Get Mystery Box with random crypto!

2. የውያኔ ወራሪ ኃይል ትጥቅ ባለፈታበትና አማራው መልሶ በመስዋእትነቱ ያስከበራቸውን አፅም እርስ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

2. የውያኔ ወራሪ ኃይል ትጥቅ ባለፈታበትና አማራው መልሶ በመስዋእትነቱ ያስከበራቸውን አፅም እርስቶቹን ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጸለምትና ራያን በምእራብውያን ተፅእኖ መልሶ ለመቆጣጠር ጥረት በሚያደርግበት በአሁኑ ግዜ፤ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና የአማራ ሚሊሺያ በአማራው ህዝባዊ እምቢተኛነት እየታገዘ በተጠንቀቅ በመቆም የአብይ አህመድን
ትጥቅ የማስፈታትና የአማራን ህልወና የመግሰስ ዘመቻ ሊያኮላሹ ይገባል። አገር እያፈረስ ያለውን አገዛዝ በህዝባዊ እምቢተኝነት የታገዘ ትግል ለማድረግ የተጠናከሩ አደረጃጀቶችና መሪዎችን በመፍጠር፤ የችግሩን ምንጭ ከአራት ኪሎ ማስወገድ ካልተቻለ የአማራ ህዝብ በታሪኩ ያላየውና ያልደረስበት ግፍና መከራ ከፊታችን እንደተጋረጠ በመገንዘብ
ህዝባዊ ትግሉን በስፋትና በጥልቀት በማሳደግ እንድታቀጣጠሉ ጋሻ የአማራ ድርጅት አስቸካይ ጥሪ ያቀርባል።

3. በኢትዬጵያ ውስጥ የምትንቀሳቀሱ የፓለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የወጣት አደረጃጀቶች፣ የሙያ ማህበራት፣የሴቶችና የእናቶች አደረጃጀቶች፣ የዩኒቨርስት ተማሪዎችና አስተማሪዎች፣ የነጋዴ ማህበራቶች በአጠቃላይ በመላው ሀገሪቱ የተደራጃችሁ አደረጃጀቶች በሙሉ፤ ይህንን አገር አፍራሽ፣ ህዝብ ገዳይና ጨፍጫፊ የኦህዴድ የብልፅግና መንግስት መግለጫ በማውጣት ብቻ የማናስወግደው መሆኑን ተገንዘበን የመረረ ህዝባዊ ትግል በማድረግ አገርን ከማፍረስ ህዝብን ከመፍለስ እንድትታደጉ አስቸኳይ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

4. በመጭረሻም የአማራ የትግል አብሪ የሆነውን እርበኛ ዘመነ ካሴንና ሌሎች ለአማራው ህዝባችንና ለኢትዮጵያ የተዋደቁ ጀግኖቻችንን ከማክበርና ከመሽለም ይልቅ በማዋረድና አንገት በማስደፈት እስር ቤት የተወረወሩ ወገኖቻችንን በመንግስት ልምምጥና ልመና ሳይሆን ህዝቡ በራሱ ትግል እንዲይልስፈታቸው የመጨረሻ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

አማራው በረዥሙ ያሽንፋል!!!
ጋሻ የአማራ ድርጅት