገኖቻችን
በደብረ ብርሀን የመጠለያ ካምፕ ምግብ የሚስጣቸው አጥተው በችጋር ሲረግፍ እያየ እንዳላየ የሚያልፍና የክልሉን ህዝብ ለኦሆዲድ ብልፅግናና ለትህነግ ጣምራ ወራሪዎች አሳልፈው ሰጥተውታል። በመሆኑም በክልሉ ወስጥና ከክልሉ ወጭ የሚኖረው አማራ ወገናችን በባርነት ቀንበር ውስጥ እንዲወድቅ እየስሩ ያሉ የአማራ ክልል ባለስልጣኖችን ህዝባችን አንድ በአንድ ነጥሎ በህዝባዊ አመፅና ሁለ ገብ ትግል ካላስወገዳቸው በስተቀር የአማራው ህዝባችን መብቱ ተረግጦና ተዋርዶ ለቀጣዩ መጪ ዘመናት በባርነት ቀንበር ውስጥ መውደቁ የማይታበል ሃቅ ነው።

ስለዚህ ቀጣይ የእማራነትን የዘር ማጥፍትን እና የባርነት ቀንበር ከጫንቃው ላይ አሽቀንጥሮ ለመጣል የሚከተሉትን ነጥቦች ማስቀመጥ እንወዳለን፣-

1. የእገር መከላከያ ስራዊት የአገርን ዳር ድንበርና የህዝቡን የኑሮ ዋስትና ማረጋገጥ እንጂ በህዝቦች መካከል ጣልቃ ገብቶ የአብይን ትእዛዝ ለመፈፅም የሚያደርገውን ህገወጥ ግድያ በአስቸካይ እንዲያቆምና አሁኑኑ አንዳንድ የደቡብ፣ የጋምቤላና የአማራ የመከላከያ ወታደሮች የአማራ ወገናችንና በህዝባችን ላይ አንተኩስም ያሉትን ፍትሃዊ የሆነ የህሊና ሚዛን
ያለውን ውሳኔያቸውን በመከተል ሌሎች የመከላከያ ስራዊት አባላት ህዝባችንን መግደል አቁማችሁ በአስቸካይ ከክልሉ እንድትወጡ አስቸኳይ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
2.0K views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 11:48:32
ልዩ ኃይል ይፈርሳል መባሉን ተከትሎ በሶማሌ ክልል ፊቅ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

በሶማሌ ክልል ኖጎብ ዞን በፊቅ ከተማ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሰልፈኞች ወደ አደባባይ በመውጣት የክልሉን ልዩ ኃይል መልሶ ለማደራጀት የተወሰነውን ውሳኔ ተቃውመዋል።

የሶማሌ ክልል ሚያዝያ 02 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 12ኛው ምክር ቤት ጉባኤ የክልሉን ልዩ ኃይሎች መልሶ ለማደራጀት ያወጣውን ውሳኔ ማፅደቁን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ኡመር በትዊተር ገጻቸው ማስፈራቸው ይታወሳል።

የልዩ ኃይሉ ቤተሰብ አባል ናቸው የተባሉት የፊቅ ከተማ ነዋሪዎች የክልሉ መንግስት የደረሰበት ውሳኔ ህይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ የሚቃወሙት መሆኑን አንዳንድ የሰልፋ ተሳታፊዎች ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።

ናዲያ ፋራ እና ዴቃ ያሲን (ስማቸው ተቀይሯል) የተባሉ ነዋሪዎች ልዩ ኃይሉ መልሶ ሲደራጅ አንድም አባል ከስራ እንደማይሰናበት፣ የደሞዝ መቀነስና እና ከማዕረግ ዝቅ የሚደረግ እንደማይኖር የዞኑ አስተዳደር በመግለፁ ሰልፉ በስምምነት ተበትኗል ብለዋል።

ጉዳዩን አስመልክተን የሶማሌ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮንና የዞኑን አስተዳዳሪዎች በስልክ ለመግኘት ያደረግነው ጥረት የሞባይል ስልካቸው ባለመነሳቱ ልናገኛቸው አልቻልንም፡፡ አዲስ ዘይቤ እንደዘገበው
2.7K views08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 11:47:55
ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋውን የፀጥታ ሀይል ነን ያሉ አፋኝ ሀይሎች ከቤቱ መውሰዳቸውን ወላጅ እናቱ ገልፀዋል።
2.5K views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 11:47:23
የኢትዮ 251 ሚዲያ ስቱዲዮ በፀጥታ ኃይሎች ተከቧል።

አራት ኪሎ "ድንቅ ሥራ ኮምፕሌክስ" ህንጻ ላይ የሚገኘው የኢትዮ 251 ሚዲያ በፀጥታ ኃይሎች ከበባ እንደተፈፀመበት የአይን እማኞች ከቦታው ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጸዋል።

ከበባውን የፈፀሙት የኢትዮጵያ ፌድራል ፖሊስ አባላት እንደሆኑ እና አሁንም ድረስ 8ተኛ ፎቅ ላይ እንደሚገኙ የመረጃ ምንጮቻችን ተናግረዋል።

መጋቢት 10 ቀን 2015 ዓ.ም ኢትዮ 251 ሚዲያ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ሚዲያው ዘረፋ እንደተፈፀመበት ይታወቃል።

ከበባ የተፈፀመበት የኢትዮ 251 ሚዲያ ስቱዲዮ አራት ኪሎ ሚዲያ እና ነገር ወልቃይት ሚዲያ በጋራ የሚጠቀሙበት መሆኑ ይታወቃል።

የነገረ ወልቃይት ሚዲያ የበላይ ኃላፊ ዶ/ር አሰፋ አዳነ በአዲስ አበባ መታሰራቸው ይታወቃል። የአራት ኪሎ ሚዲያ መሥራችና ባለቤት እንዲሁም አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በትላንትናው ዕለት በመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የደህንነት ሰዎች ታፍኖ የት እንደደረሰ ማወቅ አልተቻለም።
2.6K views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 16:54:31
3.5K views13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 16:54:07 የአማራ ወጣት - የማይወይበውን ጀግንነትህን የምታስመሰክርበት ጊዜው አሁን ስለሆነ በየአካባቢህ ተደራጅተህ ከልዩ ኃይሉ ጎን እንዲቆም ባልደራስ ጠየቀ

የአማራ ሚዲያ ማዕከል
ሚያዝያ 04 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

የኦህዴድ/ብልፅግና መንግሥት ህወኃት ሙሉ በሙሉ ከትግራይ ህዝብ ትክሻ ላይ እንዲራገፍ እንደማይፈልግ ከተለያዩ ተግባሮቹ መገንዘብ ተችሏል፡፡ በህወሃት እና በኦህዴድ/ብልፅግና መካከል ያለው ልዩነት የሥልጣን ሽኩቻ እንጅ የፖለቲካ አመለካከት እንዳልሆነ ግልፅ ነው፡፡ ዛሬ የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች የአማራ ህዝብ ቀጣይ ጥቃት እንዲፈፀምበት ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የአማራን ልዩ ኃይል፣ ፋኖን እና ሚሊሻውን ለማፍረስ ቀን ከሌት እየባዘኑ ይገኛሉ፡፡

አማራ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር ሆኖ ሀገሩን በደሙ ያቆመ፣ የሀገርን እና የሕዝብን አንድነት ያስጠበቀ፣ የጀግንነት አኩሪ ታሪክ ያለው ሕዝብ ነው፡፡ ዳሩ ግን ያለፉት ሰላሳ ሁለት ዓመታት ለአማራ ህዝብ የህማማት ጊዜያት ሆነውበታል፡፡ በጽንፈኛ አክራሪዎች ታርዷል፤ ቤትና ንብረቱ ወድመውበታል፤ ከቀየው ተፈናቅሏል፤ ከኢኮኖሚ ባለቤትነትና ከፖለቲካ ሥልጣን ተገልሏል፡፡ ከመኖሪያው ተፈናቅሎ በተለያዩ ሥፈራዎች የተበተነውም የሚመገበው፣ የሚለብሰውና የሚያድርበት ተቸግሮ በስቃይ ላይ ይገኛል፡፡ ሰሞኑንም በንፁሀን ህይወት ላይ በሚቆምሩ ፖለቲከኞች ምክንያት የአማራን ህዝብ ትጥቅ አስፈታለሁ በማለት ሀገሪቱን መውጫ ወደሌለው መቀመቅ እያስገቧት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡

የኢትዮጵያን አንድነት የሚያናጋው የጎሳ ፖለቲካ፣ ህገ መንግስቱ እና የክልሎች አከላለል ባልተቀየረበት ሁኔታ ልዩ ኃይሉን ማፍረስ ከቃላት በዘለለ ወንድማማችነትን ሊያስገኝ እንደማይችል ግልጽ ነው፡፡ ‹‹የሌሎች ክልሎች ልዩ ኃይሎች ሳይፈርሱ የአማራን ልዩ ኃይል ብቻ መርጦ ማፍረስ የአማራን ሕዝብ ለጥቃት ማጋለጥ ነው›› በማለት በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞውን ለማሰማት ወደአደባባይ የወጣውን ኗሪ ክቡር ህይወት መቅጠፍ በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር ነው፡፡ ይህ ድርጊት የፖለቲካውን መስመር ወደ መራራ ትግል ይመራዋል እንጅ አያስቆመውም፡፡ ዜጎችንም ማሰር ትግሉን አያዳክመውም፡፡ የልዩ ኃይሉን ደመወዝ እና ምግብ ማቋረጥም ትግሉን አይጎትተውም፡፡

ስለዚህ፡-
➢መላው የአማራ ህዝብ - ከብልፅግና የፋሽስት አገዛዝ ነፃ እስክትወጣ ድረስ መከታ የሆነህን ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚሊሺያ በምግብ አቅርቦት እንድትደግፍ፣

➢መላው የአማራ ህዝብ የንግዱ ማህበረሰብ - በክብር እና በሰላም እንድትኖር የታደገህን እና አሁንም እየታደገህ ያለውን ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻ እንዳይራብ ድጋፍ እንድታደርግ፣

የመከላከያ ሰራዊት - ሰሜን ዕዝ ሲጨፈጨፍ እና ሲኖ ትራክ በጭንቅላቱ ላይ ሲነዳበት እና በግፍ ሲታረድ ከጎንህ በቆመው የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ፣ ሚሊሻ እና ህዝብ ላይ ቃታህን እንዳትስብ፣

➢አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን - የጥቁር ህዝብ ህይወት ግድ ይለኛል /Black lives matter/ የሚለው ማህበራዊ ንቀናቄ በጥቁሮች ላይ የሚፈፀመውን አድልዎ የሚቃወም ንቅናቄ ሲሆን፣ በዚህ ንቅናቄ ላይ ከጥቁሮች በተጨማ ነጮችም ተሳታፊዎች እንደነበሩ የዓለም ታሪክ ያስረዳል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታም በአማራ ላይ ሲደርስበት የነበረውን እና እየደረሰበት ያለውን የዘር ማጥፋትና ማፅዳት፣ አድልኦ እና ጭቆና በመቃወም የአማራ ሕዝብ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንድትቀላቀሉ፣

➢የአማራ ወጣት - የማይወይበውን ጀግንነትህን የምታስመሰክርበት ጊዜው አሁን ስለሆነ በየአካባቢህ ተደራጅተህ ከልዩ ኃይሉ ጎን እንድትቆም፣

➢የአማራ ህዝብ እና የሀገሬ ጉዳይ ግድ ይለኛል የምትሉ ሌሎች ኢትዮጵያውያን - ሃገርን ከመበታተን የማዳን ትግሉን ተቀላቅላችሁ ይህን ዘረኛ ሥርዓት በመገርሰስ ሂደት የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታበረክቱ የአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ
3.5K views13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 16:53:22
3.0K views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 16:47:58 ከአማራ ህዝባዊ ሰራዊት በጎንደር የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ሚዲያ ማዕከል
ሚያዝያ 04 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ ከህወሓት በቀጠለው ስርዓት በርዕዮተ-ዓለም በተደገፈ መልኩ ጥቃት እየደረሰበት መሆኑ ይታወቃል። ጠላቶቻችን ጥቃቱን አጠናክረው ለመቀጠልና ህዝባችን አንገቱን ደፍቶ እንዲኖር ለማድረግ ከሰሞኑ የመጨረሻ መጀመሪያ የሆነውን ተልዕኮ ጀምረዋል። ይኸውም በአማራ ልዩ ኃይልና በፋኖ ላይ ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻ በማድረግ ንፁሐንን ሳይቀር እየጨፈጨፉ ይገኛሉ።

ስለሆነም ከምንግዜውም በበለጠ መላው አማራ ተጋድሎውን መቀላቀሉን የምንገነዘብ ቢሆንም በሁሉም የአማራ ምድር እኩል ባልሆነ መንገድ መጓዝና ተናቦ አለመሄድ የትግሉን እድሜ የማርዘም እድል ይኖረዋል። በተጨማሪም የትግሉን ስልቶች መጠነ ሰፊ ማድረግና ከአካባቢያዊነት ወጥቶ ለሁሉም ፈጥኖ ደራሽ እንዲሆን ማድረግ የደረሰበት የእድገት ደረጃ የሚጠይቀው ጉዳይ ሆኖ ተገንቷል። በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች አሁን መሬት ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ፍሬ እንዲያፈራ አድርጎ መምራት አስፈላጊ በመሆኑና በአንፃራዊነት ጎንደር አካባቢ የደከመ የመሰለውን ህዝባዊ ንቅናቄ ለማጎልበት እንዲሁም ከጎጃም፣ ከወሎና ከሸዋ ጋር ተቀናጅቶ እኩል ለመራመድ እንዲያስችል፤ ከልዩ ኃይሎች፣ ከማህበራት፣ ከወጣቶች፣ ከፋኖዎች፣ ከሙህራን፣ ከሐይማኖት አባቶችና ከማህበረሰብ እንቂዎች የተውጣጣ ኮሚቴ ሚያዚያ 01/2015 ዓ.ም በጎንደር ከተማ መቋቋሙ ይታወቃል።

ይህ 41 አባላት ያሉት ቡድን በዋናነት ህቡዕ የትግል ስልትን የሚከተል ቢሆንም በ2008 እና 2009 ዓ.ም በጎንደር ሲደረግ የነበረውን ተጋድሎ በመድገም አካባቢውን ከአገዛዙ ነፃ ማውጣትን ያለመ ነው። ስለሆነም ኮሚቴው በትናንትናው እለት ጎንደር ከተማ ያስተላለፈውን የሰዎችን እንቅስቃሴ የመገደብና ሰዓት እላፊ ክልከላ ሙሉ በሙሉ እንደማይቀበለው በመወሰን 'የአምባገነኖች ክልከላ' በማለት ከመፈረጁም ባሻገር ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎችን ይፋ አድርጓል።

ከዛሬ ሚያዝያ 04/2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 13/2015 ዓ.ም ለአስር ቀናት በጎንደር ከተማና አካባቢው የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ እናስተላልፋለን። ይህን አድማ ኮማንድ ፖስት በሚል አጉል ክልከላ ለማደናቀፍ በሚሞክሩና በሚያደናቅፉ ግለሰቦች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የአማራ ህዝባዊ ሰራዊት በጎንደር ያስጠነቅቃል። የትግሉን አቅጣጫ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ብያኔ ለማበጀት፤ ከሌሎች አካባቢ የአማራ ህዝባዊ ሰራዊት መሪዎች ጋር በመነጋገር ቀጣይ አቅጣጫዎች እያስቀመጠ እንደሚቀጥል ጨምሮ ይገልፃል።
አማራነት ያሸንፋል!
ከአማራ ህዝባዊ ሰራዊት በጎንደር አስተባባሪ ኮሚቴ
ሚያዝያ 04/2015 ዓ.ም
3.4K views13:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ