Get Mystery Box with random crypto!

ልዩ ኃይል ይፈርሳል መባሉን ተከትሎ በሶማሌ ክልል ፊቅ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ በሶማሌ ክል | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

ልዩ ኃይል ይፈርሳል መባሉን ተከትሎ በሶማሌ ክልል ፊቅ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

በሶማሌ ክልል ኖጎብ ዞን በፊቅ ከተማ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሰልፈኞች ወደ አደባባይ በመውጣት የክልሉን ልዩ ኃይል መልሶ ለማደራጀት የተወሰነውን ውሳኔ ተቃውመዋል።

የሶማሌ ክልል ሚያዝያ 02 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 12ኛው ምክር ቤት ጉባኤ የክልሉን ልዩ ኃይሎች መልሶ ለማደራጀት ያወጣውን ውሳኔ ማፅደቁን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ኡመር በትዊተር ገጻቸው ማስፈራቸው ይታወሳል።

የልዩ ኃይሉ ቤተሰብ አባል ናቸው የተባሉት የፊቅ ከተማ ነዋሪዎች የክልሉ መንግስት የደረሰበት ውሳኔ ህይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ የሚቃወሙት መሆኑን አንዳንድ የሰልፋ ተሳታፊዎች ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።

ናዲያ ፋራ እና ዴቃ ያሲን (ስማቸው ተቀይሯል) የተባሉ ነዋሪዎች ልዩ ኃይሉ መልሶ ሲደራጅ አንድም አባል ከስራ እንደማይሰናበት፣ የደሞዝ መቀነስና እና ከማዕረግ ዝቅ የሚደረግ እንደማይኖር የዞኑ አስተዳደር በመግለፁ ሰልፉ በስምምነት ተበትኗል ብለዋል።

ጉዳዩን አስመልክተን የሶማሌ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮንና የዞኑን አስተዳዳሪዎች በስልክ ለመግኘት ያደረግነው ጥረት የሞባይል ስልካቸው ባለመነሳቱ ልናገኛቸው አልቻልንም፡፡ አዲስ ዘይቤ እንደዘገበው