Get Mystery Box with random crypto!

የወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ድ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

የወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ግንቦት 29/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት በደብረ ብርሃን በመገኘት ከወለጋ ለተፈናቀሉ እና በድንኳን መጠለያ ካምፕ ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች መጭውን ክረምት ታሳቢ ያደረገ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።

የተደረገው ድጋፍም ግምቱ 400,000 ብር /አራት መቶ ሺህ ብር / የሆነ ለ200 አባዎራዎች የተከፋፈለ መሆኑ ተገልጧል።

ድጋፉ የተደረገላቸው ወገኖችም ከአካባቢው የአየር ፀባይ እና ያሉበት የኑሮ ሁኔታ አንፃር ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን በመግለፅ ለተደረገላቸው ድጋፍ ከልብ አመሠግነዋል።

4ኛ ዙር ድጋፉ መሆኑን የገለጸው ድርጅቱ
ይህ እንዲሳካ ድጋፍ ላደረጉ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ለሚገኙ የማህበሩ አባላትን እና ደጋፊዎች ምስጋና አቅርቧል።

አሁን ላይ በደብረብርሃን ከተማ ብቻ ከ30,000 /ሰላሳ ሺህ / በላይ ተፈናቃዮች እንዲሁም በሰሜን ሸዋ ዞን አጠቃላይ 80,000 /ሰማኒያ ሺህ /ተፈናቃዮች ያሉ ሲሆን በዘላቂነት ህይወታቸው የሚሻሻልበትን መንገድ እንዲመቻችላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና በጎ አድራጎት ድርጅትም በቀጣይ ግዜ በዘላቂነት የወገኖቻችን ህይወት የሚቀይር ለወጣት ሴቶች የሙያ ስልጠና ለመስጠት እቅድ ያለው ሲሆን ይሄንን መደገፍ የምትፈልጉ በሀገር ውስጥ እና በውጭ የምትገኙ ግለሰቦችና ማህበራት ከድርጅቱ ጋር በጋራ መስራት እንድትችሉ ጥሪ ቀርቦላችኋል።

ድርጅቱን መደገፍ ለምትፈልጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000347415891 "ወሎ ቤተ አምሐራ በጎ አድራጎት ድርጅት" ብላችሁ ድጋፋችሁን ማድረስ እንደምትችሉ ተገልጧል።

ዋና መስሪያ ቤት አዲስ አበባ መገናኛ አደባባይ፣ ሲሊከን ቫሊ ኮሌጅ ያለበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ መሆኑን አስታውቋል።