Get Mystery Box with random crypto!

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_media_center — አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center
የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_media_center — አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center
የሰርጥ አድራሻ: @amhara_media_center
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.55K

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-26 23:58:13
5.2K views20:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-26 23:58:13 ቀጣይ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ?

"ለውጥ" አደረግን ተብሎ ምዕራባውያንን ጭምር የወተወቱባቸው ሶስት ተሿሚዎች ናቸው። መአዛ ለቅቃለች። ብርቱካን ቀጥላለች። የቀረው ዶክተር ዳንኤል ነው። እሱንም ቢሆን ትህነግ እያማረረበት ነው።

ደህና ሰሩም አልሰሩም፣ ምዕራባውያን "እነዚህን ከሾሙ አበረታች ነው" ይላሉ ተብሎ የመጡት ሰዎች እየተማረሩ እየለቀቁ ነው። ዶክተር ዳንኤል ላይ ያለው ጫና የሚታወቅ ነው።

በጦርነቱ ትህነግ ለምዕራባውያን ያሳየውን ወዳጅነትና የተደረገለትን አይተው ደግሞ እነ ክንድያን አምጥተው ይሾሙ ይሆናል። "ለውጥ" ምናምን ያሉት አፈር ከበላ ቆይቷል። አሁን ምንም አይነት ማስመሰያ እንዳይኖራቸው የቀረው ዳንኤል ነው።

ሶስቱን ሰዎች ሾምን ብለው የውጮቹንም አደንቁረው ነበር። የኢትዮጵያን ህዝብም "ከብልፅግና ውጭ ሾምን" ብለው ደጋግመውለታል። አሁን አንድ ብቻ ቀርቷል። በቦታቸው ከትህነግም ወይንም ከቲክቶክ ያመጡ ይሆናል።
5.0K views20:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-26 14:15:51 ብርሃኑ ጁላ የራሱን ዘመድ አስር አለቃ ለምደባ አቅርቦ፤ ለዛ ስራ በቂ የሆኑ የሌላ ብሔር መቶ አለቃዎች አሉ ስትለው

በነገራችን ላይ የእነ ብርሃኑ ጁላ ምደባ እንደዛ ነው።
4.7K views11:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-26 12:33:45 የስራ ማቆም አድማዋን ገዥዎቹ ይፈልጓታል!

ብዙ ጊዜ የስራ ማቆም አድማ ወዘተ ጥሪ ወረቀት ፌስቡክ ላይ አያለሁ። ገዥዎቹ ለይምሰል ይቃወሙት ይሆናል እንጅ የሚፈልጉት ነው። በተለይ ያልተደራጀና ያልተጠና ከሆነ።

1) ገዥዎቹ ራሳቸው ህዝብ ስራ እያስፈቱ ነው። ጉዳያቸው አይደለም ባይሰራ። መንገድ ዘግተው ወደስራ እንዳይሄድ ሲከለክሉ ከርመዋል። ማዳበሪያ አያቀርቡ፣ ሲሚንቶ ከነጋዴ ጋር ተመሳጥረው በህገወጥ እየሸጡ ሌላውን ስራ አጥ አድርገውታል። በሶስት አመት ያልቃል የተባለ ግድብ 12 አመት የሞላው አለ። ፋብሪካዎቹ ስራ አቁመዋል። በሚቀጥለው አመት ደግሞ ተመራቂ አንቀጥርም ብለዋል። መስርያ ቤት ስራ የለም። ሄደህ ማየት ነው።ገዥዎቹ በኢትዮጵያ ላይ የስራ ማቆም አድማ ካወጁ ቆይተዋል። ብትሰራ ባትሰራ ጉዳያቸው አይደለም።

2) ወደ አገር ቤት የምትላከውን ትንሽ ዶላር ለራሳቸው አድርገዋል። ገንዘብ ጠፍቷል። አቅርቦት የለም። ነዳጅ በለው ስኳር ማቅረብ እየቻሉ አይደለም። ዘይት በለው ዱቄት ከቀን ቀን እየተወደደ ነው። ሱቅ ብትዘጋላቸው፣ ሳምንትና ወር ፀጥ ረጭ ብትል እረፍት የሰጠሃቸው ነው የሚመስላቸው። ችግሩ አንተ ባወጅከው የመጣ አድርገው፣ የአቅርቦት ጉዳይ ሳያስጨንቃቸው እረፍት ነው የሚወስዱበት።

3) የስራ ማቆም አድማ ስታደርግ ከአደባባይ ትጠፋለህ። ገዥዎቹ የሚፈሩት አደባባይ መውጣትን እንጅ ቤት ከተቀመጥክማ ደስታቸው ነው። ህዝብ የቤት ቁልፍ ቢሰጣቸው ዘግተውበት ቢጠፉ በወደዱ።

4) የስራ ማቆም አድማ የሚጎዳው ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ ውስጥ ያለውን ነው። አብዛኛውን ህዝብ ማለት ነው። ይህ ማለት ደግሞ ህዝብ የስራ ማቆም አድማ የጠራውን ያማርራል ማለት ነው። አሊያም ገዥዎቹ አድማ የጠሩት እንዲጠሉ ያደርጋሉ። ለኢኮኖሚ ምስቅልቅል የዳረገው ገዥው ሆኖ ህዝብን ያስራበው የሶስት ቀን አድማ አድርገው ያቀርቡልሃል። በጅራፍህ ትገረፋለህ ማለት ነው። ነፃ አወጣዋለሁ ባልከው ህዝብ ዘንድ ፖለታካ ይሰሩብሃል።

5) በተለይ ባልተቀናጀ መልኩ ሲደረግ ሌላ ቀን አዋጭና አስፈላጊ ሲሆን ቢጠራ ህዝብ ከቁም ነገር እንዳያየው፣ ስልቱን እንዲሰለቸው፣ ትግሉን እንዲርቀው ያደርጋል።

6) ዋናዎቹ ገዥዎቹ አማራ ክልል በኢኮኖሚ ድቅቅ እንዲል ይፈልጋሉ። ስራ አቁሞ ቢከርም አድማ የጠራውን አካል ያመሰግኑታል። ህዝብ ትግሉን ሊያግዝ የሚችለው ደግሞ ገንዘብ ሲኖረው ነው። ሌላው በህገወጥ መንገድ ስራ እየሰጠ፤ አማራው ባለችውም ዘግቶ ከዋለ ለጠላቶቹ አዋጭ ነው።

7) ትግል ጊዜን ይጠይቃል። ተማሪዎች ለአመታት የደከሙበት ፈተና የሚፈተኑበት ወቅት ላይ "የትምህርት ማቆም" ተብሎ ስልት ከታጋይ ይሁን ከገዥዎች የመጣው ግራ የሚያጋባ ነው።

ከዚህ ይልቅ የተቃውሞ ምንጩ ግራ እስኪገባቸው ድረስ ሊደረጉ የሚችሉ ስልቶች አሉ። በርካቶች ናቸው። ትግል የሚመራ አካል ስልቶቹን በደንብ አይቶ መርጦ፣ ጉዳትና ጥቅማቸውን አይቶ መሆን አለበት።

ህዝብ በቀላሉ የሚቀባበለው፣ ለሚዲያ ግቡ የሆነ፣ ሰው አይቶት ምልክት የሚያደርገው፣ ፋሽን የሚያደርገው፣ የፀጥታ ኃይሉ ህገወጥ ነው አይደለም ብሎ የሚወዛገብበት፣ ቢከለክል ከህዝብ ጋር የሚጣላበት ስልት ሞልቷል። ከዚህ ላይ ልፃፈው? አልፅፈውም! እንደዛ አይደረግም!
5.0K views09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-11 18:44:12
ወጣት ቢንያም ታደሰ ወደ አፋር ተላከ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ሰኔ 4/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አባል የሆነው ወጣት ቢንያም ታደሰ (ቢኒ ሳንጃው) እስር ላይ እያለ የተወሰዱበትን ስልክ እና ሌሎች ንብረቶቹን እንዲወስድ ፖሊስ በስልክ ጠርቶት በሄደበት እንደታፈነ መዘገባችን ይታወሳል።

ሆኖም ዛሬ እንደደረሰን መረጃ፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ በህገወጥ መንገድ የግፍ እስረኛውን ማፈኑ ሳያንስ ወደ አፋር-ሰመራ አግዞታል። ለአፋር መደበኛ ፖሊስም አሳልፎ ሰጥቶታል።

በቢንያም፣ በሌሎች የባልደራስ አባላት ላይና የገዢውን ቡድን ህገወጥ ድርጊት በሚቃወሙ ዜጎች ላይ የሚደረገውን አፈናና ተጨማሪ ህገወጥ ድርጊት ፓርቲያችን በጥብቅ ያወግዛል።

የግፍ እስረኞችንም በአስቸኳይ እንዲፈቱ ያሳስባል ሲል ባልደራስ ለእውነተኚ ዲሞክራሲ ፓርቲ ገልጿል።

መረጃው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ነው።
1.9K views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 18:49:23
5.9K views15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 18:47:26 የወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ግንቦት 29/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት በደብረ ብርሃን በመገኘት ከወለጋ ለተፈናቀሉ እና በድንኳን መጠለያ ካምፕ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች መጭውን ክረምት ታሳቢ ያደረገ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።

የተደረገው ድጋፍም ግምቱ 400,000 ብር /አራት መቶ ሺህ ብር / የሆነ ለ200 አባዎራዎች የተከፋፈለ መሆኑ ተገልጧል።

ድጋፉ የተደረገላቸው ወገኖችም ከአካባቢው የአየር ፀባይ እና ያሉበት የኑሮ ሁኔታ አንፃር ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን በመግለፅ ለተደረገላቸው ድጋፍ ከልብ አመሠግነዋል።

4ኛ ዙር ድጋፉ መሆኑን የገለጸው ድርጅቱ
ይህ እንዲሳካ ድጋፍ ላደረጉ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ለሚገኙ የማህበሩ አባላትን እና ደጋፊዎች ምስጋና አቅርቧል።

አሁን ላይ በደብረብርሃን ከተማ ብቻ ከ30,000 /ሰላሳ ሺህ / በላይ ተፈናቃዮች እንዲሁም በሰሜን ሸዋ ዞን አጠቃላይ 80,000 /ሰማኒያ ሺህ /ተፈናቃዮች ያሉ ሲሆን በዘላቂነት ህይወታቸው የሚሻሻልበትን መንገድ እንዲመቻችላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና በጎ አድራጎት ድርጅትም በቀጣይ ግዜ በዘላቂነት የወገኖቻችን ህይወት የሚቀይር ለወጣት ሴቶች የሙያ ስልጠና ለመስጠት እቅድ ያለው ሲሆን ይሄንን መደገፍ የምትፈልጉ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የምትገኙ ግለሰቦችና ማህበራት ከድርጅቱ ጋር በጋራ መስራት እንድትችሉ ጥሪ ቀርቦላችኋል።

ድርጅቱን መደገፍ ለምትፈልጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000347415891 "ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት" ብላችሁ ድጋፋችሁን ማድረስ እንደምትችሉ ተገልጧል።

ዋና መስሪያ ቤት አዲስ አበባ መገናኛ አደባባይ፣ ሲሊከን ቫሊ ኮሌጅ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ መሆኑን አስታውቋል።
5.7K views15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 15:29:59
6.2K views12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 15:29:50 በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የማክሰኞ ገበያ ወረዳ ነዋሪዎች የወሰንና ማንነት ጥያቄዎች በአስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጣቸው ለዓለም ማኅበረሰብ ድምፃቸውን አሰሙ።

የአማራ ሚዲያ ማዕከል
ግንቦት 27 2016 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በሰልፉ ላይ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የወረዳው ሰላም አስከባሪዎች፣ ወጣቶች፣ የመንግሥት ሠራተኞችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ኹነዋል።

ባለፉት ዓመታት የወልቃይት ጠገዴ ነዋሪዎች በአማራ ማንነታቸው ምክንያት እስራት፣ ግርፋትና ሞት እንዲሁም ለሰው ልጅ የማይገባ እንግልት ሲደርስባቸው መቆየቱን በሰልፉ ላይ መልእክት አስተላልፈዋል።

የወልቃይት ጠገዴ የወሰንና የማንነት ጥያቄውን የፌደራል መንግስት በህግ ሊያረጋግጥልን ይገባል ሲሉ ለዓለም ማኅበረሰብ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

የማክሰኞ ገብያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ጌታሁን ብርሀኔ በሕዝባዊ ሰልፉ ላይ ባስተላለፉት መልእክት፤ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ከደረሰበት ግፍና በደል አንፃር ሲታይ በሰው ልጅ ታሪክ ተፈፅሞ የማያውቅ ወንጀል የተፈፀመበት ሕዝብ መሆኑን ገልፀዋል። ለዚህ ሕዝብ ካሳና ይቅርታ በቂ እንኳን ባይሆንም ቅሉ ጉዳዩን ወደ ጎን በመተው በቁስል ላይ እንጨት እንደመስደድ ያክል የሚቆጠር ድርጊት አሁንም እየተፈፀመ ይገኛል ብለዋል።

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ጥያቄ ማንነቴ አማራ ነው እንጂ አማራ ልሁን የሚል ጥያቄ አይደለም ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፤ የፌደራል መንግስ እስካሁን ድረስ በጀት ሳይመድብ ቢቆይም ሃብታችንና በጀታችን ማንነታችን ነው ብሎ በርካታ ችግሮችን ተቋቁሞ መቆየቱን ገልፀዋል።

ትላንት በጦርነት ወደነበረበት የበጌምድር አማራ የተመለሰውን የወልቃይት ጠገዴ የወሰንና የማንነት ጥያቄ የፌደራል መንግስት በህግ ሊያረጋግጥልን ይገባል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ንፁህ የትግራይ ተወላጆች አሁንም ድረስ በወልቃይት ጠገዴ ምድር በሰላም እየኖሩ መሆኑ እየታወቀ ግን የትግራይ ተወላጆች ከወልቃይት ጠገዴ ተፈናቅለዋል የሚባለው ከእውነት የራቀ ሀሳብ ነው፤ ይልቁንስ ገዳዮችና ጨፍጫፊዎች እኩይ ሥራቸውን ፈፅመው መሄዳቸውን የማይካድራው የንፁሀን ጅምላ ጭፍጨፋ ዋና ማሳያ መሆኑን ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳች መምሪያ ኃላፊ አቶ ገብረዮሐንስ የሺነህ በበኩላቸው ሰልፉ በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በዛሬው እለት መካሄዱን ገልፀው ባለፉት ሰላሳ ዓመታት በህወሀት የጭቆና አገዛዝ ስርዓት የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የደረሰበትን ግፍና በደል ለዓለም ማኅበረሰብ ማሳየት የሰልፉ ዓላማ እንደሆነ ተናግረዋል።

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ በማንነቱ ምክንያት ተዘርዝረው የማያልቁ በደሎች ደርሰውበታል ያሉት ኃላፊው ንፁህ የወልቃይት አማራዎች በማንነታቸውና በያዙት እውነተኛ አቋም ምክንያት ተጨፍጭፈው ሳለ በእኛ ሞት ገዳዮች እንደሞቱና እንደተጎዱ ተደርጎ የሚወራው ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን ሊታወቅ እንደሚገባ ገልጸዋል። በታሪክ ሂደት "ወልቃይት ጠገዴን የትግራይ አንድ አካል መሆን ቀርቶ የወልቃይት ጠገዴን ሕዝብ አንድም የትግራይ ገዥ አስተዳድሮት አያውቅም ወደፊትም ቢሆን የማይታሰብ የቁም ቅዥት መሆኑን ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል" ሲሉ አሳስበዋል።

የወልቃይት ጠገዴ የወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ደምለው ጀጃው እንደተናገሩት የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ከ1985 ጀምሮ የነበረ የበርካቶች ንፁሀን ሕይዎት የተገበረበት እንደሆነ ተናግረዋል። የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ በትግል አማራዊ ማንነቱን አረጋግጧል ያሉት አቶ ደምለው፤ አሁንም ቢሆን መንግስት የሕዝቡን የማንነትና የወሰን እንዲሁም የበጀት ጥያቄዎች በአፋጣኝ ምላሽ ሊሰጥ ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል።

የሰልፉ ተሳታፊ የሆኑት መላከ ሰላም አዳነ ከፍያለው እንደተናገሩት የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ አማራዊ ማንነት እንዳለው እየታወቀ እስካሁን ድረስ በግዴታ ማንነቱን ተቀምቶ ቆይቷል፤ አባትና እናቴን የማውቀው እኔ ባለቤቱ እያለሁ ሌላ ማንነት በኃይል ተቀበል የሚለኝ አካል ሊኖር አይችልም ሲሉ ተናግረዋል።

እኛ ወልቃይት ጠገዴዎች እንግዳ ተቀባይ እንጅ በቤታችን ሌላ አዛዥና ፈትፋች እንዲኖር አንፈቅድም ያሉት መላከሰላም አዳነ ከፍያለው እስካሁን ልብሳችንን አጥፈን ለብሰን መቆየታችን መንግስት የማንነትና የበጀት ጥያቄያችንን ሳይመልስን የመቆየቱ ምሳሌ ነውና አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጠን ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸውን የጠገዴ ወረዳ መረጃ ያመላክታል።

አሚኮ ይህን ዘገባ ከገፁ አጥፍቶታል።
5.8K views12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 15:28:29
ሰበር ዜና!

ጀግናው አርበኛ ዘመነ ካሴ ከእስር አሁን ተፈታ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ግንቦት 27/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

አርበኛ ዘመነ ካሴ በአሁኑ ሰአት ከማረሚያ ቤት ወጥቷል።

ከመስከረም ወር ጀምሮ በባህር ዳር ሰባታሚት ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የቆየው አርበኛ ዘመነ ካሴ ዛሬ ከማረሚያ ቤት ወጥቷል::

በተለያዩ ጊዜያት ፍርድ ቤት በመቅረብ ክርክር ሲያደርግ የቆየው አርበኛ ዘመነ ካሴ የአማራ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 25/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት አርበኛውን በነጻ ማሰናበቱ ይታወሳል።

ሆኖም የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ በመተላለፍ በመንግስት አመራሮች ከማረሚያ ቤት ድጋሚ ለሁለት ቀናት የቆየው አርበኛ ዘመነ ዛሬ የባህር ዳርና አካባቢው ወጣቶች በተገኙበት ከሰባታሚት ማረሚያ ቤት ወጥቷል።

የባህር ዳርና አካባቢው ወጣቶች ትላንትም አርበኛው ሲለቀቅ ለመቀበል ማረሚያ ቤት በር ላይ ሲጠባበቁ መዋላቸው የሚታወስ ሲሆን ዛሬ አርበኛው ሲወጣ በደስታና በጭፈራ ተቀብለው ይዘውት ወጥተዋል።

አርበኛ ዘመነ ለ9 ወራት ያክል በግፍ እስር ላይ ቆይቷል።

የዘሜ ወዳጆች ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ/አለን!

ምንጭ_አሻራ ሚዲያ
5.0K views12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ