Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ልዩ ኃይልን ማፍረስ፣ አማራን በከበባ የማጥፋት የአብይ/ኦሮሚማ ሴራ ነው! ከጋሻ የአማራ ድ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

የአማራ ልዩ ኃይልን ማፍረስ፣ አማራን በከበባ የማጥፋት የአብይ/ኦሮሚማ ሴራ ነው!
ከጋሻ የአማራ ድርጅት የአቋም መግለጫ

የአማራ ሚዲያ ማዕከል
ሚያዚያ 5 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የአማራ ህዝብ ላለፈው 27 አመት በዘረኛው የህዋት የመንግስት ዘመን ሲገደል ሲታስር ሲፈናቀል የኖረ ማህበረስብ ሲሆን በወልቃይትና በጉራ ፈርዳ፣ በወተር፣ በበደኖ፣ በአርባ ጉጉ፣ በሐረር፣ በአሩሲና አሁን ደግሞ በቅርቡ በማይካድራ የዘር ማጥፍት ወንጀል የተፈጸመበት ሲሆን ባለፉት 5 አመታት ደግሞ በጨፍጫፊውና በገዳዩ በአብይ መንግስት ስር በተቃቃሙ የገዳይ
ቡዱኖች በኦነግ፣ ኦነግ ሽኔና በኦሮሞ ልዩ ሃይል በቤንሻንጉል፣ ጉምዝ በወለጋ አራቱም ዞኖች፤ በአጣዬ ከአስራ አንድ ግዜ በላይ ግድያና ጭፍጨፍ በመፈፅም በጅምላ በመቅበር በአማራ ህዝብ ላይ ከፍተኛ የዘር ማጥፍት ወንጀል የፈጸሙ ሲሆን እስካሁን ድረስ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የአማራ ተወላጆችን ከወለጋ፣ ከቤንሻንጉል፣ ከአጣዬና ከአዲስ አበባ ዙሪያ በማፈናቀል ከዘር ማጥፍት፣ ግድያና ጭፍጨፍ የተረፈው ደግሞ በረሃብ፣ በእርዛትና በበሽታ እንዲያልቅ በአማራ ህዝብ ላይ አብይ የሚመራው የኦህዴዱ-ብልፅግናው/የኦሮሙማ መንግስት ከፍተኛ ወንጀል ፈፅሟል።

ባለፍት ሁለት አመታት ደግሞ ትግራይ ውስጥ የነበረውን ጦርነት በአሻጥር ወደ አማራ ክልል መልሶ በማምጣት የአማራ ህዝብ የኢኮነሚ ተቋማት፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ ሆስፒታሎች፣ ትህምርት ቤቶች፣ መንገዶች፣ የንግድና የኢንቨስትመንት ተቋሞች እንዲወድሙ በማድረግ የአማራን ክልል ኢኮኖሚ አርባ አመታት ወደ ሃላ የመለሰ ሲሆን በገንዘብም ከ40 ቢሊዮን ብር በላይ በክልሉ ላይ ኪሳራ እንዲደርስ አድርጓል ።

በጦርነቱም ወቅት በህዝብ ከተስበስበ ግብርና ቀረጥ ደመወዝ የሚከፈለው የመከላከያው ስራዊት ሆን ተብሎ እንዲሽሽ በማድረግ የአማራ ገበሬዎችና ወጣቶች በከፍተኛ ቁጥር የተገደሉ ሲሆን እናቶችና ህፃናት በወራሪው ሃይል እንዲደፈሩ አድርጓል።

የመከላከያው ጦሩ በዚህ መልኩ ህዝቡን ለህዋት ወራሪዎች ለአደጋ እያጋለጠ በሚሽሽብት ግዜ የአማራው የቁርጥ ቀን ልጆች የሆኑት የአማራ ልዩ ሃይልና፣ፋኖ እንዲሁም ሚሊሺያ በከፈሉት የላቀ መስዋእትነት የወራሪው የህዋት ኃይል ተሽንፈው ከአማራ ክልል እንዲወጡ ተደርጋል።

ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ ይህንን የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች የሆኑትን የአማራ ልዩ ኃይል ጨካኙ የአብይ መንግስት ያለምንም ምክንያት ወይም አሳማኝ ነገር በሌለበት የአማራን ክልል ለማፈረራስ የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ማስፈታት አለብን ብሎ የአብይ ኦሆዲድ ብልፅግና ፓርቲ በወስነው መስረት ዛሬ ላይ የመከላከያ ልብስ የለበሱ የኦሮሞ ልዩ ኃይሎችን በገፍ በማስገባት የአማራ ወጣቶችን፣ የአማራ ፍኖዎችንና ልዩ ኃይሎችን እየገደሉ ሲሆን ለተቃውሞ የወጣውን የአማራ ህዝብ ግንባሩ ላይ እየተኮሱ ገድለዋል። ምንም እንኳን የክልል ኃይል የሚባል አደረጃጀት አሁን ባለው አማራን ባገለለው ሕገመንግስት ውስጥ ባይካተትም
የአማራን ልዩ ኃይል በዚህ ወቅትና ስዓት ለማፍረስ መወስኑ ከላይ እንደጠቀስነው ወቅቱን ያላገናዘበና ሆን ተብሎ አማራውን ያለጠባቂ ለማስቀረት የተወስነ ውሳኔ ነው። የውሳኔውም ዋና አላማ በእብሪተኝነት አብይ የሚከተለው የዘረኝነት ፓሊሲ ሁሉንም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኃይሎችን ተራ በተራ በመደፍጠጥ እሱ የሚመራው የኦህዲድ ብልጽግና ፓርቲ በጥናት እያራመዱ ያለውን ኢትዮጵያን የማፈራረስ እንቅስቅሴ እቅድ ለማስፈፅም የሚቻለው ያስጉኛል የሚላቸውን ኃይሎች በማጥፍት ኦሮሙማና በኢትዮጵያ መቃብር ላይ ለመመስረት እንደሆነ ለሁልም ግልፅ ነው።

በሌላ በኩል በህዋትና በብልፅግና መካከል ፕሪቶርያ ላይ ተደረገው በተባለ ሚስጥራዊ ስምምነት መሰረት ህወሀት ትጥቅ መፍታት ሲገባው ይህ ሙሉ በሙሉ ተጥሶ ባለበት፤ እንዲያም ህወሀት ለተጭማሪ ወረራ እየተዘጋጀ ባለበት፣ ሌሎች ክልሎች ትጥቅ ባልፈቱበት ሁኔታ የአማራ ልዩ ኃይልን ብቻ አፋጥኖ በተናጠል ትጥቅ ማስፈታት ፈፅሞ የማይቻል መሆኑን የብልፅግና አገዛዝ
ሊገነዝበው ይገባል። በተቃራኒው ደግሞ የኦሮሞ ልዩ ኃይል ቱርክ ሰራሽ መሳሪያዎችን በመንግስት ወጪ እንዲታጠቁ መደረጉ የብልፅግናን የተስፉፊነት ፓሊስ በግልፅ የሚያሳይ ሲሆን አሁንም የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ለማስፈታት እነዚህኑ ኃይሎች ወደ
አማራ ክልል በመከላከያ ዩኒፎርም ሽፋን ማስገባቱ በከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ መልስ ሊሰጠው ይገባል ብሎ ድርጅታችን ያምናል።

በአጠቃላይ የብልጽግና አገዛዝ በኦሮሚማ ሙሉ ቁጥጥር ያለው የመከላከያ ኃይል፣ አብይ በሚያወርደው የሃገር ማፍረስ ትእዛዝ መሰረት የሀገሪቱ ሉአላዊንት ተደፍሮ በጎንደር ለሱዳን የተስጠው መሬታችን በተያዘበት፤ በደቡብ ሱዳን የጋምቤላ መሬት ሆነ ተብሎ እንዲወረር በተደረገበት ወቅት፤ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለመውረር ምቹ ግዜ አግኝተናል እያሉ ከበባበሚፈፅሙበት ስአት፤ በብዙ አቅጣጫ የተከበበው እና መዋከብ የበዛበት አማራው ወገናችን ህልውናው ከፍተኛ አደጋ ውስጥ እያለ፣ መላው ህዝብ ከአማራው ልዩ ኃይልና ከፍኖዎች ጎን ቆሞ የኦሆዲድ ብልፅግናን ወረራ ብቻ ሳይሆን በሱዳን በኩል ሊቃጣብን የሚችለውን የሐይማኖትና ባህል የማጥፍት ጦርነት መቋቋም ብቻ ሳይሆን ማሸነፍ እንዲቻል በህዝባዊ እንቢተኝነትና ጽናት ድጋፍ እንዲአደርግ ድርጅታችን በፅኑ ያስገነዝባል።

የአማራ ህዝብ በአሁኑ ስአት መሪ የሌለው ሲሆን መሪ ነን ባዮች የቀድሞ የብአዴን፣ የአሁኑ የአማራ ብልፅግና አመራሮች ህዝባችንን ላለፈው 32 አመት እጅና እግሩን አስረው እያሳረዱትና እያስጨፈጨፉት፤ የራሱ በተባለለት ክልል ውስጥ እንኳን ተሳዳጅ ሲሆን በአዲስ አበባና በየክልሉ ቤታቸው ፈርሶ፣ ሃብታቸው ተነጥቆ፣ በየመንገዱ የወደቁትን የአማራ ወገኖቻችን
በደብረ ብርሀን የመጠለያ ካምፕ ምግብ የሚስጣቸው አጥተው በችጋር ሲረግፍ እያየ እንዳላየ የሚያልፍና የክልሉን ህዝብ ለኦሆዲድ ብልፅግናና ለትህነግ ጣምራ ወራሪዎች አሳልፈው ሰጥተውታል። በመሆኑም በክልሉ ወስጥና ከክልሉ ወጭ የሚኖረው አማራ ወገናችን በባርነት ቀንበር ውስጥ እንዲወድቅ እየስሩ ያሉ የአማራ ክልል ባለስልጣኖችን ህዝባችን አንድ በአንድ ነጥሎ በህዝባዊ አመፅና ሁለ ገብ ትግል ካላስወገዳቸው በስተቀር የአማራው ህዝባችን መብቱ ተረግጦና ተዋርዶ ለቀጣዩ መጪ ዘመናት በባርነት ቀንበር ውስጥ መውደቁ የማይታበል ሃቅ ነው።

ስለዚህ ቀጣይ የእማራነትን የዘር ማጥፍትን እና የባርነት ቀንበር ከጫንቃው ላይ አሽቀንጥሮ ለመጣል የሚከተሉትን ነጥቦች ማስቀመጥ እንወዳለን፣-

1. የእገር መከላከያ ስራዊት የአገርን ዳር ድንበርና የህዝቡን የኑሮ ዋስትና ማረጋገጥ እንጂ በህዝቦች መካከል ጣልቃ ገብቶ የአብይን ትእዛዝ ለመፈፅም የሚያደርገውን ህገወጥ ግድያ በአስቸካይ እንዲያቆምና አሁኑኑ አንዳንድ የደቡብ፣ የጋምቤላና የአማራ የመከላከያ ወታደሮች የአማራ ወገናችንና በህዝባችን ላይ አንተኩስም ያሉትን ፍትሃዊ የሆነ የህሊና ሚዛን
ያለውን ውሳኔያቸውን በመከተል ሌሎች የመከላከያ ስራዊት አባላት ህዝባችንን መግደል አቁማችሁ በአስቸካይ ከክልሉ እንድትወጡ አስቸኳይ ጥሪያችንን እናቀርባለን።