Get Mystery Box with random crypto!

ከአማራ ህዝባዊ ሰራዊት በጎንደር የተሰጠ መግለጫ የአማራ ሚዲያ ማዕከል | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

ከአማራ ህዝባዊ ሰራዊት በጎንደር የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ሚዲያ ማዕከል
ሚያዝያ 04 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ ከህወሓት በቀጠለው ስርዓት በርዕዮተ-ዓለም በተደገፈ መልኩ ጥቃት እየደረሰበት መሆኑ ይታወቃል። ጠላቶቻችን ጥቃቱን አጠናክረው ለመቀጠልና ህዝባችን አንገቱን ደፍቶ እንዲኖር ለማድረግ ከሰሞኑ የመጨረሻ መጀመሪያ የሆነውን ተልዕኮ ጀምረዋል። ይኸውም በአማራ ልዩ ኃይልና በፋኖ ላይ ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻ በማድረግ ንፁሐንን ሳይቀር እየጨፈጨፉ ይገኛሉ።

ስለሆነም ከምንግዜውም በበለጠ መላው አማራ ተጋድሎውን መቀላቀሉን የምንገነዘብ ቢሆንም በሁሉም የአማራ ምድር እኩል ባልሆነ መንገድ መጓዝና ተናቦ አለመሄድ የትግሉን እድሜ የማርዘም እድል ይኖረዋል። በተጨማሪም የትግሉን ስልቶች መጠነ ሰፊ ማድረግና ከአካባቢያዊነት ወጥቶ ለሁሉም ፈጥኖ ደራሽ እንዲሆን ማድረግ የደረሰበት የእድገት ደረጃ የሚጠይቀው ጉዳይ ሆኖ ተገንቷል። በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች አሁን መሬት ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ፍሬ እንዲያፈራ አድርጎ መምራት አስፈላጊ በመሆኑና በአንፃራዊነት ጎንደር አካባቢ የደከመ የመሰለውን ህዝባዊ ንቅናቄ ለማጎልበት እንዲሁም ከጎጃም፣ ከወሎና ከሸዋ ጋር ተቀናጅቶ እኩል ለመራመድ እንዲያስችል፤ ከልዩ ኃይሎች፣ ከማህበራት፣ ከወጣቶች፣ ከፋኖዎች፣ ከሙህራን፣ ከሐይማኖት አባቶችና ከማህበረሰብ እንቂዎች የተውጣጣ ኮሚቴ ሚያዚያ 01/2015 ዓ.ም በጎንደር ከተማ መቋቋሙ ይታወቃል።

ይህ 41 አባላት ያሉት ቡድን በዋናነት ህቡዕ የትግል ስልትን የሚከተል ቢሆንም በ2008 እና 2009 ዓ.ም በጎንደር ሲደረግ የነበረውን ተጋድሎ በመድገም አካባቢውን ከአገዛዙ ነፃ ማውጣትን ያለመ ነው። ስለሆነም ኮሚቴው በትናንትናው እለት ጎንደር ከተማ ያስተላለፈውን የሰዎችን እንቅስቃሴ የመገደብና ሰዓት እላፊ ክልከላ ሙሉ በሙሉ እንደማይቀበለው በመወሰን 'የአምባገነኖች ክልከላ' በማለት ከመፈረጁም ባሻገር ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎችን ይፋ አድርጓል።

ከዛሬ ሚያዝያ 04/2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 13/2015 ዓ.ም ለአስር ቀናት በጎንደር ከተማና አካባቢው የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ እናስተላልፋለን። ይህን አድማ ኮማንድ ፖስት በሚል አጉል ክልከላ ለማደናቀፍ በሚሞክሩና በሚያደናቅፉ ግለሰቦች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የአማራ ህዝባዊ ሰራዊት በጎንደር ያስጠነቅቃል። የትግሉን አቅጣጫ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ብያኔ ለማበጀት፤ ከሌሎች አካባቢ የአማራ ህዝባዊ ሰራዊት መሪዎች ጋር በመነጋገር ቀጣይ አቅጣጫዎች እያስቀመጠ እንደሚቀጥል ጨምሮ ይገልፃል።
አማራነት ያሸንፋል!
ከአማራ ህዝባዊ ሰራዊት በጎንደር አስተባባሪ ኮሚቴ
ሚያዝያ 04/2015 ዓ.ም