Get Mystery Box with random crypto!

ወጣት ቢንያም ታደሰ ወደ አፋር ተላከ። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ሰኔ 4/2015 ዓ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

ወጣት ቢንያም ታደሰ ወደ አፋር ተላከ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ሰኔ 4/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አባል የሆነው ወጣት ቢንያም ታደሰ (ቢኒ ሳንጃው) እስር ላይ እያለ የተወሰዱበትን ስልክ እና ሌሎች ንብረቶቹን እንዲወስድ ፖሊስ በስልክ ጠርቶት በሄደበት እንደታፈነ መዘገባችን ይታወሳል።

ሆኖም ዛሬ እንደደረሰን መረጃ፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ በህገወጥ መንገድ የግፍ እስረኛውን ማፈኑ ሳያንስ ወደ አፋር-ሰመራ አግዞታል። ለአፋር መደበኛ ፖሊስም አሳልፎ ሰጥቶታል።

በቢንያም፣ በሌሎች የባልደራስ አባላት ላይና የገዢውን ቡድን ህገወጥ ድርጊት በሚቃወሙ ዜጎች ላይ የሚደረገውን አፈናና ተጨማሪ ህገወጥ ድርጊት ፓርቲያችን በጥብቅ ያወግዛል።

የግፍ እስረኞችንም በአስቸኳይ እንዲፈቱ ያሳስባል ሲል ባልደራስ ለእውነተኚ ዲሞክራሲ ፓርቲ ገልጿል።

መረጃው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ነው።