Get Mystery Box with random crypto!

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_media_center — አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center
የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_media_center — አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center
የሰርጥ አድራሻ: @amhara_media_center
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.55K

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 15

2023-04-02 09:54:49
የባልደራስ ም/ፕሬዝደንት አቶ አምሀ ዳኜው በፀጥታ ኃይሎች ታፈኑ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 24 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት አምሀ ዳኜው መጋቢት 23/2015 ዓ.ም ምሽቱን በደህንነት ኃይሎች እና በፌደራል ፖሊስ ታፍነው ተወስደዋል።

አቶ አምሀ ዳኜው ታፍነው የተወስውዱት ከመኖሪያ ቤታቸው ነው።

ከዚህ ቀደም በመጋቢት 2/2015 ዓ.ም በኦህዴድ/ብልፅግና መንግስት የታጠቁ ኃይሎች ለሰዕታት ታግተው እንደነበር ይታወሳል ሲል ባልደራስ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።
136 views06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 19:20:26
1.7K views16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 19:20:19 በደራ አማራዎች ላይ በአሸባሪ ኦነጋዊያን በተደጋጋሚ የሚፈጸምባቸው የግፍ እገታ፣ ግድያ፣ ዝርፊያ እና ቃጠሎ በአስከፊነቱ ቀጥሏል፤ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ብቻ ከ100 በላይ ነዋሪዎች ታግተዋል።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 23 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

በሸዋ የደራ አማራዎች በአሸባሪ ኦነጋዊያን በተደጋጋሚ የሚፈጸመው የግፍ እገታ፣ ግድያ፣ዝርፊያ እና የቤቶች ቃጠሎ ዛሬም በአስከፊነቱ ስለመቀጠሉ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከስፍራው እየደረሱ ያሉ መረጃዎች አመልክተዋል።

ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በቡድኑ ታግተው ወደ ጫካ ከተወሰዱት ከ100 በላይ ሰዎች መካከል በርካቶች ገንዘብ ከፍለው ሲለቀቁ የተገደሉ እና ደብዛቸው የጠፉ፣ መኖሪያ ቤታቸው የተቃጠለባቸው ወገኖች ስለመኖራቸው ለማወቅ ተችሏል።

ይህ ሲሆን የኦህዴድ ብልጽግና የክልሉ አገዛዝም ሆነ የፌደራል ፖሊስ አማራዊ የማንነት ጥያቄው ለዘመናት ታፍኖ ሲሳደድ ለኖረው ህዝብ እየደረሱ እንዳልሆነ ተገልጧል።

ከመንግስት አካላት ጭምር ስንቅ፣ ትጥቅ እና መረጃ የሚያገኙ በተለያዩ ጊዜያት ከኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ከ30 በላይ ባንኮችን የዘረፉ ራሳቸውን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ነን የሚሉ አሸባሪ ኦነጋዊያን በደራ አማራዎች ላይ የሚፈጽሙት ሁለንተናዊ ግፍ ማቆሚያ አለማግኘቱን ተከትሎ ከ2 ወራት በፊት ሚሊሾች ከአካባቢው መስተዳድር ጋር በመተባበር የተያዙ ከ7 በላይ ቀበሌዎችን ነጻ አውጥተዋቸው እንደነበር ተሰምቷል።

ይህ ተጋድሎ ከተደረገ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አንዳንድ የደራ ወረዳ አመራሮች የአማራ ሚሊሾችን ፋኖ ናቸው በማለት ለማስመታት እና ለማሳፈን ሙከራ በማድረጋቸው ግንኙነቱ እየላላ በመምጣቱ አሁን ላይ የሽብር ቡድኑ አባላት ወደለቀቋቸው ቀበሌዎች ጭምር ሰርገው እየገቡ ንጹሃንን አግተው እየወሰዱ፣ እየገደሉ እና በመቶ ሽህ የሚቆጠር ገንዘብ እያስከፈሉ መሆናቸው ተነግሯል።

ባሳለፍነው ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ከ100 በላይ ነዋሪዎች የታገቱ ሲሆን በያዝነው መጋቢት ወር ብቻ በደራ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች 75 ሰዎች በአሸባሪ ቡድኑ ታግተው ወደ ጫካ ተወስደዋል ብለዋል ነዋሪዎቹ።

ይኸውም:_

1) ከሀርቡ ደሶ ቀበሌ:_
15 ሰዎችን አግተው በመውሰድ እስከ 200 ሽህ ብር እንዲከፍሉ እየተደረገ ነው።

2) በመንቃታ ቀበሌ:_
30 ሰዎችን አግተው ወስደዋል።

21 የሚሆኑት 200 ሽህ ብር ከፍለው ተለቀዋል።

3) ማካፍታ ጅሩ ሮጌ:_
በመጋቢት 3ተኛ ሳምንት 5 ሰዎችን አግተው ወስደዋል።

ታፍነው የተወሰዱት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አልተመለሱም።

4) ከሩሱባ ቀበሌ:_
6 ሰዎችን ታፍነው ተወስደው አልተመለሱም።

5) በቾ ቀበሌ:_
2 ሰዎች ታፍነው ተወስደው አልተመለሱም።

6) አዳሃ መልኬ ቀበሌ:_
10 ሰዎች ታፍነው ወደ ጫካ ተወስደዋል።

7) ወሬ ገብሮ:_
7 ሰዎች ታግተው በቡድኑ ተወስደዋል።

ከታገቱት መካከልም አማራዎችን እየለዩ በመግደል እና አፍኖ ደብዛ በማጥፋት ላይ ስለመጠመዳቸው ከነዋሪዎች ለአሚማ የደረሰው መረጃ አመልክቷል።

አግተው የወሰዷቸውን ለማስለቀቅ ሚሊሾች ወደ አካባቢው እንዳይሄዱም ሆንተብሎ በሀሰት የአማራን ስም በመጥራት እያጠፉ በመሆን አስቸጋሪ መሆኑ ተገልጧል።

የፌደራል ፖሊስ በቱቲ የሚኖሩ የአማራ ሚሊሻዎችን አብረን እንዝመት በማለት ከዘመቱ በኋላ በክህደት የደራ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊን አቶ አሰፋ ነበበን ለማፈን ሙከራ ማድረጉ እና ከተወሰነ ጊዜ በኋላ እንዲፈታ መደረጉ ይታወሳል።
1.7K views16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 18:55:41 ለመከላከያ ሰራዊት አባልነት በሚል ከቀበሌ ተመልምለን ወደ ነቀምት ከተወሰድን በኋላ በአማራዊ ማንነታችን ብቻ እንድንመለስ ተደርጓል ሲሉ በጉቶጊዳ ወረዳ የጃርሳ ቶሌራ ቀበሌ ወጣቶች ተናገሩ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 23 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉቶጊዳ ወረዳ ከጃርሳ ቶሌራ ቀበሌ ለመከላከያ ሰራዊት በሚል ተመልምለው ወደ ነቀምት ከተወሰዱ በኋላ እንዲመለሱ ከተደረጉት ወጣቶች መካከል አንዱን እና ሌላ አንድ የአካባቢው ነዋሪን አነጋግሯል።

የጃርሳ ቶሌራ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ 11 ወጣቶች ለመከላከያ ሰራዊት አባልነት በሚል ከቀበሌ ተመልምለው የካቲት 29/2015 ወደ ነቀምት በጸጥታ አካላት ታጅበው ተወስደዋል።

ከተወሰዱ እና የሜዲካል ምርመራውን ካለፉ በኋላ ግን በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ እንድንመለሱ ስለመደረጉ ገልጸዋል።

ከቀበሌ ተመልምለው ወደ ነቀምት ከተወሰዱ በኋላ 2 ልጆች በሜዲካል ምርመራ እንዲመለሱ መደረጉ ተወስቷል።

በ3ተኛ ቀናቸው እንዲመለሱ የተደረጉት ወጣቶችም:_

1) አድምጠው ካሳሁን እና
2) ያብባል ይባላሉ።

ለ10 ቀናት ያህል በወረዳ የስብሰባ አዳራሽ እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ ግን "እናንተ አታስፈልጉም" በሚል ከቀበሌው ተመልምለው የተላኩ አማራዎች ተለይተው እንዲመለሱ ስለመደረጉ ተገልጧል።

በአጠቃላይ ከጃርሳ ቶሌራ ቀበሌ ለመከላከያ ሰራዊት በሚል ተመልምለው ከተላኩ እና ከተጉላሉ በኋላ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ የተደረጉት የአማራ ወጣቶችም:_

1) አድምጠው ካሳሁን፣
2) ሰለሞን ባህሩ፣
3) ማንደፍሮ ልዬው፣
4) ማስረሻ፣
5) ሸጋ ታዴ፣
6) አየነው ቢያልፈው፣
7) ልብሞኝ፣
8 አቡሻ፣
9) ካሳሁን ጎበዜ፣
10) ሙሉቀን ዳኛቸው እና
11) ያብባል የሚባሉ ወጣቶች ናቸው።

ከ100 በላይ የኦሮሞ ተወላጆችን ወደ ጉቶጊዳ ወረዳ ባቀኑ በ7ኛ ቀናቸው ለይተው ገንዘብ እየከፈሉ ለስልጠና ሲልኩ የአማራ ልጆችን ግን ያለምንም ክፍያ ከአስር ቀናት የአዳራሽ ቆይታ በኋላ ወደ ቀበሌያቸው እንዲመለሱ አድርገዋል በሚል ካድሪዎች ተወቅሰዋል።

"እዚህ ተቀምጣችሁ ኦሮምኛ ለምን አትችሉም?" በሚል ጥያቄ ሁሉ በአንዳንድ የጉቶጊዳ ካድሪዎች ስለመጠየቃቸውም ምንጮች ተናግረዋል።

በጉቶጊዳ ወረዳ ካድሪዎች ዘረኛ አሰራር የተነሳ በአማራዊ ማንነታችን ብቻ መጋቢት 21/2015 በ10ኛ ቀናችን ወደ ቀበሌያችን ታጅበን እንድንመለስ ተደርጓል ብለዋል።
1.6K views15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 17:59:54
የሸዋሰማ ልማት ማህበር ዋና ስራ አኪሂያጅ እና የአማራ ምሁራን መማክርት አመራር ረ/ት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው መታፈናቸውን ቤተሰቦቻቸው ገለፁ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 23 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

መጋቢት 22/2015 በመኖሪያ ቤታቸው እያሉ የታፈኑት የሸዋሰማ ልማት ማህበር ዋና ስራ አኪሂያጅ እና የአማራ ምሁራን መማክርት አመራር ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው ለደብረብርሃን ተፈናቃዮች ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ከረጂ ወገኖች በማሰባሰብ አከፋፍለዋል።

የመኝታ ፍራሽም ለተፈናቃይ ሲያሰባስብ ሰንብቶ መጋቢት 22/2015 ምሽት በማስጫን፣ መጋቢት 23/2015 ቅዳሜ ረፋድ ለማከፋፈል ያዘጋጁ መሆኑ ታውቋል።

ይሁን እንጅ መጋቢት 22/2015 ከምሽቱ 4:00 ለጥያቄ እንፈልግሃለን ባሉ አካላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው የት እንዳለ ለማወቅም አልተቻለም ሲል ዘሀበሻ ዘግቧል።
1.6K views14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 17:55:41 ከናዝሬት በቅርብ ርቀት ጮሬ በተባለ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ አሸባሪ ኦነጋዊያን በ3 አማራዎች ላይ እገታ ሲፈጽሙ አንደኛውን በጥይት ቀጥቅጠው ገደሉ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 23 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

በምስራቅ ሸዋ ዞን ከናዝሬት በቅርብ ርቀት በምትገኘው ጮሬ በተባለች አካባቢ ነዋሪ የሆነው ደረጀ በላይነህ ገብረ ዮሃንስ በመኖሪያ ቤቱ በተኛበት በአሸባሪ ኦነጋዊያን ከበባ ተደርጎ በ30 ጥይት ቀጥቅጠው በግፍ የገደሉት ስለመሆኑ ቤተሰቦቹ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል።

አሳዛኝ ግድያው የተፈጸመውም መጋቢት 18/2015 ከሌሊቱ 5 ሰዓት ላይ መሆኑ ታውቋል።

በአልሞትባይ ተጋዳይነት ወቅትም
አቶ ደረጀ በላይነህ አሰቃቂ ግድያ ከፈጸሙት መካከል አንዱን ይዞ መውደቁ ወይም መግደሉ ተሰምቷል።

ሟች አቶ ደረጀ በላይነህ ገብረ ዮሃንስ ዕድሜው 36 ዓመት ሲሆን የ3 እና የ11 ዓመት ልጆች አባት መሆኑ ተገልጧል።

ስርዓተ ቀብሩም በእለተ ማክሰኞ መጋቢት 19/2015 ተፈጽሟል።

በጮሬ አካባቢ ከ5 ቀናት በፊት በተመሳሳይ ሌሎች 3 አማራዎችዎ በመኖሪያ ቤታቸው እያሉ መዋቅራዊ ድጋፍ ባላቸው በእነዚህ አሸባሪ ኦነጎች ታግተው ወደ ጫካ መወሰዳቸው እና ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አድራሻቸው አልታወቀም ሲሉ ነዋሪዎች ለአሚማ ተናግረዋል።

ከተደራጁ ነፍሰ ገዳዮች መካከልም አንዱን ይዞ መውደቁ ወይም አንዱን መግደሉ ታውቋል።
1.5K views14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 17:54:22
1.5K views14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 17:54:14 አሳዛኝ ዜና!

ከምስራቅ ወለጋ ኪረሞ ወረዳ ተነስተው ለህክምና ወደ አማራ ክልል በእግራቸው እየተጓዙ የነበሩ 5 አማራዎች በአሸባሪ ኦነጋዊያን በግፍ ተገደሉ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 23 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

አማራዎች በማንነታቸው ተለይተው በአሰቃቂ መልኩ በተደጋጋሚ ከተጨፈጨፉባቸው በዋናነት 9 የኦሮሚያ ዞኖች መካከል የምስራቅ ወለጋ ዞን አንደኛው ነው።

በምስራቅ ወለጋ ዞን በሁሉም ወረዳዎች በሚባል ሁኔታ አሸባሪ እና ወራሪ ኦነጋዊያን ከመንግስት አካላት ጭምር በስንቅ፣በትጥቅ እና በመረጃ እየተደገፉ ተደጋጋሚ አማራ ተኮር ፍጅት፣ የማፈናቀል እና ዩየማሳደድ አስከፊ ወንጀል ፈጽመዋል።

ከእነዚህ ወረዳዎች መካከል አንዱ የሆነው ኪረሞ በኦሮሞ ልዩ ኃይል በማንነታቸው የታሰሩ ሴቶች፣ህጻናት እና አቅመ ደካሞች ጭምር በግፍ ተገድለዋል።

መጋቢት 19/2015 ከንጋቱ 12 ሰዓት ገደማ ጀምሮ ከኪረሞ ወረዳ ሀሮ አዲስ ዓለም እና ከባጊን ቀበሌ ተነስተው ለህክምና ወደ አማራ ክልል በእግራቸው እየተጓዙ የነበሩ 5 አማራዎች በአሸባሪ ኦነጋዊያንን በግፍ ተገድለዋል።

እነዚህ እድሜያቸው ከ35 እስከ 50 ዓመታት የሆኑት አማራዎች ለህክምና በሚል በአባይ በርሃ በኩል ጫካ ለጫካ እየሄዱ ባሉበት አባይ ወንዝ እንደደረሱ በአሸባሪ እና ወራሪ ኦነጋዊያን ተይዘው አረመኔያዊ በሆኑ መልኩ በጥይት እና በስለት ተወግተው ተገድለዋል።

በግፈኞች የተገደሉት አማራዎችም:_

1) አቶ ክንዱ አምሳሉ፣
2) አቶ ፈንታልጅ አቸነፍ፣
3) አቶ ሲሳይ ነጋሽ፣
4) አቶ መሀመድ ሀሰን እና
5) ወ/ሮ ሰርኬ ተገኘ የተባሉ የኪረሞ ነዋሪዎች ሲሆኑ በተለይም ወ/ሮ ሰርኬ ተገኘ እና አቶ መሀመድ ሀሰን እናት እና ልጁ አንድ ላይ የመገደላቸው መራር ዜና ብዙዎችን አሳዝኗል።

በወቅቱም የታመሙትን እናት ወ/ሮ ሰርኬን እየደገፉ ወደ አማራ ክልል በመውሰድ ለማሳከም እና አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታም ለማግኘት በሚል ጭምር በእግር ተጉዘው አባይ ወንዝ ሲደርሱ ነው ከተደበቁበት ጎሬ በመውጣት የገደሏቸው።

በጥይት ከመቱ በኋላም በምሳር እና በቆንጨራ ጭምር ጭንቅላታቸውን እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎቻቸውን በመምታታቸው እና በመቆራረጣቸው ለቀብርም አስቸጋሪ እንደነበር ተመላክቷል።

አቶ ክንዱ አምሳሉ፣አቶ ፈንታልጅ አቸነፍ እና አቶ ሲሳይ ነጋሽ ነዋሪነታቸው በኪረሞ ወረዳ ባጊን ቀበሌ ሰጊ ኪዳነ ምህረት በመሆኑ አስከሬናቸው እንዲነሳ ተደርጎ መጋቢት 20/2015 ከቀኑ 6 ሰዓት ገደማ ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።

የኪረሞ ወረዳ ነዋሪዎች ከነቀምት ወደ ባህር ዳር የሚወስደው የፌደራሉ መንገድ በአሸባሪ ኦነጋዊያን በመንግስት አካላት ትብብር ጭምር ከተዘጋባቸው ሶስት ዓመት ገዳማ እንደሆናቸው ተናግረዋል።

በዚህም ምክንያት በኦሮሞ የመንግስት የጸጥታ አካላት እና በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ቅንጅት በተደጋጋሚ የወረራ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል፤ በርካታ ሰላማዊ ነዋሪ አማራዎችም ተጨፍጭፈዋል።

አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ እንዳይደርሳቸው ከመደረጉም ባሻገር ወደ ኪረሞም ሆነ ወደ ነቀምት፣ ወደ ጎጃም እና ወደ ሌሎችም አካባቢዎች ተጉዘው እንዳይገበያዩ፣ እንዳይሸጡ፣ እንዳይለውጡ በመዳረጋቸው ለከፍተኛ ሁለንተናዊ ችግር ተዳርገዋል።

የህክምና ተቋም፣ ባለሙያ እንዲሁም መድኃኒት ባለመኖሩ ወላድ እናቶች፣ በተጨማሪም ህጻናት እና በአሸባሪው ኦነግ እና በኦሮሞ ልዩ ኃይሎች የቆሰሉት ነዋሪዎች ህክምና ባለማግኘታቸው በርካቶች እየሞቱ ስለመሆኑ የአካባቢው የመረጃ ምንጮች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል።

ከፍተኛ የሆነ የአቅርቦት ችግር እንዳለ የሚናገሩት ነዋሪዎች መከላከያም በአማራዎች ጭፍጨፋ በተፈጸመበት ኪረሞ ከገቡ 3 ወራት የተቆጠረ ቢሆንም ለሀሮ አዲስ ዓለም አማራዎች ሊደርሱከት እንዳልቻሉ ተመላክቷል።

ማዳበሪያ የለም፣ በጸጥታ ችግር የተነሳ ተንቀሳቅሰን ለመስራት ተቸግረናል፣ መውጫ መግቢያ አጥተናል፣ ኑሮ በከፍተኛ ሁኔታ ተወዷል፣ እንደአብነትም አንድ የልብስ ሳሙና እስከ 100 ብር እንዲሁም 5 ሊትር ዘይት ከተገኘ እስከ 1,600 ብር እየገዛን ለመጠቀም ተገደናል ብለዋል።

በመጨረሻም የሚመለከተው አካል ሁሉ በአስቸኳይ ፍትህ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
1.7K views14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 22:30:07 "አገርን ለትርምስ፤ ሕዝብን ለጥቃት የሚያጋልጥ አደገኛ ውሳኔ ነው!"

በጌታቸው ሽፈራው

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 22 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ የክልል ልዩ ኃይሎች የቡድን መሣርያዎችን ለመከላከያ እንዲያስረክቡ እና ወደ መደበኛ ፖሊስና ወደ ማረሚያ ቤት ፖሊስ እንዲቀየሩ መወሰኑ ተሰምቷል።

ይህ ውሳኔ ጊዜውን ያልጠበቀ፤ ፍፁም ኃላፊነት የጎደለው፤ በተለይም ጥቃት ያንዣበበበትን ሕዝብ ለማስመታት ያለመ አደገኛ ውሳኔ ነው።

1) ከምንም በፊት በውሳኔው ላይ የተሳተፈው አመራር በሙሉ በቀጣይ ለሚፈጠር አገራዊ ትርምስ እና የሕዝብ ጥቃት ተጠያቂ መሆኑ መታወቅ አለበት።

በተለይ በማንነቱ ተለይቶ እየተጠቃ ያለው፤ በሐሰት ትርክት የተደራጁ ታጣቂዎች በየአቅጣጫው እያጠቁት የሚገኘው አማራን ወክያለሁ ብሎ በውሳኔው የተሳተፈ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ አመራር ለዚህ ታሪካዊ ስህተት ተጠያቂ መሆን ይኖርበታል።

2) ውሳኔው የተወሰነው በሽብተኝነት ተፈርጀው የነበሩ ታጣቂዎች መሣርያ ሳያወርዱ፤ ይልቁንም እንደ ትህነግ ያሉት የጥፋት ኃይሎች ተጨማሪ ሠራዊት እያሰለጠኑ እና በየአካባቢው እነዚህ ታጣቂዎች ጥቃት እየፈፀሙ ባሉበት ወቅት መሆኑ ሕዝብን ያለ ፀጥታ ኃይል ከለላ ለጥቃት የሚያጋልጥ እጅግ አደገኛ ውሳኔ ነው።

ለአገር ህልውናና ዘላቂ ሰላም ቢታሰብ ኖሮ ከማንም በፊት ትጥቅ መፍታት የሚገባቸው በአገርና በሕዝብ ላይ መጠነ-ሰፊ ጥፋት የፈፀሙትና እየፈፀሙ ያሉት ትህነግና ኦነግ-ሸኔ ነበሩ፡፡

ሆኖም እየሆነ ያለው ከዚህ ተቃራኒ በመሆኑ እንዳይኖሩ የተፈለጉት አገርና ሕዝብን የታደጉት እንደ አማራ ልዩ ኃይል ያሉት ናቸው፡፡

ውሳኔውን ፍፁም ኃላፊነት የጎደለውና አደገኛ የሚያደርገው ይህ ነው፡፡

3) በሰላም ስምምነቱ መሠረት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የትግራይ አካባቢዎችን ይቆጣጠራል ሲባል ጥሎ በወጣበት፣ ትህነግ ትጥቅ እንዳይፈታ በተደረገበት፣ ኦነግ-ሸኔ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ እየገባ ያልተቋረጠ ጥቃት እየፈፀመ ባለበት እና የፌደራል ፀጥታ ኃይል ለሕዝብ ባልደረሰበት ሁኔታ የየአካባቢውን ሕዝብ ለጊዜው የሚጠብቁ ልዩ ኃይሎች ላይ የሚወሰነው ውሳኔ ለአጥቂዎቹ አቅም የሚሰጥ መሆኑ እሙን ነው።

እንደ ትህነግ እና ኦነግ-ሸኔ ካሉት በተጨማሪ የጎረቤት አገር ኃይልን ጥቃት እየመከቱ ያሉ ልዩ ኃይሎች እንዳሉ እየታወቀ እነዚህ ስጋቶች ባልተቀረፉበት በአንድ ፓርቲ ውሳኔ የሚደረገው ትጥቅ ማስፈታትና ልዩ ኃይሎችን መበተን አገርንም ጭምር ለአደጋ ያጋለጠ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል።

4) ትክክል ሆነም አልሆነም የክልል መንግሥታት የየክልሎቹን ፀጥታ ኃይሎች እንዲያዋቅሩ በሕግ የተቀመጠና ሲሠራበት የቆየ ጉዳይ ነው።

ይህ ሕግና አሠራር መሻር ካለበትም ሥርዓቱን መጠበቅ መሻር ይኖርበታል፡፡

መታወቅ ያለበት፣ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ መንግሥት የሚጠበቅበትን የዜጎችን ሕይወት የመጠበቅ ኃላፊነት መወጣት ባለመቻሉ ምክንያት የየክልሉ ሕዝብም የየአካባቢውን ልዩ ኃይል ከጥቃት ያድነኛል ብሎ ያምናል።

ስለሆነም ሕገ-መንግሥቱ ሳይሻሻል፣ ሕዝብ ጋር ውይይት ሳይደረግ፣ የክልል ምክር ቤቶችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ሳይወያዩበት፣ መሰል ጉዳዮችን ይፈታል ተብሎ የሚታሰበው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ሳያጠና በአንድ ያውም ተደጋጋሚ ስህተት በፈፀመ፣ ታማኝነቱን ባጣ እና የራሱን ችግር ለመፍታት በተቸገረ ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ የሚደረገው ውሳኔ ቅቡልነት የሌለው፣ ለተቃውሞና ትርምስ የሚዳርግ፣ ካለው ሕግና አሠራር አንፃር ሕገ-ወጥ መሆኑ መታወቅ አለበት።

5) ይህን ውሳኔ የወሰነው ብልጽግና ፓርቲ እርስ በእርሱ በሥልጣን ሽኩቻና መፈንቅለ መንግሥት በሚካሰስበት ወቅት የተወሰነው ይህ ውሳኔ እስካሁን ካለው አካሄድ ጠባብ ቡድናዊ ጥቅምና ፍላጎትን መሰረት አድርጎ ሌሎችን ለማጥቃት እንደሆነ የማያሳዩ መረጃዎች አሉ።

ባለው የሥልጣን መዛነፍና አፈፃፀም በሁሉም አካባቢዎች ተመሳሳይ አፈፃፀም እንደማይኖረው የሚታመን ከመሆኑም በላይ በተለይ እንደ አማራና አፋር ያሉ ክልሎች ላይ ሆን ተብሎ ጥቃት ለማስፈፀም የተደረገ ደባ ተደርጎ የሚወሰድ ነው።

ይህ ውሳኔ የአማራና አፋር ልዩ ኃይሎችን ትጥቅ በማስፈታት ትጥቅ መፍታት ለነበረበት ትህነግ ታጣቂ እድል ሰጥቶ ሁለቱ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀልና ጦርነት የሚያሳውጅ ውሳኔ ነው።

6) የፌደራል መንግሥትም ሆነ መከላከያ ሠራዊት ኦነግ-ሸኔ ጋምቤላ ከተማ ሲደርስ ሕዝብን አልታደጉም። አጣዬ ስትቃጠል አልደረሱም።

ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ገብቶ አካባቢውን ሲያተራምስ የደረሰ የለም፡፡

በየክልሉ ኦነግ-ሸኔ ትርምስ ሲፈጥር ፀጥታ አላስከበሩም።

ይህን አቅም ባላዳበሩበትና ፍላጎት ባጡበት ወቅት እነዚህ በሽብር የተካኑ ቡድኖች የትም ሄደው ጥቃት እንዲፈፅሙ እድል የሚያመቻች ውሳኔ ነው።

የአንዳንድ ክልሎች ፀጥታ አካላት አሁንም ስልጠና እየወሰዱ፣ ለመከላከያ ሰራዊት መሳርያ እያዋሱ ባሉበት አተገባበሩ እኩል ይሆናል ተብሎ አይታሰብም።

በተለይ ጥቃት ለመፈፀም እየጣረ የሚገኘው ትህነግ ትጥቅ እንዳይፈታ በተደረገበትና ለቀጣይ ጥቃት በተሰለፈበት የአማራና የአፋር ሕዝብን እንዲጠቃ የሚያመቻች፣ በተለየ ሁኔታ ትህነግ ሌት ተቀን ለጥቃት እቅድ የሚያወጣባቸውን የራያ፣ ወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት እና አበርገሌ ንጹሐን ላይ ሌላ ዙር በቀልና ዘር ፍጅት እንዲፈፀም የሚያመቻች ነው።

ውሳኔው አገሪቱን ወደ ሰላም ሳይሆን ወደ እልቂትና ትርምስ የሚስገባ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

7) አደጋውን የሚረዱት የልዩ ኃይል አዛዦች፣ አባላትና ሕዝብ በሚኖረው መከፋት እና እርስ በእርስ ግጭት አገር ከየአቅጣጫው ጦርነት ውስጥ እንድትገባ የታቀደበት አደገኛ ውሳኔ በመሆኑ በአስቸኳይ ተሽሮ ሒደቶችንና ስጋቶችን ባገናዘበ መልኩ መፈፀም ይኖርበታል።

ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ሕዝብ የዘር ፍጅት የታወጀበት መሆኑን እና የሚከላከልለት አካል እንዳይኖር የተደረገበት መሆኑን አምኖ ውሳኔውን በአደባባይ መቃወምና ማስቀየር ይኖርበታል!
2.4K views19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 22:26:10
2.2K views19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ