Get Mystery Box with random crypto!

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_media_center — አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center
የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_media_center — አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center
የሰርጥ አድራሻ: @amhara_media_center
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.55K

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2023-04-04 12:00:28
“ከጅቡቲ ወደብ ጋር የሚያገናኘውን የአስፓልት መንገድ ለመዝጋት እና ሁከት ለመፍጠር ሙከራዎች ተደርገዋል” በሚል የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የሦስት ሰዎች ህይወት አልፏል።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

"ከጅቡቲ ወደብ ጋር የሚያገናኘውን የአስፓልት መንገድ ለመዝጋት እና ሁከት ለመፍጠር ሙከራዎች ተደርገዋል” በሚል የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የሦስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጧል።

በተጨማሪም ከ10 በማያነሱት ላይ ደግሞ ከባድ የመቁሰል አደጋ መድረሱን በስልክ ያነጋገርናቸው የአይሻ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ይህንን ተከትሎም በዞኑ አብዛኛው አካባቢዎች ውጥረትና አለመረጋጋት በመፈጠሩ ከድሬዳዋ ወደ ጅቡቲ የሚወስደው አስፓልት መንገድ መዘጋቱን ከአካባቢው ማህበረሰብ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

“ተወልደን ካደግንበትና በቋሚነት ከምንኖርበት መፈናቀላችን አግብባ አይደለም” ሲሉ አስተያየታቸውን የገለፁት አቶ ጣሂር ዲረኔ የተባሉ ነዋሪ “የአፋር ክልል ከተሞች ከሆኑት ከገርበኢሴ፣ ኡንድፎ እና አደይቱ ከተሞች በታጠቁ ኃይሎች በደረሰባቸው ጥቃት ወደ ሲቲ ዞን መሰደዳቸውን” ይገልፃሉ።
ዘገባው የአዲስ ዘይቤ ነው።
1.6K views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 11:56:38
በደብረ ዘይት ከተማ የሞጣ ከነማ እግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾች ድብደባ ተፈጸመባቸው፤ ክለቡ ቀሪ ጨዋታዎችን በሌላ ቦታ እንዲያደርግም ጠይቋል።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

ሞጣ ከነማ ከመቱ ከነማ መጋቢት 24/2015 በነበረው ጨዋታ የመቱ ደጋፊዎችና ተጫዋቾች ሞጣ ከነማዎች ላይ ድብደባ በመፈጸም ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ክለቡ አስታውቋል።

በተካሄደው ጨዋታም ሞጣ ከነማ መቱን አሸንፎ መውጣቱ ይታወቃል።

በቀን 24/07/2015 የሞጣ እግር ኳስ ክለብ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባወጣው ፕሮግራም መሰረት ክለባችን ከመቱ እግር ኳስ ክለብ ጋር በነበረው ውድድር ጨዋታውን ካጠናቀቅን በኋላ በእለቱ የመቱ እግር ኳስ ክለብ ወጌሻና ተጨዋቾች ከሞጣ ከነማ ቅያሪ ቦታ መቀመጫ ላይ በመምጣት:_

በድንጋይ፣ በዱላ፣
በቦክስ ተዋጫዋቾችንና ስታፍ ላይ የአካል ጉዳት አድርሰዋል ብሏል።

በዚህም 3 ተጨዋቾች በክለቡ የህክምና ባለሙያ የታከሙ ሲሆን፣ 2 ተጫዋቾች ደግሞ በቢሾፍቱ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እያደረጉ ነው ብሏል።

በተጨማሪም በእለቱም ምሽት 1፡30 በኋላ የክለቡን ወጌሻና የተወሰኑ ተጫዋቾችን እንግዳ ማረፊያ ድረስ በመምጣት ተደጋጋሚ ጉዳት ለመፈፀም ዛቻና እንግርግሪያ ፈጽመዋል ሲል ሞጣ ከነማ አስታውቋል።

በዚህ ሁኔታ ቀሪ ውድድሮችን ለመጨረስ እጅግ በስጋት ውስጥ የምንገኝ በመሆኑ ፌዴሬሽኑ ይህን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባትና ክለባችን ያለምንም ስጋት ቀሪ ውድድሩን እንዲያጠናቅቅ እና በሌላ የውድድር ሜዳዎች ቀሪ ውድድሮችን እዲያካሂድ እንዲደረግልን ሲል አቤቱታ አቅርቧል።
1.7K views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 19:26:27
2.5K views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 19:26:12 ሜሪይ ጆይ ኢትዮጵያ ደብረብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች የ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 25 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

የሜሪይ ጆይ ኢትዮጵያ መስራች ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ እንደገለጹት ከዚህ በፊት መጥተው ባዩት ነገር በማዘናቸው ከሜሪ ጆይ በጎፈቃደኞች፣አርቲስቶችና በውጭ ከሚኖሩ ተባባሪ አካላት የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አሰባስበው መምጣታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ዛሬ የሰው እጅ ለመጠበቅ የተገደዱት ወገኖች ትላንት ብዙ ሀብት የነበራቸውና ሌሎችን ይረዱ የነበሩ በተፈጠረው ችግር ለአደጋ መጋለጣቸው አሳዛኝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በተቆራረጠ መንገድ ለተፈናቃዮች የሚደረገው ድጋፍም ለውጥ እንደማያመጣና መንግስት ዘላቂ መፍትሄ መፈለግ እንዳለበት አመልክተዋል፡፡

እስከዚያው ተባብረን ተፈናቃዮችን ልንረዳቸው ይገባል ብለዋል፡፡

የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ተስፋየ ዘውዴ እንደገለጹት በሰው ሰራሽ ችግር ወገኖች ለአደጋ መጋለጣቸው ልብ የሚነካና የሚያሳዝን ነው ብለዋል፡፡

በሀገራቸው ዜጎች በዚህ ደረጃ ችግር ውስጥ ወድቀው ማየት ልብ የሚነካ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአሜሪካና በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆኑት አቶ ዮኒ ቬጋስ እንደገለጹት ባለፈው ሳምንት መጥተው ችግሩን በማየታቸው ሜሪጆይ፣አርቲስቶች፣ባለሀብቶች ተነጋግረው ድጋፍ አሰባስበው ይዘው መምጣታቸውን አስታውቀዋል፡፡

አሁን ላይ ሳምንት ከነበረው የተፈናቃይ ቁጥር መጨመሩን መመልከታቸውን ጠቅሰው ችግሩን ለመቀነስ ሰው የሚፈናቀልበትን ምንጭ ማድረቅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

መንግስት ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡

ሰውን ለመርዳት ብሄር፣ ዘር ወይም ሃይማኖት እንደማያግደው ጠቅሰው በችግር ውስጥ ያሉትን ዜጎች ተባብሮ መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ወደፊትም የሚያደርጉት ድጋፍ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በተመሳሳይ በአሜሪካ ጆርጅያ ላስቬጋስ የሚኖሩት ወይዘሮ መስከረም ጌታቸው እንደገለጹት ለ3ኛ ጊዜ መምጣታቸውን አስታውሰው በካምፕ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች በተለይም ህፃናት ያሉበት ችግር በጣም አሳዛኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አርቲስት አብራር አብዶ አክለው እንደገለጹት ተፈናቃዮች ያላቸውን ሀብትና ንብረት አጥተው በችግር ውስጥ መሆናቸውን ጠቅሰው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በገንዘብ፣በቁሳቁስ፣በአልባሳት ድጋፍ እንዲያደርጉ በፈጣሪ ስም ጠይቀዋል፡፡

የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወይዘሮ እታገኝ አደም ድጋፉን ሲረከቡ እንደተናገሩት መንግስት ሰፊ ድጋፍ እያደረገ ቢሆንም ከተፈናቃዮች ቁጥር ብዛት አንጻር ሁሉንም መድረስ ባለመቻሉ ክፍተቱን ለመሙላት ተባብራችሁ የወገኖቻችን ችግር ተሰምቷችሁ ድጋፍ ላደረጋችሁ አካላት ሁሉ በክልሉ መንግስት ስም ምስጋና አቅርበዋል።

በአማራ ክልል ሰፊና ውስብስብ ችግር መኖሩን ጠቅሰው በክልሉ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ክልሉ 3 ጊዜ ጦርነት የተካሄደበት በመሆኑ ከክልሉ ውጭና በክልሉ ውስጥ ብዙ ህዝብ መፈናቀሉን አመልክተዋል፡፡

የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እንዳጋራው።
2.4K views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 17:09:21 የማይሳካው አማራን ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻ- አቶ ተፈራ ደምሴ እና ዶ/ር አረጋኸኝ ንጋቱ ከወ/ሮ የሽ ደምሴ ጋር https://youtube.com/live/OB9nierpoAQ?feature=share
2.5K views14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 11:33:12
978 views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-03 11:33:04 በአማራ ክልል በተመረጡ የተለያዩ ከተሞች የብልጽግናን ጸረ አማራ አገዛዝ የሚያወግዙ የተቃውሞ ሰልፎች ተደርገዋል።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 25 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

በህወሓት መራሹ ዘመን ባለፉት 27 ዓመታት በአማራ ህዝብ ላይ የተፈጸመው የጅምላ ፍጅት፣ እስር፣ መፈናቀል እና ስደት፣ ከ2013 ጀምሮ የፈጸመው የዙር ወረራ እና ፍጅትም የሚረሳ አይደለም።

መጋቢት 24/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ሰፊው የአማራ ህዝብም እየደረሰበት ያለው ተደጋጋሚ እልቂት እና መፈናቀል ከህወሓት አገዛዝ በእጅጉ በባሰ መልኩ ተጠናክሮ መቀጠሉ የሚታወቅ ነው።

መጋቢት 24/2010 የጠቅላይ ሚኒስትረጀ ብሎም የብልጽና አገዛዝ መምጣቱ ለአማራው ብሎም ለኢትዮጵያ ህዝብ ይዞት የመጣው ቱሩት ሳይሆን የመከራ ቀንበርን፣ እልቂት እና መፈናቀልን ነው በሚል በደም ላይ በመቆም ከሚደረግ የድጋፍ ሰልፍ በተቃራኒው ከእውነት ጋር በመቆም ጠ/ሚኒስትሩን እና የስርዓታቸውን ደባ የሚያጋልጥ የተቃውሞ ሰልፍ በአማራ ክልል በተመረጡ የተለያዩ ከተሞች ተደርጓል።

በህዝብ አስተባባሪ ኮሚቴ በኩል በተደረገ ጥሪ አማካኝነት በአማራ ክልል በተመረጡ የተለያዩ ከተሞች ከተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች መካከልም በስኬት የተጠናቀቁ በሚል የተገለጹት እንደአብነት:_

1) መርዓዊ፣
2) ኮረም፣
3) ምንጃር አረርቲ፣
4) በሀብሩ ወረዳ መርሳ እና ውርጌሳ፣
5) ቆቦ፣
6) መቄት፣
7) ጅጋ፣
8 ቡሬ እና
9) ደምበጫ የተባሉ አካባቢዎች ይገኙበታል።

በሰላማዊ ሰልፉም እነ አርበኛ ዘመነ ካሴ፣ እነ ፖለቲከኛ ስንታዬሁ ቸኮል፣ እነ ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጸሀፊ ታዲዎስ ታንቱ፣ ጋዜጠኞች፣ በእስር ላይ ያሉ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ
ፋኖዎች እና ሌሎች ፍትህ ፈላጊ ወገኖች ሁሉ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ተጠይቋል።

የአማራ ልዩ ኃይል ትጥቅ እንዲፈታ እና እንዲበተን ወይም ወደ ሌላ መዋቅር እንዲካተት የሚለው የስርዓቱ ውሳኔም ክፉኛ ተቃውሞ ገጥሞታል።

የአማራ ህዝብ የህልውና አደጋ ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት የልዩ ኃይል መዋቅሩ ይፍረስ ማለትም ለተጨማሪ እልቂት ድግስ ማዘጋጀት እንደማለት ስለመሆኑም ተገልጧል።

በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ፍጅት፣ መፈናቀል፣ መሳደድ እና ቤት ፈረሳ በአስቸኳይ እንዲቆምም ተጠይቋል።

ከወልቃይት፣ ጠገዴ፣ጠለምት እና ራያ መከላከያ ሰራዊት በሴራ እንዲወጣ መደረጉ እንዲቆም እንዲሁም የወልቃይት፣ጠገዴ፣ጠለምት፣የራያ፣ በጎጃም የመተከል እና በሸዋ የደራ አማራ ማንነት እና ሌሎችም ጥያቄዎች እንዲመለሱ ተጠይቋል።

በዘር ፍጅት ወንጀል ተጠያቂ ሊሆኑ የሚገባቸውን አቦይ ስብሃት ነጋን ለህክምና አሜሪካ እንዲሄዱ ፈቅዶ የሀገር ባለውለታ የሆኑትን የጦር ጄኔራል ተፈራ ማሞን ህክምና መከልከል ክህደት እና ጸረ አማራነት ነው፤ በአስቸኳይ በፈለጉት ቦታ ህክምና የማግኘት መብታቸው ሊከበር ይገባል የሚል ጥሪም ቀርቧል።

በተመሳሳይ በባህር ዳር ከተማም የተቃውሞ ሰልፉ የተደረገ ቢሆንም በመሃል አድማ በታኞች በሰልፈኞች ላይ ድብደባ በመፈጸም እንዲበተን አድርገዋል።

በደብረ ታቦር ቀድሞ ከፍተኛ የጸጥታ አካላት ስምሪት በመደረጉ እና የመስተዳድር አካላትም ሰልፉ እንዳይደረግ ከመከልከል አልፈው ቢያንስ ከአስር በላይ ወጣቶችን ማሰራቸው፣ በወልድያ ደግሞ የሰልፉ አስተባባሪዎች ከጸጥታ አካላት ጋር በመምከር ለሌላ ጊዜ እንዲራዘም ማድረጋቸውን ነው የአሚማ ምንጮች የገለጹት።
919 views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 19:42:50 መጋቢት 24 እና አማራው -ዓባይ ዘውዱ ከደራሲ ይሁኔ አወቀ ጋር https://youtube.com/live/bpMnmbiCUOo?feature=share
1.3K views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 16:06:45
የወፍላ፣ ኮረምና ዛታ ነዋሪዎች ማንነታቸው እንዲከበር የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 24 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የወፍላ፣ ኮረምና ዛታ ነዋሪዎች ማንነታቸው እንዲከበር የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።

"በሰልፉ ማንነታችን አይቀየርም፤ እኛ ዋግሹሞች እንጂ ትግራይ አይደለንም፤ ማንነታችን ይከበር በማለታቸው በትግራይ ኃይሎች የታሰሩ ወገኖቻችን ይፈቱ" የሚሉ መልእክቶችን በሰላማዊ ሰልፉ እያሰሙ ነው።
አሚኮ እንደዘገበው።
1.9K views13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 09:55:08 ኦሮሚያ ክልል ትጥቅ ከሚፈቱት ሰባት ክልሎች ዝርዝር ውስጥ አለመሆኑ ታወቀ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 24 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

መጋቢት 23/2015 በባህር ዳር በተካሄደው ስብሰባ ትጥቅ ማስፈታቱን በዝርዝር የገለፁት አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በዋናነት ከኦሮሚያ ክልል ውጭ ያሉትን ሰባት ክልሎች ብቻ እንደሚመለከት ገልፀዋል።

ትጥቅ የሚፈቱት በማለት የዘረዘሯቸው ሰባት ክልሎችም:_

1) አማራ፣
2) ትግራይ፣
3) አፋር፣
4) ቤንሻንጉል፣
5) ሶማሌ፣
6) ጋምቤላ እና
7) ደቡብ ክልል ናቸው።

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር
124 views06:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ