Get Mystery Box with random crypto!

አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_media_center — አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center
የቴሌግራም ቻናል አርማ amhara_media_center — አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center
የሰርጥ አድራሻ: @amhara_media_center
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.55K

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-04-05 23:38:18 በደብረ ታቦር ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ልታደርጉ ነው በሚል የታሰሩ ወጣቶች ተፈተዋል፤ ከመካከላቸው የተደበደቡ መኖራቸው ተገልጧል።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 27 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

በአማራ ክልል በተመረጡ ከተሞች መጋቢት 24/2015 የተደረገውን የብልጽግናን ስርዓት የሚያወግዝ ሰልፍ በደብረ ታቦር ከተማ ልታደርጉ ነው በሚል ከ15 ያላነሱ ወጣቶች መታሰራቸው ይታወሳል።

ጠ/ሚ አብይ ወደ ስልጣን የመጡበት መጋቢት 24/2015 በተለይም ለአማራ ህዝብ ይዞት የመጣው የመከራ መርገምት እንጅ የለውጥ ቱሩፋት የለም በሚል የስርዓቱን የ5 ዓመታት ቆይታ በተቃውሞ ሰልፍ መገለጹ ይታወሳል።

በደብረ ታቦር ሰላማዊ ሰልፍ ልታደርጉ ነው የተሰባሰባችሁት እና ለሰልፉ ወረቀት በትናችኋል በሚል ከ15 በላይ ወጣቶች በአንደኛ እና ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያዎች መታሰራቸው ይታወቃል።

ከመካከላቸውም በሶስት ወጣቶች ላይ በአያያዝ ወቅት ድብደባ የተፈጸመባቸው መሆኑን የዐይን እማኞች ለአሚማ ተናግረዋል።

ከሰልፉ ጋር በተያያዘ የታሰሩት ወጣቶችም ፍርድ ቤት ሳይወሰዱ መጋቢት 25/2015 ተፈተዋል።
2.8K views20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 23:36:50
2.6K views20:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 23:36:42 ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጸሀፊው ታዲዎስ ታንቱ የመከላከያ ምስክሮችን እያሰሙ ነው፤ ከ15 የመከላከያ ምስክሮች መካከል ዶ/ር ዳንኤል በቀለን ጨምሮ 3 ምስክሮች ተደምጠዋል።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 27 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጸሀፊው ታዲዎስ ታንቱ 5 በውጭ ሀገር የሚኖሩ ምስክሮችን ጨምሮ በድምሩ 15 የመከላከያ ምስክሮችን አቀርባለሁ ማለታቸውን ተከትሎ ከመጋቢት 25/2015 ጀምሮ የመከላከያ ምስክሮችን ማሰማታቸውን ቀጥለዋል።

በዚህም መሰረት መጋቢት 25/2015 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ አማራ ተኮር ጥቃት በተለያዩ ጊዜያት እና አካባቢዎች ስለመፈጸሙ በሪፖርታቸው አመላክተዋል።

በተመሳሳይ የምርጫ ቦርድ ኃላፊ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ እና ጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ መጋቢት 26/2015 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ተገኝተው መስክረዋል።

ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጸሀፊው ታዲዎስ ህዝብን በመንግስት ላይ እንዲነሳሳ ቅስቀሳ አድርገዋል ለተባሉትም እነ ወ/ሪት ብርቱካን በትጥቅ የተደገፈ እስካልሆነ ድረስ የሰላማዊ ትግል አካል እና ሀሳብን የመግለጽ መብት ስለመሆኑ በመጥቀስ አስረድተውላቸዋል።

ገና ከሚመሰክሩ የመከላከያ ምስክሮች መካከልም ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ጄኔራል አበባው ታደሰ እና ረ/ፕ አበባው አያሌው የተባሉ ባለስልጣናት ይገኙበታል።

አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ ) ከጠበቃ አዲሱ ጌታነህ ጋር ካደረገው ቆይታ እንደተረዳው
ብ/ጄኔራል ተፈራ ማሞ እና
ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለ ማርያም በህመም ምክንያት ገና የመከላከያ ምስክርነት ቃላቸውን አልሰጡም።

ፕ/ር ሀብታሙ መንግስቴ፣
ፕ/ር ኃይሌ ላሬቦ፣ የታሪክ ተመራማሪው አቻምዬለህ ታምሩ እና ሌሎች በድምሩ 5 ምስክሮች የፍ/ቤቱን ትዕዛዝ መሰረት በማድረግ በስካይፒ ወይም በዙም ሊቀርቡ እንደሚችሉ ተገልጧል።

የመከላከያ ምስክር የማሰማት ሂደቱም መጋቢት 27/2015 የሚቀጥል መሆኑ ተገልጧል።
2.6K views20:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 11:13:09
የአማራ ክልል መንግስት የአማራ ልዩ ኃይል ከመፍረሱ በፊት ግልፅ አቋሙን ለአማራ ህዝብ በሚዲያ ይፋ ያድርግ።

አቋሙን ካላሳወቀ አማራው በአንድነት አቋሙን ለመላው ዓለም ማሳወቅ ይኖርበታል።

አንድነት ሀይል ነው!

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር
1.1K views08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 00:03:20
1.8K views21:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 00:03:06 "አሸባሪ ትጥቅ ሳይፈታ አገር ያዳነ ልዩ ኃይል ትጥቅ ይፍታ ማለት በህዝብ ላይ ጦርነት ከማወጅ አይተናነስም!"

ጌታቸው ሽፈራው

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

1) ትህነግ ትጥቅ እንዳይፈታ ያደረገው መንግስት ነው። አቶ ሬድዋን ሁሴን "ህወሓት ስጋት አለበት" ብሏል።

ለትህነግ ደህንነት ብለው ነው ያን ወንጀለኛ ታጣቂው እንዳይፈታ ያደረጉት እንደማለት ነው።

ነገር ግን ሱዳን ያለውም እንዳይፈታ ተደርጓል። ሱዳን የትግራይ አካል አይደለም።

ሱዳን ስጋት ስላለበት አይደለም የሱዳኑ ኃይል ትጥቅ ያልፈታው። አላማው ህዝብን ለማስጠቃት ዝግጅት ነው።

2)ጌታቸው ረዳ ለቅሶ ቤት ተገኝቶ ወልቃይትን በኃይል እንይዛለን ማለቱ ተዘግቧል። ከአውሮፓና አሜሪካ ሄደው ሰሞኑን ሱዳን ያለው የትህነግ ኃይል ጋር ስብሰባ ያደረጉ የትህነግ ሰዎች ጊዜያዊ አስተዳደሩ ወልቃይትን በኃይል አስመልሳለሁ እንዳላቸው በመግለፅ "እንዘጋጅ" የሚል ቅስቀሳ አድርገዋል።

በሌላ ስብሰባ ትህነግ ለምን ትጥቅ እንደማይፈታ የተጠየቀው ጌታቸው ረዳ "ከእኛ ውጭ ሆነው ለጦርነት የሚዘጋጁ ኃይሎች አሉ።" ብሏል። ኃላፊነት ላለመውሰድ ነው።

የትህነግን ኃይል ለጦርነት የሚያዘጋጁት እነ ጌታቸው ጋር የሚውሉት ጀኔራሎች ናቸው። ዋናው ግን ለጦርነት እየተዘጋጁ እንደሆነ አምኗል።

3) እነ አዲሱ አረጋ የዘር ፍጅት አውጀዋል። ይህን የዘር ፍጅት የሚፈፅሙት ደግሞ በኦነግ ሸኔ እና ኦነግ ሸኔ አስመስለው በሚያሰማሩት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ነው።

የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አዲስ ምልምል እያሰለጠነ ነው። ኦነግ ሸኔም የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ትጥቅ ሳይፈቱ ሌሎቹ እንዲፈቱ ማድረግ የዘር ፍጅቱን ለማስፈፀም ነው የሚሆነው።

4) በሰላም ስምምነቱ መሰረት ትግራይን ይይዛል የተባለው መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ብቻ ሳይሆን ከትግራይ አዋሳኞች ወጥቷል።

በዚህ አካባቢ የሚኖረው ህዝብ በትህነግ የዘር ፍጅት ሲፈፀምበት የኖረና አሁንም እድል ቢያገኝ ሊበቀለው የሚፈልገው ነው። በዚህ ሁኔታ ልዩ ኃይል ትጥቅ ይፍታ ማለት ህዝብን ለዘር ፍጅት ማመቻቸት ነው።

5) በተለያዩ ጊዜያት ህዝብ ላይ ጥቃት ሲፈፀም መከላከያ አያገባውም፣ ትዕዛዝ አልተሰጠውም፣ በክልሎች ጉዳይ አይገባም እየተባለ የሚደርሰው ልዩ ኃይል ነው።

ይህ ሴራ ባልተቀየረበት ልዩ ኃይል ትጥቅ እንዲፈታ ማድረግ ህዝብን ለአሸባሪዎች አሳልፎ መስጠት ነው።

አሸባሪ ትጥቅ ሳይፈታ ልዩ ኃይል ትጥቅ ይፍታ ማለት ህዝብን ለማስጠቃት የተሸረበ ሴራ ነው።

የልዩ ኃይሎችን ጉዳይ በተመለከተ በተደረጉት ስብሰባዎች መጀመርያ አሸባሪን ትጥቅ አስፈቱ የሚል ቅድመ ሁኔታ ቀርቧል።

አሸባሪ ትጥቅ ሳይፈታ፣ የህዝብ ደህንነት ሳይረጋገጥ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ማስፈታት በህዝብ ላይ ግልፅ ጦርነት እንደማወጅ ነው።

መከላከያ ሰራዊትን ደጋግሞ የመታው የትህነግ ኃይል ትጥቅ ሳይፈታ፣ ህዝብን እየጨፈጨፈ የሚገኘው ኦነግ ሸኔና ኦነግ ሸኔን መስሎ የሚጨፈጭፈው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ትጥቅ ሳይፈታ የዘር ፍጅት ስጋት ያለበት ህዝብ ዋስትና የሆነ ኃይል ትጥቅ ይፍታ የሚል በህዝብ ላይ የታወጀን ጦርነት ማስቆም ግዴታ ነው።

ቅድመ ሁኔታ እንኳን ሳያሟሉ፣ ለትህነግ እየተቆረቆሩ ልዩ ኃይልን ለማስፈታት ሲሞክር አይሆንም ማለት ያስፈልጋል።

በዚህ ሁኔታ ልዩ ኃይሉ ትጥቅ እንዲፈታ ውሳኔ የወሰኑ አካላት ህዝብን ለማስመታት የተባበሩ እንደሆኑ መታወቅ አለበት።
1.7K views21:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 00:01:51
በአዲስ አበባ አማራን የማሰር እና የማሳደድ ስርዓታዊ ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል፤ ታደሰ ወዳይነው የተባለ የቦሌ ቡልቡላ ወጣትም መታሰሩ ታውቋል።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

ከሰሞኑ እንደ አዲስ ተጠናክሮ የቀጠለው አማራን የማሳር እና የማሳደድ ዘመቻ እንደቀጠለ መሆኑ ተገልጧል።

መጋቢት 24/2015
ታደሰ ወዳይነውን የተባለ ተአማራ ወጣት ከሚኖርበት ቦሌ ቡልቡላ አፍነው ቡልቡላ ፖሊስ ጣቢያ አሰረውታል።

ወጣቱ ሙሉ ጊዜውን በአማራ የህልውና ትግል በርትቶ የሚታገል ስለመሆኑ ተገልጧል።

የአማራ ወጣት ሲቪክ ማህበርን በአዲስ አበባ በማደራጀት በኩል ድርሻው የጎላ ስለመሆኑ ተመላክቷል።

በተለይም በቦሌ ክፍለ ከተማ በግንባር ቀደምትነት የተገኘ እና ያደረጀ ስለነበር በተረኞቹ ጥርስ የገባው ይህ ወጣት በ2011 ዓ.ም ጥቅምት 9 በቦሌ ቡልቡላ በመንግስት በተደራጁ ሸኔወች ድብደባ ተፈፅሞበታል ተብሏል።

በመጨረሻም የትግራይ ወራሪ ኃይል በአማራ ላይ ጦርነት ሲከፍት ከአዲስ አበባ ወደ ቆቦ ፣ወልድያ እና ድሬ ሮቃ ግንባር በመሰለፍ እና ሌሎችን በማደራጀት ከምስራቅ አማራ ፋኖ ጋር ሆኖ ስለመስራቱም ተመስክሮለታል።

የመረጃ ምንጭ ሳተናው ሚዲያ ነው።
1.5K views21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 00:01:04
እነ ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው፣ ስድስት ሰዎች በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቀርበው ለሚያዚያ 9 ተቀጠሩ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

የሸዋ ሰላም እና ልማት ማህበር (ሸዋሰማ) ዋና ስራ አኪሂያጅ እና የአማራ ምሁራን መማክርት አመራር ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸውን ጨምሮ በድምሩ ስድስት ሰዎች መጋቢት 25/2015 ከቀኑ 9 ሰዓት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው መዝገቡ ለይደር በተቀጠረው መሰረት መጋቢት 26/2015 ቀርበው ነበር።

ስድስቱም ማለትም:_

1) ረ/ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው፣
የሸዋ ሰላም እና ልማት ማህበር (ሸዋሰማ) ዋና ስራ አኪሂያጅ እና የአማራ ምሁራን መማክርት አመራር፣

2) ፕሮፌሰር መዓረጉ ቢያበይን፣
የተባበሩት አማራ ማህበር ሰብሳቢ፣

3) ሄኖክ አዲሴ፣
የወልድያ ዩኒቨርስቲ መምህር፣

4) ሰለሞን ልመንህ፣
የአማራ ወጣቶች ማህበር ስራ አስፈጻሚ፣

5) እርቁ ተስፋዬ፣
በህመም ላይ ያሉ የ77 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ፣

6) አምሀ ዳኜው፣
የባልደራስ ም/ፕሬዝዳንት ሁሉም መጋቢት 26/2015 በችሎት ተገኝተዋል።

ፌደራል ፖሊስ ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት በሚል በመክሰስ ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ እና የሰነድ እና የሰው ማስረጃ ለማሰባሰብ በሚል የጠየቀው 14 ቀናት በፍ/ቤቱ ተፈቅዶለታል፤ በዚህም ሚያዚያ 9/2015 እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

በህመም ላይ ያሉት የ77 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋው አባ እርቁ ተስፋዬ
መጋቢት 26/2015 በዋለው ችሎት በ20 ሽህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ትዕዛዝ መስጠቱን አሚማ ከጠበቃ ሰለሞን ገዛኽኝ ለመረዳት ችሏል።
1.5K views21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 12:03:13
1.9K views09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 12:03:07 መንግስት ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እና ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬን በአስቸኳይ እንዲፈታ ብሎም የፕሬስ አባላትን ማሰሩን እንዲያቆም የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ ( ሲፒጄ) ጥሪ አደረገ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

የፌደራል ፖሊስ አባላት የዩቲዩብ የግል ንብረት የሆነው ሮሃ ኒውስ የዜና ማሰራጫ መስራች እና ዋና አዘጋጅ አራጋው ሲሳይን በቁጥጥር ስር ስለማዋላቸው ጠበቃ አዲሱ አልጋው እና ባለቤታቸው ህይወት መና ለሲፒጄ ስለመግለጻቸው ተወስቷል።

በተመሳሳይ የአማራ ድምጽ የስርጭት ዋና አዘጋጅ ጌትነት አሻግሬ በአዲስ አበባ ከመኖሪያ ቤቱ እያለ ተወስዶ ስለመታሰሩ ጠበቃ አዲሱ አልጋው እና የጋዜጠኛው እህት እመቤት ታደሰ ሲፒጄን በስልክ አነጋግረዋል።

ሁለቱም ጋዜጠኞች በአዲስ አበባ አራዳ ፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሰሞኑ ቀርበው ፖሊስ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሁከትና ብጥብጥ ቅስቀሳ አድርገዋል በሚል ክስ እንደመሰረተባቸው ሲፒጄ አመላክቷል።

"ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ጌትነት አሻግሬ እና አራጋው ሲሳይ በአስቸኳይ መፈታት አለባቸው እና ከስራቸው ጋር በተያያዘም ተጨማሪ እንግልት እንዳይደርስባቸው ማረጋገጥ አለባቸው" ሲል የCPJ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ አንጀላ ኩንታል ተናግረዋል።

“ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ጋዜጠኞች በየጊዜው በሚደርሰው የእስር ዛቻ ውስጥ መሥራት የለባቸውም። ይህ ወሳኝ ጋዜጠኞችን ከእስር ቤት የመወርወር ዘዴ መቆም አለበት።" የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል።

የሮሃ ኒውስ ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እና የአማራ ድምጽ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬ:_

መጋቢት 17/2015 በፌደራል ፖሊስ ከመኖሪያ ቤታቸው መያዛቸው፣

መጋቢት 19/2015 ፍ/ቤት መቅረባቸው እና ለሚያዚያ 2/2015 ተለዋጭ ቀጠሮ የተሰጣቸው መሆኑ፣

መጋቢት 20/2015 ቤታቸው በፖሊስ መፈተሹ ይታወሳል።
1.9K views09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ