Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና! ጀግናው አርበኛ ዘመነ ካሴ ከእስር አሁን ተፈታ። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

ሰበር ዜና!

ጀግናው አርበኛ ዘመነ ካሴ ከእስር አሁን ተፈታ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ግንቦት 27/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

አርበኛ ዘመነ ካሴ በአሁኑ ሰአት ከማረሚያ ቤት ወጥቷል።

ከመስከረም ወር ጀምሮ በባህር ዳር ሰባታሚት ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የቆየው አርበኛ ዘመነ ካሴ ዛሬ ከማረሚያ ቤት ወጥቷል::

በተለያዩ ጊዜያት ፍርድ ቤት በመቅረብ ክርክር ሲያደርግ የቆየው አርበኛ ዘመነ ካሴ የአማራ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 25/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት አርበኛውን በነጻ ማሰናበቱ ይታወሳል።

ሆኖም የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ በመተላለፍ በመንግስት አመራሮች ከማረሚያ ቤት ድጋሚ ለሁለት ቀናት የቆየው አርበኛ ዘመነ ዛሬ የባህር ዳርና አካባቢው ወጣቶች በተገኙበት ከሰባታሚት ማረሚያ ቤት ወጥቷል።

የባህር ዳርና አካባቢው ወጣቶች ትላንትም አርበኛው ሲለቀቅ ለመቀበል ማረሚያ ቤት በር ላይ ሲጠባበቁ መዋላቸው የሚታወስ ሲሆን ዛሬ አርበኛው ሲወጣ በደስታና በጭፈራ ተቀብለው ይዘውት ወጥተዋል።

አርበኛ ዘመነ ለ9 ወራት ያክል በግፍ እስር ላይ ቆይቷል።

የዘሜ ወዳጆች ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ/አለን!

ምንጭ_አሻራ ሚዲያ