Get Mystery Box with random crypto!

‹‹በሚዲያ የአማራ ሕዝብ ግፍ ደርሶበታል ብለህ ሕዝቡን አነሳስተሀል›› ሲል ፖሊስ ወነጀለ! ጋዜጠ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

‹‹በሚዲያ የአማራ ሕዝብ ግፍ ደርሶበታል ብለህ ሕዝቡን አነሳስተሀል›› ሲል ፖሊስ ወነጀለ!

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርቧል። ጋዜጠኛው የአማራ ሕዝብ ግፍ ደርሶበታል በማለት መንግስትን አስገድዶ ከስልጣን ለማውረድ በሚዲያ ሲንቀሳቀስ ነበር። ተከባብሮ የሚኖርን ሕዝብ ለመለያት ሲሰራ ነበር የሚል ክስ የቀረበበት ሲሆን፤ ለተጨማሪ ማጣራት 14 የምርመራ ቀን ታስሮ ይቆይልን ሲል ፖሊስ ጠይቋል።

የጋዜጠኛው ጠበቆች በበኩላቸው ፤ የሚዲያ ባለሙያ ታስሮ የሚጣራበት የሕግ አግባብ የለም ስለዚህ የዋስትና መብቱ ተከብሮ በዋስ ይለቀቅ›› ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። አክለውም -ደንበኛችን ከሕግ አግባብ ውጪ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ 48 ሰዓት አልፎታል፤ የመብት ጥሰት ተከናውኖበታል ሲሉ ፖሊስን ከሰዋል። ፖሊስም ‹‹ከባህርዳር መከላከያ ነው የያዘው፤ ከእነሱ እስክንረከብ ነው ጊዜ የሄደብን›› የሚል ምላሽ ለፍርድ ቤቱ ሰጥተዋል።

በመጨረሻ፣ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ በጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ላይ የ10 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በተያያዘ ዜና የኢትዮ ሰላም ሚዲያ ባለቤት የሆነውና ከጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ጋር በአንድ መዝገብ የተከሰሰው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው፤ በተመሳሳይ ክስ የተከሰሰ ሲሆን፤ የአስር ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶበታል። ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በአሁኑ ሰዓት ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ጊዜያዊ እስረኛ ማቆያ በእስር ላይ ይገኛል፡
ዘገባው የኢትዮ 251 ነው