Get Mystery Box with random crypto!

የታላቁ ቦሩ ሜዳ ጉባኤ ቤት የሐዲስ ኪዳን መምህር በመሆን በርካታ ሊቃውንትን ያፈሩት መምህር ኃ/ማ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

የታላቁ ቦሩ ሜዳ ጉባኤ ቤት የሐዲስ ኪዳን መምህር በመሆን በርካታ ሊቃውንትን ያፈሩት መምህር ኃ/ማርያም ዘውዱ ባሕር ዳር ከተማ በጸጥታ ኃይሎች መወሰዳቸው ተሰማ።

የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ግንቦት 5/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የታላቁ ቦሩ ሜዳ ጉባኤ ቤት የሐዲስ ኪዳን መምህር በመሆን በርካታ ሊቃውንትን ያፈሩት መምህር ኃ/ማርያም ዘውዱ ባሕር ዳር ከተማ በጸጥታ ኃይሎች መወሰዳቸው ተሰምቷል።

መመህር ኃ/ማርያም ዘውዱ ሰሞኑን ሢመተ ጵጵስናን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያስጠብቅ፣ ምእመናንም የተሰጣቸውን ድርሻ እንዲወጡ እድል እንዲሰጣቸው በማኅበራዊ ሚዲያ በተከታታይ በልጅነት ሲጠይቁ ከነበሩ መምህራነ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ናቸው።

በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥንም ከ3 ዓመት በላይ የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜን በየሳምንቱ እያስተማሩ ይገኛሉ።

ምንጭ_የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድ ካስት አገልግሎት