Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና #ሸዋሮቢት ነፃነቷን አወጀች የአማራ ሚዲያ ማእከል ሚያዚያ 25 2015 አ/ም አዲስ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

ሰበር ዜና

#ሸዋሮቢት ነፃነቷን አወጀች

የአማራ ሚዲያ ማእከል
ሚያዚያ 25 2015 አ/ም
አዲስ አበባ

ሸዋ ሮቢት ከተማ ከትናንት ከሰዓት ጀምሮ በህዝባዊ ኃይሉ ቁጥጥር ሰር ገባች

ላለፉት ሶስት ቀናት ከኦህዴድ ሠራዊት ጋር ከፍተኛ ትንቅንቅ ሲያደርግ የነበረው የሸዋ ህዝብ እና ጀግናው የአማራ ፋኖ አንድነት በሸዋ አካባቢውን በመቆጣጠር ከትናንት ከሰዕት ጀምሮ ህዝቡ ራሱን ማስተዳደር ጀምሯል።

የከተማ አስተዳደሩ፣የብልፅግና ፅ/ቤት እና የፀጥታ ተቋማት በሙሉ በህዝብ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

የሸዋ ህዝብ ከተማዉ በህዝባዊ ሠራዊቱ ቁጥጥር ስር እንድትወድቅ ስንቅ በማቀበል፣መንገድ በመዝጋት፣ህዝቡን ሊጨፈጭፍ የገባውን ሠራዊት በመመከት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።

ህዝቡ ከጨፍጫፊው የብልፅግና አገዛዝ ወጥቶ እራሱን ማስተዳደር ለዓመታት ሲፈልገው እና ሲመኘው የነበረ መሆኑን በሀሴት ገልጿል።

የሸዋሮቢት ከተማ ህዝብ እና የአማራ ፋኖ አንድነት በሸዋ አካባቢውን ተቆጣጥሮ ማስተዳደሩን መጀመሩን ተከትሎ ብስጭት ውስጥ የወደቀው ኦህዴድ ብልፅግና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት ወደ ከተማዋ እንዲላክ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ከደብረብርሃን መስመር ተነስቶ "ቀይት፤ጉዶ በረት" የሚባሉ አካባቢዎች ለይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦህዴድ ሠራዊት ወደ ሽዋ ሮቢት ከተማ ለመግባት ሲርመሰመስ ተስተውሏል።

የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ጨምሮ ሁሉም የአገር ውስጥ እና የውጭ የሲቪክ ተቋማት እንዲሁም ሚዲያዎች የኦህዴድ ሠራዊት አካባቢውን ከቦ በሶስት ቀናት ውስጥ ካደረሰው የንፁሃን ጭፍጨፋ በባሰ መልኩ ሊፈፅም ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን እንድታውቁልን ጥሪ እናቀርባለን ሲል ህዝባዊ ኃይሉ አስተዋቋል።ድያስፖራው ማህበረሰብም በዲፖሎማሲ እና በፋይናንስ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

"ከዚህ በኋላ የሸዋን ህዝብ የኦህዴድ ሠራዊትም ይሁን የኦህዴድ ብልፅግና መዋቅር በጉልበት ሊገዛ አይችልም፤በቃን፤ነፃነታችንን በክንዳችን አስመልሰናል፤ በኦህዴድ ብልፅግና መዋቅር መገደል፣መፈናቀል፣መራብ እና መጨቆን በቅቶናል፤ሁሉም የአማራ ህዝብ የራሱን ህዝባዊ አስተዳደራዊ መዋቅር ልክ እንደ ሸዋ ህዝብ ይፈጠር"ሲሉ ለተቀረው የአማራ ክፍል አስቸኳይ ጥሪ አቅርበዋል።

በስተመጨረሻ ለኦህዴድ ሠራዊት አባላት የአማራ ፋኖ አንድነት በሸዋ እና የሸዋ ህዝብ እንዲህ ሲል ጥሪ አቅርቧል"...ለወንድም የአማራ እና የደቡብ ተወላጅ የሠራዊቱ አባላት እንዲሁም ለሚመለከተው የሠራዊቱ አባላት በሙሉ ትናንት በነበረ የዕርስ በርስ ጦርነት ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ረግፈዋል፤ከነዚህ መካከል በመቶሽዎች የሚቆጠረው ምስኪኑ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ነው።በየጥሻው ያለቀው ሠራዊት ደም እንኳን ሳይደርቅ፣ሲያጋድሉ የነበሩ አካላት ውስኪያቸውን መራጨት ጀምረዋል፤ዛሬም ምስኪኑ የሠራዊት አባላት ለዐብይ አህመድ ሥልጣን መቆየት ብቻ ሲባል ከተደገሰለት ዳግም ዕልቂት እራሱን ሊጠብቅ ይገባል።በህዝብ ላይ አልተኩስም በማለት ህዝባዊነቱን ሊያስመሰክር ይገባል።እየከዳ ቢወጣ ልንቀበለው ዝግጅት ጨርሰናል"ብሏል።