Get Mystery Box with random crypto!

የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ከአቶ ስንታየሁ ቸኮል የያዘባቸውን የግል ፓስፖርት አንሰጥም ማ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ከአቶ ስንታየሁ ቸኮል የያዘባቸውን የግል ፓስፖርት አንሰጥም ማለቱ ተሰማ በነገው እለት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።

የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ግንቦት 17/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የአቶ ስንታየሁ ቸኮል የግል ፓስፖርት ከሀገር ሊወጡ ስለሚችል አይሰጥም እንደተባሉ ገልጸዋል።

አቶ ስንታየሁ ቸኮል በሕገወጥ ቡድን በቤተክርስቲያ ቀኖና ጥሰት የተፈጠረውን ችግር በመቃወማቸው ከየካቲት 3ቀን 2015 ዓ,ም ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ እገታ አዋሽ ሰባት ለሁለት ወር ታስረው የቆዩ ሲሆን "በጥላቻ ንግግር " በ6 ክስ በፍርድ ቤት ተከሰዉ በ10ሺህ ብር ዋስ የተፈቱ መሆኑ ይታወቃል።

ይሁን እና አቶ ስንታየሁ ቸኮል በፖሊስ የተያዘባቸውን የግል ንብረት እንዲመለስ ቢጠይቁም ከስልክ ውጭ የግል ፓስፖርታቸዉን እንደማይሰጥ የነገራቸዉ ፌደራል ፖሊስ ምክንያቱን ሲጠይቁ ከሀገር ሊወጡ ስለሚችል ክሱ እስኪቋረጥ ድረስ ፓስፖርት አንሰጥም መባላቸውን ገልፀዋል።

አቶ ስንታየሁ ቸኮል በነገው እለት ግንቦት 18/2015 ዓም ጠዋት 3:30 በከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በተከሰሱበት የጥላቻ ንግግር የክስ መቃወሚያ ለማስገባት ከጠበቃቸው ታለማ እና አዲሱ ጌታነህ ጋር ይቀርባሉ።
ዘገባው የጽናት ሚዲያ ነው።