Get Mystery Box with random crypto!

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_media_center — አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center
የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_media_center — አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center
የሰርጥ አድራሻ: @amhara_media_center
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.55K

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-04-09 10:36:50 በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ፣

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው የአቋም መግለጫ የገዥው ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የክልል ልዩ ኃይሎችን ለማፍረስ ያሳለፈው ውሳኔ በሁሉም ክልሎች ልዩ ኃይሎች ላይ በእኩል ደረጃ ተፈጻሚ የማይሆን እና የውሳኔው ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ማስፈታት መሆኑን በመገምገም ፣ መንግስት የአማራ ልዩ ኃይልን ለማፍረስ ያሳለፈው ውሳኔ ወቅቱን ያልጠበቀ ፣ ነባራዊ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ ያላስገባ እና ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ የአማራ አካባቢዎችን እና የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተገማች እና ቀጥተኛ ለሆነ ጥቃት እና አደጋ የሚዳርግ አደገኛ ውሳኔ መሆኑን በመግለጽ ውሳኔው ተፈጻሚ እንዳይሆን ማሳሳቡ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ድርጅታችን አብን ያቀረበውን ማሳሳቢያ ወደ ጎን በማለት የፌዴራሉ መንግስት የክልሉን ልዩ ሃይል ትጥቅ ለማስፈታት በመንቀሳቀሱ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በክልሉ ልዩ ኃይል እና በፌዴራል የጸጥታ ተቋማት መካከል ከፍተኛ ውጥረት እንዲፈጠር ምክንያት ሁኗል፡፡

ውጥረቱን ተከትሎ ድርጅታችን መጋቢት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ያለ በቂ ዝግጅት ፣ ውይይት ፣ የጋራ መግባባት እና መተማመን በድንገት እና ያለበቂ የጸጥታ ዋስትና የፌዴራል መንግስት የክልሉን ልዩ ኃይል ለማፍረስ ያሳለፈው ውሳኔ እና ውሳኔውን ለማስፈጸም እየሄደበት ያለው መንገድ ሃላፊነት የጎደለው እና ዳፋው በአማራ ክልል ብቻ ሳይወሰን በሃገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አለመረጋጋት የሚፈጥር ፣ ክልሉን እና ሀገራችን ኢትዮጵያን ወደ ሌላ የቀውስ አዙሪት የሚከት አደገኛ አካሄድ መሆኑን በማስጠንቀቅ ፣ የፌዴራሉ መንግስት ውሳኔውን በአፋጣኝ እንዲቀለብስ እና ከአማራ ክልል መንግስት እና ከክልሉ ሕዝብ ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት እና ምክክር እንዲደረግ እና የክልሉን እና የሀገራችንን ዘላቂ ሰላም በሚያረጋግጥ መልኩ ውሳኔው እንዲከለስ ፣ የልዩ ኃይሉ ቀጣይ እጣ ፈንታ ከአማራ ሕዝብ፣ ከክልሉ ልዩ ኃይል አመራሮች እና ከመላው የሠራዊቱ አባላት ጋር በሚደረግ ውይይት እና የጋራ መግባባት ብቻ ውሳኔ ላይ እንዲደረስበት ማሳሳባችን ይታወቃል፡፡

ይሁንና የፌዴራሉ መንግስት ከሕግ አግባብ ውጭ የገዥው ፓርቲን ውሳኔ ለማስፈጸም የገፋበት በመሆኑ ፣ በአማራ ክልል በርካታ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ ሕዝባዊ ቁጣ ቀስቅሷል፡፡ ድርጅታችን አብን እስካሁን ድረስ ለሀገራዊ አንድነት እና ሰላም ሲባል ጉዳዩን በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ሲከታተል ቆይቷል። ይሁንና መንግስት ችግሩን በሰከነ መንገድ ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ ከዕለት ወደ ዕለት የለየለት የኃይል ፣ የአፈና እና የማደናገር አማራጭ እየገባ መሆኑን ፖርቲያችን ተረድቷል። መንግስት ችግሩን በሰከነ መንገድ ፣ በውይይት ፣ በጋራ መግባባት እና በመተማመን የመፍታት ኃላፊነት ያለበት ቢሆንም በስህተት ላይ ሌላ ስህተት እየደረበ እና ችግሩን በአፈና እና በጉልበት ለመፍታት ቆርጦ የተነሳ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ፖርቲያችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ከዛሬ ጀምሮ ለችግሩ ዘላቂ እልባት እስከሚሰጥ ድረስ መንግስት እና ግብረ-አበሮቹ በአማራ ልዩ ኃይል ፣ በፋኖ እና በአጠቃላይ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚነዟቸውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳዎች በይፋና በተከታታይ የሚያጋልጥ መሆኑን ለማሳወቅ ይወዳል።

የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እና ፋኖ የሀገር እና የሕዝብ የሰላም ዘብና ዋስትና እንጂ የፀጥታ ስጋት ምንጭ ሆነው አያውቁም። ሀገር የማዳን ተልዕኮዎችን በከፍተኛ ብቃት የፈጸሙ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አስተማማኝ ጋሻ እና ደጀን ሆነውና ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍለው ሀገር የመታደግ ጉልኅ ታሪክ የሰሩ የሀገር መከታዎች ናቸው፡፡ ለዚህ መላው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አመራሮችና አባላት ህያው ምስክሮች ናቸው። መላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንም በክብር የሚያወሱት ወገናዊ የታሪክ ሃቅ ነው። ይሁንና የፌዴራሉ መንግስት ለልዩ ኃይሉ ክብር እና ውለታ በማይመጥን እና ፍጹም ክብረ-ነክ በሆነ ሁኔታ የልዩ ኃይሉን አመራር ከሠራዊቱ በመነጠል እና ስንቅ ፣ ሎጂስቲክ እና ደሞዝ በመከልከል ጭምር ልዩ ኃይሉን ለመበተን ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህም የክልሉ መንግስት የሚቆጣጠረውን እና የሚመራውን ኃይል በመበተን ፣ በእዝ የማይመራ እና መንግስት የማይቆጣጠረውን ኃይል ለመፍጠር እና ክልሉን ወደ ቀውስ እና ትርምስ ለመውሰድ የሚደረግ ጥረት ሆኖ የሚቆጠር ነው፡፡

የአማራ ሕዝብ ከመላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበርና ከፍተኛ መስዋዕትነት በመክፈል የትሕነግ-ኢሕአዴግን አገዛዝ ከስልጣን አስወግዶ ያመጣውን ለውጥ ለሀገራዊ አንድነት ፣ ነፃነት ፣ ፍትኅ እና ለዴሞክራሲ ገቢራዊ ቀናኢነት በሌላቸው የፖለቲካ እጆች ተነጥቋል። በዚህ ምክንያት ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ወደማያባራ የነውጥ እና የግጭት፣ የአፈና እና የዘር ፍጂት ምዕራፍ እየተሸጋገሩ ይገኛሉ። መንግስት ዝቅተኛ የሆነውን ለሕይወት እና ንብረት ከለላ የመስጠት ግዴታውን ለመወጣት አቅም ወይም ፍላጎት እንደሌለው ከበቂ በላይ ማሳያዎች ተከስተዋል። በተለይም የአማራ ሕዝብ ከየትኛውም ዘመን በላይ ሰላሙን ፣ ሕይወቱን፣ ማንነቱን እና ንብረቱን በገፍና በይፋ እየተነጠቀ ያለበት ወቅት ነው። ሕዝባችን ይሄን ዘግናኝ ግፍ እና መስዋእትነት ተሸክሞ የቀጠለው ምናልባት ወደፊት እውነተኛ ፍትኅ ፣ እኩልነት እና ዴሞክራሲ የሰፈነበት ሥርአት ይፈጠራል የሚል ተስፋ ሰንቆ ነበር።

ድርጅታችን አብን መዋቅራዊ እና ሕገ-መንግስታዊ ሽግግር እንዲደረግ እና በሥራ ላይ ያለው ሃሳዊ የፌዴራል አወቃቀር በእውነተኛ ፌዴራላዊ የአስተዳደር ሥርአት እንዲተካ እና የሀገራችን አንድነት እና ሉአላዊነት ፣ የዜጎች እና የሕዝብ መብትና ነፃነት እንዲከበር ለማስቻል የበኩሉን ኃላፊነት ለመወጣት ያለመታከት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ነገር ግን ይህ ተስፋና ግምት በየቅጣጫው እና በየደረጃው ተሸርሽሮ በአሁኑ ሰዓት የመጨረሻው ዝቅታ (rock bottom) ላይ የደረሰ መሆኑ አይካድም።

ሀገራዊ በጎ ቱርፋት ያጎናፅፋል የተባለለት "የለውጥ ምዕራፍ" ሰቆቃና ስጋት የነገሰበት ሆኗል። የኢትዮጵያን ሕዝብ ከጥላቻ አዙሪት በማስወጣት በነፃነትና በእኩልነት ለማስተዳደር በአደባባይ ቃል ገብተው የነበሩ "የለውጥ አመራሮችም" የዘር አንጓዎችን ተከትለው ከነጎዱ ሰንብተዋል። የአማራ ሕዝብም ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (ትሕነግ) እያለ የሚጠራው ቡድን በከፈተበት መጠነ ሰፊ ባለ ሶስት ዙር የወረራ ጦርነት ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ደርሶበታል። በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች የሚኖረው የአማራ ሕዝብ ተደጋጋሚ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማፅዳት ወንጀሎች ተፈፅመውበታል ፤ አሁንም ቢሆን በከፍተኛ የደኅንነት ስጋት ውስጥ ይገኛል። እነዚህ መጠነ-ሰፊ እና ተደጋጋሚ የሆኑ የዘር ጥቃቶች በዋናነት የሚፈፀሙት በሽብር ኃይሎች ቢሆንም በመንግስታዊው መዋቅር እና ባለስልጣናት ቸልተኝነት ፣ ይሁንታ ፣ ፈቃድ እና እገዛ ጭምር እንደሚፈፀሙ በግልፅ ይታወቃል።
2.7K views07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 19:53:48 https://www.youtube.com/live/7xUbqq2ULwg?feature=share
1.7K views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 18:54:55
ህዝባዊ እንቢተኝነት በደብረ ማርቆስ ቀጥሏል።
2.0K views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 16:14:32
ህዝባዊ እንቢተኝነት በአማራ የተለያዩ ክፍሎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።
#ጎንደር
2.4K views13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 15:21:04
ሉማም አዋበል እየተደረገ የሚገኝ ህዝባዊ እምቢተኝነት
መጋቢት 30 2015 ዓ/ም
2.5K views12:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 15:20:13
2.4K views12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 15:20:05 ጋዜጠኛዋን አፍነው የውሰዷት ለቀዋታል።
የአማራ ሚዲያ ማዕከል
መጋቢት 30 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ

ፀሀፊ ይትባረክ ዋለልኝ

ሰኞ ዕለት ለም ሆቴል አካባቢ ለስራ ስትንቀሳቀስ በደህንነት ሰዎች ታገተች።

". . 2 ወጠምሾች ከግራና ከቀኝ እጄን ያዙኝ። አንደኛው ኮቱን ገለጥ አድርጎ የታጠቀውን ሽጉጥ አሳየኝ። "እኛ ነን እወቂን እንደማለት" . . . በአቅራቢያቸው በነበረ ቪ8 መኪና ውስጥ አስገቡኝ። በሜክሲኮ፣ ሳር ቤት አድርገው ወደ ለቡ ወሰዱኝ። የጸጥታ ተቋም በማይመስል ሰፊ የመኖሪያ ግቢ ውስጥ አስገቡኝ።

እዛ ግቢ፣ እዚያ ቤት ውስጥ እንደኔ በደህንነት የተጠለፉ በርካታ ሰዎች አሉ። በተመሳሳይ ጉዳይ፣ በአንድ ዐይነት የደህንነት ሰዎች ታፍነው የመጡ ናቸው። በሹክሹክታ ማውራት ይቻላል። ስልካችን በእጃችን ነው ግን ደውሎ ለማውራት ድፍረቱ የለንም። ሰው ከደወለልን አንስተን ማናገር እንችለን። ግን ስልኩን ስናናግር ምንም እንዳልተፈጠረ ሰላም እንደሆንን አድርገን እንድናወራ እንገደዳለን። እኔም አንድ ሶስት ስልክ ተደውሎልኝ ልክ እንደሌላው ጊዜ በፈገግታ ለማውራት ሞከርኩ። ፈገግታው ግን ከልብ የመነጨ ስላልሆነና ድራማ ስለነበር ረጅም ሰዓት በዛ ሁኔታ ለማውራት አልቻልኩም። በዚህ የተነሳ የሚደወሉልኝ አንዳንድ ስልኮችን አላነሳም ነበር።

በቤቱ ውስጥ ዓይናችን እያየ እኛ ፊት የሚደበደቡ ሰዎች አሉ። በተለይ አንዷ አራስ ነች። በብሔሯ ምክንያት እንዳመጣት ጮሃ ትናገራለች። "በአማራነቴ ነው. . . አማራ በመሆኔ ነው ሌላ ጥፋት የለብኝም" እያለች ትጮሃለች። ሴቶቹ ፖሊሶች ጸጉሯን ይዘው ከግድግዳው ጋር ያጋጯታል። ምንም ርህራሄ የላቸውም።

በቤቱ ምግብ የለም። በሶስት ቀን ቆይታዬ ምንም ምግብ አልበላሁም። ሌሎቹም እስረኞች እንደኔው ናቸው። እዛ ቤት እዛ ግቢ ምግብ አላየሁም። አንድ ነገር ብቻ ይፈቀዳል። እሱም ሽንት ቤት መጠቀም ብቻ። ሴት ፖሊስ አለች ትመጣና"ሽንቱ የመጣ፣ ሽንቱ የመጣ ይውጣ" ትላለች። ሁላችንም ላይ መደናገጥና የፍርሃት ስሜት ስላለ ሽንቱም ከሰላማችን ጋር አብሮ ጠፍቷል። ደግሞስ ምን ተበልቶ ምን ተጠጥቶ ሊሸና።

በማግስቱ ማለትም ማክሰኞ ዕለት ምርመራ ተብዬ አንዱ ቢሮ ገባሁ። መርማሪው " የመንግስት ባለስልጣናትን ክብር ነክታችኋል፣ ኦቦ ሽመልስ አብዲሳን ይውረድ፣ አዳነች አቤቤንም ስልጣን ታስረክብ፣ በአጠቃላይ ኦሮሞ ሀገር መምራት አይችልም ብላችሁ በሐበሻ ወግ መጽሔት አውጥታችኋል። አሁን እንዴት ሀገር መምራት እንደምንችል ላሳያችሁ ነው የያዝንሽ" አለኝ።

ነገሮችን ላስረዳው ስሞክር "ዝም በይ አንቺ አታስተምሪኝም። ይህንን ሞያ ጥርሴን የነቀልኩበት ነው። እናንተ በዘመነ ህወሃትም መንግስትን እርስ በርስ ስታባሉ ነበር ዛሬ ደግሞ እኛ ላይ ተነሳችሁ ብሎ በጥፊ መታኝ።

ጥፊ፣ እርግጫ፣ ቦክስ ለመርመርማሪዎቹም ለደህንነት ሰዎቹም የመግባቢያ ቋንቋቸው እስኪመስል ድረስ በየደቂቃው ስድብ፣ ጥፊ፣ እርግጫ. . በመጨርሻም ከምርመራ ክፍል አውጥተው ብዙዎች ወዳለንበት ክፍል መለሱኝ። አካላዊ ጥቃትና ሀራስመንት አድርሰውብኝ በማግስቱ ፍርድ ቤት የለ ፖሊስ ጣቢያ የለ በመኪና ጭነው ወሰዱኝ።

ደሞ የት ይሆን ስል 4 ኪሎ ብልጽግና ጽ/ቤት ፊት ለፊት ስንደርስ " ውረጂ" ብሎ በሀይለ ቃል ተናገረ። እኔ ከመኪናው ስወርድ ወደ መጣበት አቅጣጫ ተፈተለከ።
የሀገራችን ሁኔታ እዚህ ደረጃ ደርሷል። ቤተሰብ ሳይሰማ እንደወጣሁ ሶስት የሰቆቃ ቀንና ሌሊቶች አሳልፌ ወደ ቤቴ ገባሁ።
አሁን የገባኝ ማንኛችንም በዚህ ሰአት ደህና ነን ብለን ስለደህንነታችን በነጻነት መናገር የማንችልባት ሀገር ውስጥ እየኖርን እንዳለ ነው። እኔ ብቻ ሳልሆን ሁለት ጋዜጠኞች እንዲሁም ዜጎች በማንነታቸው ብቻ በደህንነት ሰዎች ሊታፈኑ፣ ሊሰወሩ ይችላሉ።
---------------------------

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ማሳደድ፣ ማሰርና መሰወር በመንግስት የደህንነት ሰዎች ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጉባዔ፣ Cpj እና ሌሎችም ሀገር ዓቀፍና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት የጉዳዩን አሳሳቢነት በመግለጽ ተደጋጋሚ መግለጫ ማውጣታቸው ይታወቃል።

#cpj
#amnestyinternationalitalia
#Amnesty_International_USA
#AmnestyInternational
#ethio_fimaljournalist
ከይትባረክ ዋለልኝ
2.5K views12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 15:19:10
የብልፅግናን መንግስት በመቃወም በደብረ ማርቆስ ህዝባዊ እንቢተኝነት እየተካሄደ ነው።
2.3K views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 18:28:41
1.4K views15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 18:28:19 ከአማራ ፋኖ አንድነት ምክር-ቤት የተሰጠ መግለጫ
የተከበረኸው የአማራ ህዝብ

ከመቸውም ጊዜ በላይ በምንጊዜም ጠላቶችህ የጥፋት ወጥመድ ተጠምዶብሀል። እንደሚታወቀው የአማራ ፋኖ ከጥንት ጀምሮ ሀገር እየታደገ የመጣ የሀገር አድባር የኢትዮጵያ መከታ ሆኖ ዘመናትን አሻግሯታል።

ወራሪው የትግራይ ሀይል የእናቱን ጡት በነከሰበት ጊዜም ክተት ለነፃነት፣ መክት ለእናት ሀገር ብሎ ተዋግቷል፣ ሙቷል ቆስሏል። የባለስልጣኑን ወንበርም አድኗል። ዘርፈው ሻንጣ ጠቅልለው ሊወጡ የነበሩት ካድሬወችም ተመልሰው ከወንበራቸው ተቀምጠዋል። ለዚህ ውለታው ተረኞቹ በየቀኑ ሲያወግዙን እና ሲያጥላሉን ቆይተዋል። በዚህ ያልበቃቸው ጠላቶቻችን ፈረሳቸውን ብአዴንን ተጠቅመው የአማራን ፋኖ እና የአማራ ልዩ ሀይል ትጥቅ አስፈትተው አማራን ለማጥፋት ጋላቢወቹ ህውሀት እና ኦነግ በብልፅግና ሽፋን ሊያጠፉን በፈረሳቸው በብአዴን በኩል በራችን ድረስ መጥተዋል። በመሆኑም ሁሉም አማራ ከአማራ ፋኖ እና ከአማራ ልዩ ሀይል ጎን በመሰለፍ አማራን ከማንኛውም ጥቃት ትከላከል ዘንድ የአማራ ፋኖ አንድነት ምክርቤት ጥሪውን ያስተላልፋል!

የአማራ ልዩ ሀይልን እና ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን አቅዶ ወደ ስራ የገባው ተስፋፊ እና ጨፍጫፊው የኦረሙማ ሀይል እየተጠቀመባቸው ያሉት ብአዴን እና የብአዴን እርዝራዦች፣ የስርዐቱን የእጅ ጥራጊ መብላት የለመደባቸው ከሀዲ የፖለቲካ እና የፀጥታ አመራሮች፣ የዋንጫ ልቅላቂ መጠጣት የለመዱ አንዳንድ አድሀሪ የአማራ ተወካይ ተብየወች፣ አማራነታቸውን ክደው የአብይን አጥፊ ወንጌል ተቀላቅለዋል። በአማራ ህዝብም የዘር ፍጅት አብረው አውጀዋል። በአንፃሩ ሰው በላው የአብይ መንግስት የአማራን ህዝብ እያጠፋ መሆኑ ገብቷቸው በድብቅ እና በግልፅ ከኛ ዘንድ የሆኑ የፖለቲካ እና የፀጥታ አመራሮች ምስጋና ይገባቸዋል። እስከ መጨረሻው የድል ጮራ ድረስ በፅናት እንዲታገሉም እንጠይቃለ።

ከአማራ ፋኖ አንድነት ምክርቤት ጎን ለተሰልፋችሁ የአማራ ልዩ ሀይሎች በሙሉ የናንተ ዕውነት፣ ፅናት፣ አይበገሬነት፣ ከግብረ-በላወቹ በላይ የአንበሳ ግርማሞገስ አለው፣ ስለ አማራነት ታምናችሁ ከስግብግቦቹ እና አምባገነኖቹ ጋር አንተባበርም አማራ ሆነን ነው የተወለድነው አማራ ሁነን ታግለን እንሞታለን በማለታችሁ ኮርተንባችኋል! የጋራ ትግላችንም ለድል ይበቃል፣ የንፁሀንን እንባ እንጠርጋለን፣ የአማራን እርስቶችም እናስከብራለን።
...
የተከበራችሁ የአማራ ልዩ ሀይል እናንተ ልክ እንደ አማራ ፋኖ ተክዳችኋል። የሞታችሁለት፣ የቆሰላችሁበት፣ የደማችሁበት ትግል፣ በመጨረሻ አፈሙዝ አዙሮባችኋል። ምክንያቱ ደግሞ አማራ በመሆናችሁ አማራን ለማጥፋት አቅዶ እየሰራ ያለው የብልፅግ መንግስት ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት እና ሁመራን፣ የራያ አለማጣ እና ወፍላን እርስቶቻችንን አሳልፎ ለመስጠት እንቅፋት ይሆኑኛል ያለውን የአማራ ፋኖን እና የአማራ ልዩ ሀይልን ትጥቅ በማስፈታት በአማራ ህዝብ ላይ ክህደት እየፈፀመ ይገኛል። ይሄን እኩይ ሴራ ተረድታችሁ ለአማራ ህዝብ ለመታገል እና ህዝባችንን ለማታገል ቆርጣችሁ ከፋኖ ጎን የተሰለፋችሁ የአማራ ልዩ ሀይል አባላት እና አዛዦች ለአማራ ህዝብ እስከመጨረሻ የደም ጠብተችሁ በታማኝነት እንድትፋለሙ በአማራ ህዝብ ስም እንጠይቃለን።

የብአዴን አሽከላ ለመሆን የወሰናችሁ የአማራ ልዩ ሀይል የክፍለ ጦር አዛዦች እና ከዛ በላይ ያላችሁ አመራሮች ለማዕረግ ጭማሪ፣ ለስልጣን፣ ለተሻለ ጡረታ፣ ለቤትመስሪያ ቦታ እና መኪና ብላችሁ አማራነታቹህን እና ክብራችሁን ለንዋይ ፍቅር አሳልፋችሁ በመስጠት፣ በኩርነታችሁን የሸጣችሁ ይሁዳወች እናንተን ለዘለዓለም የአማራ ህዝብ ይቅር አይላችሁም። ልጆቻችሁን እና ቤተሰቦቻችሁንም ጭምር አንገት አስደፍታችኋል።

አማራን የካዳችሁ ግብረበላ ጥቁር አማራወች፣ ከመንግስት ጎን የተሰለፋችሁ አክቲቪስቶች፣ ፖለቲከኞች እና ባለስልጣናትን ዛሬ እንኳን ከህዝባችን ትካሻ በመውረድ ይሄንን አስከፊ ስርዐት ለመታገል እና ለማስወገድ ከህዝባችን ጎን እንድትሰለፉ ጥሪ እናቀርባለን።

የአማራ አድማ ብተና፣ የአማራ ፓሊስ እና የአማራ ሚሊሻ ስለ አማራነት ከሚዋደቀው አማራ ፋኖ እና ከአማራ ልዩ ሀይል ጎን እንድትሰለፍ እንጠይቃለን። ኦነግ ሸኔ እና ትህነግ በጋራ ሊያጠፉህ ወስነው አንተ ግን ከአማራው ወንድምህ ጋር አፈሙዝ እንድትዟዟር እያሴሩ ነው እምቢ አማራነኝ ብላችሁ ከአማራ ወንድማችሁ ጋር ለማንነታችሁ ትፋለሙ ዘንድ በአማራነታቸው በተጨፈጨፉት የንፁሀን ደም ስም እንጠይቃችሁአለን።

የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን የአማራ ህዝብ ትግል ለበላይነት የሚደረግ ሳይሆን የኢትዮጵያን አንድነት ግቡ ያደረገ ለሰላም፣ለፍትህ ፣ለእኩልነት እና ለዲሞክራሲ የሚደረግ እንዲሁም ፣ከሁሉም በላይ በህይወት መኖር የተከለከለውን የአማራ ህልውና አደጋ ለመቀልበስ የተገደድን በመሆናችን ከጎናችን በመሰለፍ የበኩላችሁን ትወጡ ዘንድ የአማራ ፋኖ አንድነት ምክርቤት በጥብቅ ያሳስባል።

የመከላከያ ሠራዊት አባላትም ከአማራ ህዝብ እና ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንጂ ከአምባገነኖች ጎን እንደማትሰለፉ እንተማመንአለን። እናንተ የኢትዮጵያ እንጅ የተረኞች የወጭ እና ወራጅ ካድሬ መጠቀሚያ አይደላችሁም። ከናንተ ጋር አብሮ ከሞተው እና በአንድ ጉድጓድ ከተቀበረው የአማራ ፋኖ እና ልዩ ሀይል ጋር በመዋጋት ታሪካዊ ስህተት እንዳትሰሩ አደራ እንላለን።

ጀግናው የአማራ ህዝብ አባቶችህ እና እናቶችህ በከፈሉት መስዋዕትነት የቆመችውን ጥንታዊት አገርህ ኢትዮጵያ ከአንተ እንደተወሰደችብህ በመረዳት ለትግሉ በፅናት እንድትቆም አደራ እያልን በደም እና በአጥንታችን የአማራን ህዝብ የህልውና አደጋ እንቀለብሳለን። የሁላችንም የጋራ ሀገር ኢትዮጵያንም ከጠባብ እና ተስፋፊወች እንታደጋትአለን።

ከዚህ ውጭ በሆነ መንገድ ግን የአማራ ህዝብ ጠላቶች ሚሳኤል እና ድሮን ቀርቶ ኑክሌር ቢታጠቁ ህዝባችን በጋራ በማታገል ጠላትን ድባቅ እንመታለን። ጎልያድ በዳዊት ወንጭፍ መውደቁን ልብ እንላለን። ንጉስም በሰራዊቱ ብዛት እንደማይድን እናውቃለን። በወለጋ፣ በጉምዝ በወልቃይት በራያ በግፈኞች የፈሰሰውን ደም የምናደርቀው እምቢ ማለት ስንጀምር ነው። እምቢ በል አማራ!!
እምቢ ለርስቴ እምቢ ለማንነቴ

ህልውናችን በክንዳችን!!

የአማራ ፋኖ አንድነት ምክርቤት
መጋቢት 29/2015 ዓ.ም
1.4K views15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ