Get Mystery Box with random crypto!

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_media_center — አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center
የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_media_center — አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center
የሰርጥ አድራሻ: @amhara_media_center
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.55K

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-25 18:52:18
"የባህርዳር ከነማ ደጋፊዎች ላይ የተሰነዘረው የቦንብ ጥቃት በጣም አሳፋሪ እና ነውርም ነው"

የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህርዳር (አወማ)

የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ግንቦት 17/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በንፁሃን ዜጎች ፣ ኳስ ደጋፊዎች ላይ ጥቃት በማድረስ የሚገኝ የፖለቲካ ትርፍ የለም ።

እንደዚህ አይነት ነውረኛ ተግባር በመፈፀም የአማራ ህዝብ ለመከፋፋል የሚደረግ እንቅስቃሴ ተሞክሮ የከሸፈ ያለፈበት ተግባር ነው ።

በፈተና ወቅት ህዝባችን ከምንጊዜውም በላይ አንድነቱን አስጠብቆ ይዘልቃል።

የአማራ ወጣቶች ማህበር በባህር ዳር ጉዳት በደረሰባችሁ ወንድም ፣እህቶቻችን ቁስላችሁ በተሎ ይሽር ዘንድ ያለውን ወገናዊ ምኞቱን ይገልፃል።

ድል ለጣናው ሞገድ!

ድል ለአማራ ህዝብ!
9.6K views15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 15:23:19
የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ከአቶ ስንታየሁ ቸኮል የያዘባቸውን የግል ፓስፖርት አንሰጥም ማለቱ ተሰማ በነገው እለት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።

የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ግንቦት 17/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የአቶ ስንታየሁ ቸኮል የግል ፓስፖርት ከሀገር ሊወጡ ስለሚችል አይሰጥም እንደተባሉ ገልጸዋል።

አቶ ስንታየሁ ቸኮል በሕገወጥ ቡድን በቤተክርስቲያ ቀኖና ጥሰት የተፈጠረውን ችግር በመቃወማቸው ከየካቲት 3ቀን 2015 ዓ,ም ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ እገታ አዋሽ ሰባት ለሁለት ወር ታስረው የቆዩ ሲሆን "በጥላቻ ንግግር " በ6 ክስ በፍርድ ቤት ተከሰዉ በ10ሺህ ብር ዋስ የተፈቱ መሆኑ ይታወቃል።

ይሁን እና አቶ ስንታየሁ ቸኮል በፖሊስ የተያዘባቸውን የግል ንብረት እንዲመለስ ቢጠይቁም ከስልክ ውጭ የግል ፓስፖርታቸዉን እንደማይሰጥ የነገራቸዉ ፌደራል ፖሊስ ምክንያቱን ሲጠይቁ ከሀገር ሊወጡ ስለሚችል ክሱ እስኪቋረጥ ድረስ ፓስፖርት አንሰጥም መባላቸውን ገልፀዋል።

አቶ ስንታየሁ ቸኮል በነገው እለት ግንቦት 18/2015 ዓም ጠዋት 3:30 በከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በተከሰሱበት የጥላቻ ንግግር የክስ መቃወሚያ ለማስገባት ከጠበቃቸው ታለማ እና አዲሱ ጌታነህ ጋር ይቀርባሉ።
ዘገባው የጽናት ሚዲያ ነው።
8.1K views12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-24 16:06:03
7.0K views13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-24 16:05:58 መንግሥት በቤተ ክርስቲያን ላይ የደቀነውን የህልውና አደጋ እና በንጹሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን የከፋ በደልን የሚያወግዝ አለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ሊጠራ ነው።

የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ግንቦት 16/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምዕመናን ኅብረት እንዳስታወቀው መንግሥት በቤተ ክርስቲያን ላይ የደቀነውን የህልውና አደጋ እና በንጹሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን የከፋ በደልን የሚያወግዝ አለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ ሊጠራ ነው።

በመንግሥት ጣልቃ ገብነት እና አቀናባሪነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ውስጥ በጥር ወር የተከሰተው የሕገ ወጥ ሹመት ችግሩ ያልተቀረፈ ከመሆኑም ባለፈ መንግሥት ስልቱን በመቀያየር ያቀደውን ትልም ለማስፈጸም በትጋት እየሰራ ይገኛል ብሏል ህብረቱ በመግለጫው።

አሁንም መንግሥት በቀጥታ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል ለራሱ አጀንዳ አስፈጻሚ ሊሆኑ የሚችሉ ሊቃነ ጳጳሳትን በመመልመል ዓላማውን ለማስፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስን የመክፈል ሥራ እየሠራ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር መሆኑን ጠቅሷል።

ለዚህም ዐቢይ ማሳያው በቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ የርክበ ካህናት ስብሰባ ላይ “ሊቃነ ጳጳሳት ለአንድ ብሔር ብቻ” ይሾሙ በማለት መንፈሳዊነት የሌለው፤ ከሐዋርያት አስተምህሮና ቀኖና ውጭ ለተግባራዊነቱም ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተካሄደ መሆኑ ነው ብሏል።

አካሄዱም ሐዋርያዊት ብለን የምናምንባትን ቤተ ክርስቲያን የፖለቲካ ሃሳብ ማስፈጸሚያ ከማድረግ አልፎ ቤተ ክርስቲያኒቱን እና ሃገራችንን የሚያጠፋ ነው ሲል አውግዞታል።

መንግሥት ቤተ ክርስቲያኒቱ በሰላም እንዳትተዳደር በቅዱስ ሲኖዶስ መንፈሳዊ አስተዳደር ውስጥ ጣልቃ በመግባት፣አገልጋይ ካህናቷን፣ ሊቃውንቷን እና ምእመናኗን በመግደል፣ በማሰር እና በማሰቃየት መከራ እያጸናባት ነው የመጨራሻ ግቡም ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ከምድሪቱ ላይ ማጥፋት ብሎም ኢትዮጵያ የምትባል ሃገርን መበተን ነው ብሏል የሰሜን አሜሪካ የካህናትና የምእመናን ኅብረት በመግለጫው።

በመሆኑም:_

1- መንግሥት በቤተ ክርስቲያን ላይ ብሎም በንጹሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው በደል የከፋ ከመሆኑ ባሻገር ይህ የቤተክርስቲያንን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ነውና ጉዳዩን ለዐለም ማህበረሰብ ለማሳወቅ በቅርቡ ዐለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚጠራ፣

2- መንግሥት ቤተ ክርስቲያንን በመከፋፈል ሃይማኖትን የማጥፋት ሃገርንም የመበተን ስራ በከፍተኛ ደረጃ እየሰራ ነው።

ይህ ደግሞ በቀጣይነት የማያቋርጥ የእርስ በእርስ ግጭት ፤የደም መፍሰስ እና ግድያ የሚያመጣ፤ ምስራቅ አፍሪካን ብሎም መላው ዓለምን ከፍተኛ ሥጋት ላይ የሚጥል በመሆኑ ይህንን ጉዳይ ለዐለም አቀፍ ተቋማት ለማሳወቅ፣

3- ከአሜሪካን የሕግ አውጪ አካላት ጋር በሃገሪቱ ባለ ስልጣኖች ላይ የመጓጓዝ ማእቀብ እንዲጣል ብሎም በዐለም አቀፍ ፍርድ ቤት ሃገሪቱ ውስጥ በመንግሥት እየተካሄደ ላለው ግፍ ግድያ እና እንግልት የመንግሥት ባለስልጣናት እንዲጠየቁ የሚሰራ መሆኑን አስታውቋል።
6.5K views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 12:21:24
8.2K views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 12:21:15 የአማራ ሕዝባዊ ግንባር ተመሥርቷል።

የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ግንቦት 13/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ከአማራ ሕዝባዊ ግንባር የተሰጠ መግለጫ:_

መነሻችን የአማራ ህልውና፣ መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት!

በአማራው ሕዝብ ሕልውና እና በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የተደቀነው አደጋ ወደ ከባድ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። በሀሰት ትርክትና በጭፍን ጥላቻ የሚነዳው ጽንፈኛው የኦሮሙማ ፖለቲካ ታላቋን ኦሮሚያ ለመፍጠር ስትራቴጂካዊ ግብ አስቀምጦ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ብልፅግና ፓርቲን የተቆጣጠሩት እና በዐብይ አህመድ የሚመሩት አክራሪ የኦሮሞ ብሄርተኞች "ታላቋ" የሚሏትን ኦሮሚያ ለመፍጠር በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጽሙትን የዘር ፍጅት (ጄኖሳይድ) በማስፋፋት እና አዋሳኝ የሆኑ ክልሎችን ወርረው መሬት ለመቀማት እየተንቀሳቀሱ ነው።

በዚህ ሂደት ሰለባ እንዲሆኑ ካሰቧቸው መካከል ከአማራ ክልል በተጨማሪ ሲዳማ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤንሻንጎል፣ ጌዴዮ፣ ጉራጌ፣ ጋሞ፣ ድሬዳዋ እና አዲስ አበባ ይገኙበታል። "አገረ ኦሮሚያ የባህር በር ያስፈልጋታል" ብለው ስላመኑም፣ የሶማሌ ክልልን ለሁለት ቆርጠው ወደ ቀይ ባህር ለመዝለቅ ዕቅድ አዘጋጅተዋል። አዲሲቷ ኦሮሚያ ከሌላ ብሔሮች የጸዳች ብቻ ሳትሆን፣ ከኦርቶዶክስ እምነትና ከነባሩ እስልምና የጸዳችም እንድትሆን አልመው በመስራት ላይ መሆናቸው ፀሐይ የሞቀው ሃቅ ነው።

ባለፉት አምስት ዓመታት በተበታተነ መልኩም ቢሆንም ውጥናቸውን ተግባራዊ ለማድረግ በተደረገ እንቅስቃሴ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አማራዎች በኦሮሚያ ክልል የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የመፈናቀል እና የጅምላ ግድያ ሰለባ ሆነዋል።

በሀገራችን ላይ ያንዣበበው አደጋ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ እነዚህ ተጨባጭ ማስረጃዎች ናቸው።

ሁኔታዎች በዚሁ ከቀጠሉም የወደፊት እጣ ፈንታችን ከሩዋንዳ የዘር እልቂት የከፋ እንደሚሆን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል።

ይህንን በመላው ኢትዮጵያ፣ በተለይም የውጥኑ ዋና እንቅፋት ይሆናል ተብሎ በተሰጋውና የዘር-ፍጅት (ጄኖሳይድ) በታወጀበት የአማራ ሕዝብ ላይ የተነሳውን ከባድ አደጋ ለመቀልበስ የሚያስችል ሀገራዊ እና ሕዝባዊ ትግል የመጀመሪያ ምዕራፍ የሚያቀናጅ የአማራ ሕዝባዊ ግንባር (Amhara Popular Front) ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

የግንባሩ ዓላማ:-
1. የአማራ ሕዝብ ራሱን ከጅምላ ፍጅት (ጄኖሳይድ) ለመከላከል የሚያደርገውን የህልውና ትግል ቀዳሚ መነሻ ማድረግ፤

2. የአማራ ሕዝብ የህልውና ማስጠበቅ ትግል መዳረሻው የኢትዮጵያን እንደሃገር ለሚቀጥለው ትውልድ ማስተላለፍ፤

3. ለአማራ ሕዝብም ሆነ ለኢትዮጵያ የህልውና ስጋት የሆነውን ህገ-መንግስት ለኢትዮጵያ ሕዝብ አብሮነት ዋስትና በሚሰጥ መንገድ እንዲሻሻል ማድረግ፤

4. በሕዝባዊ ትግል ነፃ በሚወጡና የብልፅግና ፓርቲ አስተዳደር በሚፈረሰባቸው ቦታዎች ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከፋኖ እና የሕዝቡን ትግል ከተቀላቀሉ የመንግሥት ሹማምንት በተውጣጡ አካላት የአካባቢ አሥተዳደሮችን መመሥረት፤

5. በሚቋቋሙት የአካባቢ አሥተዳደሮች አማካኝነት የሕዝብን ሠላም፣ ዲሞክራሲያዊ መብቶችና ፀጥታ ማስጠበቅ፤

6. በአማራ ሕዝብ ላይ ያንዣበበውን የጅምላ የዘር ፍጅት (ጄኖሳይድ) እና የሀገር ብተናን አደጋ ለመግታት ከሚንቀሳቀሱ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኃይሎች ጋር ተባብሮ መስራት ናቸው።
በአብይ አህመድ የሚመራው የብልፅግና ፓርቲ ብቃት እና ሕዝባዊ መሠረት የሌለው፣ ከእውቀት የፀዳ፣ በጥላቻ የተመረዘ፣ ለሰው ልጅ ክብር የሌለው እና ሙሰኛ ድርጅት ነው። ህወሓት-መራሽ በሆነው የኢህአዴግ ዘመን የነበረውን ሥርዓት በከፋ ሁኔታ አጠናክሮ አስቀጠለው እንጂ አለወጠውም።

በኢህአዴግ ዘመን የነበረው የኦህዴድ አገዛዝ ለ27 ዓመታት ለኦሮሞ ሕዝብ ጠንቅ ሆኖ ኖሯል። የአሁኑ የኦህዴድ ብልፅግና ፓርቲ ደግሞ ይህንን የክህደት ታሪኩን ለማስረሳት እና ሕዝብን ከፋፍሎ ለመግዛት እንዲያመቸው ሥርዓቱን የኦሮሞ ሕዝብ ሥርዓት በማስመሰል የኦሮሞን ሕዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በሐሰት ትርክት እያጋጨ፣ በስጋትና በጥርጣሬ እንዲታይ እያደረገው ይገኛል። የኦሮሞ ሕዝብ ከዚህ ውጥንቅጥ እንደማያተርፍ ካለፈው የህወሓት ኢህአዴግ ሥርዓት ውድቀት ተምሮ አሰላለፉን ከሌላው ኢትዮጰያዊ ወገኑ ጋር ማድረግ ይገባዋል።

ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ሠላምና አንድነት ተጠቃሚው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው። የብልፅግና ፓርቲ ዘረኛና ኋላቀር አገዛዝ ሀገርን ከማፍረሱ በፊት መላው ኢትዮጵያዊ በጋራ በመቆም ሀገር የመታደግ ታሪካዊና ሕዝባዊ አደራን መወጣት ይኖርበታል። ይህን አደራ ለመወጣት የአማራ ሕዝብ ግንባር በበኩሉ በሙሉ ኃይሉ ይንቀሳቀሳል።

በመጨረሻም፣ የምስረታውን ዜና በሚያበስርበት በዚች ዕለት፣ የአማራ ሕዝባዊ ግንባር የሚከተለውን ጥሪ ያስተላልፋል፡ -

1. የአማራ ሕዝብ ሆይ! ከተከፈተብህ የጅምላ የዘር ፍጅት (ጄኖሳይድ) ራስህን ለመከላከል ከሕዝባዊው ፋኖ እና ሌሎች መሰል አደረጃጀቶች ጎን እንድትቆም፣ ቀሪው የኢትዮጰያ ሕዝብም ለዚህ የፍትህ ትግል በሙሉ ኃይልህ እንድትተባበር፤

2. የመከላከያ፣ የአማራ ክልል ልዩ ሃይልና ሚሊሺያ፣ የፖሊስ እና የአድማ ብተና አባላት ሆይ! በራሳቸሁ ሕዝብ ላይ እንድትተኩሱ የሚሰጠውን ትዕዛዝ እንዳትቀበሉ፣ በማንነትም ሆነ በሐይማኖት እንዳትከፋፈሉ፤

3. የሐይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ሆይ! ከአብራኩ ከወጣችሁት ሕዝብ ትግል ጎን እንድትቆሙ፤

4. የፖለቲካ ድርጅቶች ሆይ! የቆማችሁለትን ዓላማ በተለያዩ ሰበብ አስባቦች ከመክዳት ተቆጥባችሁ፣ የሕዝቡን ትግል በአግባቡ እንድትመሩ፤

5. የሲቪክ ተቋማት፣ የሙያና የሠራተኛ ማህበራት ሆይ! ራሳችሁን ከገዢው ፓርቲ ተፅዕኖ ነፃ በማውጣት ከትግሉ ጎን እንድትቆሙ፤

6. በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጰያዊያን ወይም ዲያስፖራ ሆይ! በሀገር ቤት ውስጥ ለፍትህ እና ለዘላቂ ሰላም የሚደረጉትን ትግሎች በሙሉ ኃይላችሁ እንድትደግፉ፤

7. የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጰያ ለተፈፀሙት እና በመፈጸም ላይ ላሉት የጅምላ የዘር ጭፍጨፋዎች በገለልተኛ አካል እና በሐቀኝነት አጣርቶ ፈጻሚዎቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን!

የአማራ ሕዝባዊ ግንባር
7.9K views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 17:10:43
የታላቁ ቦሩ ሜዳ ጉባኤ ቤት የሐዲስ ኪዳን መምህር በመሆን በርካታ ሊቃውንትን ያፈሩት መምህር ኃ/ማርያም ዘውዱ ባሕር ዳር ከተማ በጸጥታ ኃይሎች መወሰዳቸው ተሰማ።

የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ግንቦት 5/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የታላቁ ቦሩ ሜዳ ጉባኤ ቤት የሐዲስ ኪዳን መምህር በመሆን በርካታ ሊቃውንትን ያፈሩት መምህር ኃ/ማርያም ዘውዱ ባሕር ዳር ከተማ በጸጥታ ኃይሎች መወሰዳቸው ተሰምቷል።

መመህር ኃ/ማርያም ዘውዱ ሰሞኑን ሢመተ ጵጵስናን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያስጠብቅ፣ ምእመናንም የተሰጣቸውን ድርሻ እንዲወጡ እድል እንዲሰጣቸው በማኅበራዊ ሚዲያ በተከታታይ በልጅነት ሲጠይቁ ከነበሩ መምህራነ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ናቸው።

በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥንም ከ3 ዓመት በላይ የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜን በየሳምንቱ እያስተማሩ ይገኛሉ።

ምንጭ_የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድ ካስት አገልግሎት
10.6K views14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 17:40:41 https://www.youtube.com/live/Y5xIQvCucCQ?feature=share
9.2K views14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 00:13:21
ኢንተርፖል በጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ አፈና ላይ እጁ እንደሌለበት አረጋገጠ። ኢንተር ፖል ከትሪፕል ኤ በቀረበለት ጥያቄ በሰጠው መልስ እንዳስታወቀው ጋዜጠኛ ጎበዜ በኢንተርፖል ዳታ ቋት ውስጥ እንደሌለ እና በአፈናው እንዳልተሳተፈ በደብዳቤ ገልጿል።

የብልፅግና መንግስት በውሸት አፈና መፈፀሙ ሳያንስ ኢትዮጵያ ውስጥ እያለ ያፈነውን ጋዜጠኛ ከሀገር ወጥቶ ነበር ብሎ ለህዝብ የገለፀበት ሂደት ፍፁም ውሸት አሳፋሪ እና ብልፅግናዊ መልክ ያለው ነው ተብሏል።
12.1K views21:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 17:29:37
10.1K views14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ