Get Mystery Box with random crypto!

ቀጣይ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ? 'ለውጥ' አደረግን ተብሎ ምዕራባውያንን ጭምር የወተወቱባቸው ሶስት ተ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

ቀጣይ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ?

"ለውጥ" አደረግን ተብሎ ምዕራባውያንን ጭምር የወተወቱባቸው ሶስት ተሿሚዎች ናቸው። መአዛ ለቅቃለች። ብርቱካን ቀጥላለች። የቀረው ዶክተር ዳንኤል ነው። እሱንም ቢሆን ትህነግ እያማረረበት ነው።

ደህና ሰሩም አልሰሩም፣ ምዕራባውያን "እነዚህን ከሾሙ አበረታች ነው" ይላሉ ተብሎ የመጡት ሰዎች እየተማረሩ እየለቀቁ ነው። ዶክተር ዳንኤል ላይ ያለው ጫና የሚታወቅ ነው።

በጦርነቱ ትህነግ ለምዕራባውያን ያሳየውን ወዳጅነትና የተደረገለትን አይተው ደግሞ እነ ክንድያን አምጥተው ይሾሙ ይሆናል። "ለውጥ" ምናምን ያሉት አፈር ከበላ ቆይቷል። አሁን ምንም አይነት ማስመሰያ እንዳይኖራቸው የቀረው ዳንኤል ነው።

ሶስቱን ሰዎች ሾምን ብለው የውጮቹንም አደንቁረው ነበር። የኢትዮጵያን ህዝብም "ከብልፅግና ውጭ ሾምን" ብለው ደጋግመውለታል። አሁን አንድ ብቻ ቀርቷል። በቦታቸው ከትህነግም ወይንም ከቲክቶክ ያመጡ ይሆናል።