Get Mystery Box with random crypto!

'የአብይ አህመድ ፋሽስታዊ አገዛዝ አማራን የማጥፋት ዘመቻውን በይፋ አውጇል፤ አማራ! በተደራጀ ሁኔ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

"የአብይ አህመድ ፋሽስታዊ አገዛዝ አማራን የማጥፋት ዘመቻውን በይፋ አውጇል፤ አማራ! በተደራጀ ሁኔታ በአንድነት ቆመህ ህልውናውን አስጠብቅ!"

ዓለምአቀፍ የአማራ ንቅናቄ

የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ሚያዚያ 24/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ከዓለምአቀፍ የአማራ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ:-

የአብይ አህመድ አገዛዝ ይዞት የተነሳውን አማራን የማጥፋት ኦነጋዊ ተልዕኮ ለመፈጸም “የማያዳግም እርምጃ” ያለውን ፋሽስታዊ ጥቃት የአማራው
ንቅናቄ መሠረት በሆነው የአማራ ክልል ሕዝብ ላይ በይፋ አውጇል።

በኢትዮጵያ መንግሥት ስም የሚያዝበትን በሙሉ ኃይል የተደራጀ የአገሪቱን የመከላከያ ሠራዊት አዝምቶ፣ የክልል ልዩ ኃይል ተብለው የታጠቁ የአማራ ወጣቶችን ትጥቅ ሲያስፈታ፣ የፋኖ አባላትን ሲያሳድድና ነቅተው
የሚያነቁና የሚያደራጁ አማራዎችን ሲያፍን ቆይቶ፣ አማራውን ምንም ዓይነት የመከላከል አቅም እንዳይኖረው በማድረግ ለሁለገብ ጥቃት
ለማጋለጥ የጀመረውን ዘመቻ “የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል” በሚለው መዋቅሩ በኩል ገልጿል።

ይህን ጦርነት ያወጀው፣ በቅድሚያ የአገር ህልውና ስጋት ነው ብሎ፣ የአማራውን ልዩ ኃይልና ሕዝባዊ ሠራዊት እንዲሁም ፋኖን ከአገሪቱ
መከላከያ ኃይል ጋር አሰልፎ ሲዋጋው የነበረውን የወያኔን ኃይል፣ ተመልሶ እንዲጠናከር ጊዜ ሰጥቶ፣ በሠላም ስምምነት ስም አማራን የማጥፋት
የጋራ ቃል ኪዳናቸውን ዳግም ባደሱበት፤ እንዲሁም “ኦሮሚያ” በሚሉት ምድር እስከትጥቁ አስገብቶ በሠራዊትና በጦር መሣሪያ እያደረጀ
ባለፉት 5 ዓመታት የአማራን ዘር ሲያስፈጅበት የቆየውን የኦነግን ሠራዊት በዓለም አቀፍ መድረክ በሚተወን “የእርቅ ድርድር” ከወንጀሉ አጽድቶ
በግላጭ የኦነጋዊው ኃይሉ አካል ለማድረግ በሚዘጋጅበት ጊዜ ነው።

ለ27 ዓመታት በደረሰበት በደል የተነሳ በፀረ ወያኔ አቋም ተጀምሮ፣ የወያኔ ወረራ በፈጠረው አስገዳጅ ሁኔታ ተደራጅቶና ታጥቆ ራስን
ወደመከላከል ያመራውን የአማራ ንቅናቄ አብይ አሕመድ ከጅምሩ በስጋት ሲመለከተው ቆይቷል። “ይች ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም” በሚል
ዘይቤ፣ የአማራን ታጥቆ የመመከት አቅም ለማመንመን የሚከተለው የተጋለጠ ብልሃት በአገልጋዩ በብአዴን መንደር ሽብር መፍጠር ነው።

“ገድሎ ማልቀስ” በሚባለው በዚህ ዘዴ ታግዞ አገልጋይ የብአዴን ታማኞቹን በጭካኔ በማስገደል በሚቆጣጠረው የአገሪቱ የብዙኃን መገናኛ በፈጠረው
ሽብር፣ የአማራው ንቅናቄ አካል የሆነውን ወታደራዊ አቅም ለማዳከም አልሞ፣ ትናንት አምባቸው መኮንንና ጓዶቹን ገድሎ ጀነራል አሳምነው ጽጌ
በአማራ ልዩ ኃይል ስም የመለመላቸውን የበቁ የአማራ አዋጊ መኮንኖች በመፍጀት የአማራውን ኃይል የተዋጊነት ብቃት ለማዳከም ሞክሯል።

ዛሬ ደግሞ በሠራዊት ብዛትና በጦር መሣሪያ የደረጀ ጦሩን በመላው የአማራ ክልል አሰማርቶ ፋኖን ሊያሳድድና አማራን ሊፈጅ ዝግጅቱን በጨረሰበት
ጊዜ፣ እንደለመደው ግርማ የሺጥላን አስገድሎ ሁከት በማወጅ ለሠራዊቱ የጭፍጨፋ ትዕዛዙን ሰጥቷል።
በዚህ ዘመቻ ብዙ የአማራ ክልል ከተሞች በአብይ አሕመድ ወታደሮች ተወርረዋል፤ የቤት ለቤት አሰሳ እየተደረገ ሰዎች ይታፈናሉ፤ ይገደላሉ፤
የተፈላጊ ሰዎች ቤተሰብ፣ ሕጻናት፣ ነፍሰጡር ሴቶችና አረጋውያን ሳይቀሩ ታፍነው ይወሰዳሉ፤ ኗሪዎች በነጻነት መዘዋወር የእለት ኑሯቸውን
መምራት አይችሉም።

ይህ ውጥረት እስካሁን ካለፈባቸው አስከፊ ሁኔታዎች ጋር ተዳምሮ አማራውን አማራጭ በማሳጣት ወደመረረ ጦርነት
ሊያስገባው እንደሚችል ይታመናል።

የአማራ ህዝብ ሆይ፣
በህልውናህ ላይ ከመቸውም ጊዜ የከፋ አደጋ አንዣብቧል። ራስን መከላከል ሰጪና ነሺ የሌለበት ተፈጥሯዊ መብት ነው። አያት ቅድም
አያቶቻቸው ደማቸውን አፍስሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው ባወረሷቸው አገር ላይ የወገናቸው መጨፍጨፍ ላስከፋቸውና በነገዳዊው አገዛዝ
ምክንያት የባለአገርነት መብት ማጣትን እምቢ ብለው ለተነሱ ፋኖዎችህ ከለላ መሆን ራስህን ለማዳን የምታደርገው ትንሹ ተግባር ነው።

ትናንት በወያኔ ወረራ እንዳየኸው የቤተሰብህ፣ የመንደርህና የከተማህ ደኅንነት በገዛ ልጆችህ እንጂ አብይ አሕመድ በሚያዘምትብህ ወታደርና ከውስጥህ
በበቀሉ ከሃዲ አገልጋዮች ሊጠበቅ አይችልም።

ስለዚህ፣ ዓለምአቀፍ የአማራ ንቅናቄ፣ መላው አማራ በአንድነት በአብይ አሕመድና በአገልጋዮቹ
ዛቻ እና ማደናገሪያ ሳይረታ፣ በክልሉ የተሰማራው ጦር ለቅቆ እስከሚወጣ እምቢታውን እንዲቀጥልና የሚሳደዱ ልጆቹን እንዲደግፍ እያሳሰበ፣
አማራው ህልውናውን ለማስከበር በሚያደርገው በማናቸውም የትግል ዘርፍ ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ አብሮት የሚቆም መሆኑን ዳግም
ያረጋግጣል።

ህልውናችን በትግላችን!
ዓለምአቀፍ የአማራ ንቅናቄ።