Get Mystery Box with random crypto!

በደብረ ብርሃን ከተማ አለም ዓቀፍ ህግን በጣሰ መልኩ በመጠለያ ካሉ በሽህ የሚቆጠሩ ተፈናቃይ ወገኖ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

በደብረ ብርሃን ከተማ አለም ዓቀፍ ህግን በጣሰ መልኩ በመጠለያ ካሉ በሽህ የሚቆጠሩ ተፈናቃይ ወገኖች በ50 ሜትር ርቀት ላይ ሰፍሮ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ከአካባቢው እንዲነሳ ተጠየቀ፤ በመጠለያ ባሉ ሴቶች ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸሙ አባላት ስለመኖራቸውም የአማራ ማህበር በአሜሪካ አስታውቋል።

የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ሚያዚያ 25/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በደብረ ብርሃን ከተማ አለም ዓቀፍ ህግን በጣሰ መልኩ በመጠለያ ካሉ በሽህ የሚቆጠሩ ተፈናቃይ ወገኖች በ50 ሜትር ርቀት ላይ ሰፍሮ የሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ከአካባቢው እንዲነሳ ተጠይቋል።

በደብረ ብርሃን መጠለያ ባሉ ሴቶች ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸሙ እና ልጃገረዶችን ለወሲባዊ ጥቃት እያስገደዱ ያሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ስለመኖራቸው ማረጋገጡን የአማራ ማህበር በአሜሪካ አስታውቋል።

ከዚህም በተጨማሪ በለጋሽ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ስራ ጣልቃ በመግባትም እርዳታ የሚያገኙበትን ሂደት እያስተጓጎሉ መሆኑ ተገልጧል።

እንደአብነትም ኢንተርናሽናል ሜዲካል ኮርፖስ (IMC) እና
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶቤተ ክርስቲያን የልማት ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በተባሉ ግብረ ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች ላይ የዛቻ ድርጊት እየተፈጸመ ስለመሆኑ ማረጋገጡን ማህበሩ ገልጣል።

በተመሳሳይ በቆቦና አካባቢዋ የገባው አብይ አህመድ ያሰማራው ጦር ሚያዝያ 22/2015 ቤት ለቤት እየዞረ በፈተሸበት ወቅት ሴቶችን አስገድዶ የደፈረ ስለመኖሩ አማራ ሚዲያ ኔት ወርክ የተባለ የዩቱብ ሚዲያ ያጋራው መረጃ አመልክቷል።

ከሚያዚያ 19/ 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቆቦና አካባቢዋ የሚገኙ ዋና ዋና መንገዶችን በመዝጋት ቤት ለቤት በማሰስ ፋኖ ምሬ ወዳጆ ያለበትን ጠቁሙ እንዲሁም የደበቃችሁትን መሳሪያ አዉጡ በማለት ህዝቡን እያሸበሩት እንደሆነ ተገልጧል።

በእነዚህ የመንግስት ሀይሎች እድሜዋ በግምት ከ20 አስከ 25 የሚሆናት ከቆቦ ወጣ ብላ የምትገኝ የገጠር ቀበሌ ነዋሪ የሆነች ታዳጊ ወጣትን 3 አባላት የተደበቀ መሳሪያ አለ አዉጭ በማለት ቢጠይቋትም እሷም ምንም መሳሪያ እንደሌለ ከፈለጉ ገብተዉ እንዲፈትሹ በመፍቀዷ እኝህ ሀይሎች ቤቷን በመፈተሽ ምንም አይነት መሳሪያ ማግኜት አልቻሉም በመጨረሻም በሚያሳዝን ሁኔታ በንዴት በመሳሪያ አንገራግረዉ እንደደፈሯት እንዲሁም የደፈሯት 3ቱም ከአማረኛ ቋንቋ ዉጭ ሌላ የማታዉቀዉ ቋንቋ ጭምር ሲነጋገሩ እንደነበር መናገሯ ተገልጧል።

ተጎጅዋ ወጣት በዚህ ሰዓት በአስቸኳይ ህክምና ማግኜት እንዳለባት ነገር ግን በመንግስት ሀይሎች ምክንያት በአካባቢዉ ሙሉ ለሙሉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ስለቆመ ተጎጅዋ የህክምና እርዳታ ማግኜት እንዳልቻለች ተዘግቧል።