Get Mystery Box with random crypto!

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

የቴሌግራም ቻናል አርማ yeilmkazna — ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል
የቴሌግራም ቻናል አርማ yeilmkazna — ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል
የሰርጥ አድራሻ: @yeilmkazna
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.91K
የሰርጥ መግለጫ

በየቀኑ የተለያዩ ኢስላማዊ እውቀቶችን ይሸምቱበታል። ይቀላለቀሉ፣ ለሌሎችም ያሰራጩ።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-04-15 19:38:57
  ዘካተል ፊጥር

ዘካተል ፊጥርን ተቀብለን ለተገቢው ሰው ሸሪዓው ባዘዘው ወቅት እናደርሳለን!

ነብያዊ ሐዲስ: "በእያንዳንዱ የሙስሊም ነብስ ላይ በረመዷን ዘካተልፊጥር ማውጣት ተደንግጓል።"

ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት ደሴ ቅርንጫፍ በረመዳን ፆም መጨረሻ በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ማውጣት ያለበትም ዘካተል ፊጥር በማስተባበር ላይ ይገኛል።

በመሆኑም በዘንድሮው ለአንድ ሰው 2.5 ኪ.ግ የፉርኖ ዱቄት  ሒሳብ 187ብር ከ50ሳ የተተመነ ሲሆን ይህንን ለእርሶ ወይም በቤተሰብዎ አባላት ቁጥር ልክ አባዝተው በመክፈል ግዴታዎን ለመወጣት ቢፈልጉ በሚከተሉት የባንክ አካውንቶች ብሩን ሲያስገቡልን እኛ ደግሞ ዱቄቱን ገዝተን ለሚስኪኖች በአማና እናደርሳለን።

ንግድ ባንክ : 1000463144749
ሒጅራ ባንክ : 10011556600001
ዘምዘም ባንክ : 0005280310301
አዋሽ ባንክ: 0140715733400
አቢሲኒያ ባንክ: 93542223

"ዘካተል ፊጥር ወደ አሏህ መቃረቢያ ኢባዳ እንጂ ስጦታ አይደለም!"

ለበለጠ መረጃ
09 27 47 87 87
09 19 96 49 89


ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት ደሴ ቅርንጫፍ


Telegram: https://t.me/merkezunadessie
543 viewsMohammed Jud, 16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 11:28:33የረመዷን ቲላዋ ግብዣ•​

በየቀኑ 1 ጁዝእበ30 ቃሪኦች

ረመዷን 23 []  ጁዝእ : 23

ቃሪእ:  ዓብዱልባሲጥ ዓብዱሶመድ

ደቂቃ : 56:50

በፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል ተመዝግቦ ለመቅራት ያመልክቱ
@FurqanOnlineQuran
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
https://t.me/furqan_school
339 viewsFurqan Online Quran, 08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 22:40:44 ገባ ገባ በሉ።

የቁርኣን ሀለቃ ፕሮግራሙ

አቀራራችሁን በቀጥታ ማሰማት የምትፈልጉ ሁሉ ሊጀመር ነው። አቀራርችሁን ማስተካከል
ማሰማት የምትፈልጉ ሁሉ

ከምሽቱ 5:00 - 6:00

ወደ ሀለቃው መግቢያ ሊንክ
https://t.me/furqan_school?videochat=dd7c8d549442fbff2c

┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል
https://t.me/furqan_school
337 viewsFurqan Online Quran, 19:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 16:24:48 ቁርኣንን የመሐፈዝ ትሩፋት
=====================
ክፍል ሁለት 

የዐውኑል መዕቡድ (ሸርሕ አቢዳዉድ) ኪታብ ባለቤት የሆኑት ሸይኽ ሙሐመድ አሽረፍ ኢብን አሚር ኢብን ዐሊይ ኢብን ሐይደር "ከዚህ ሐዲስ እንደምንረዳው ይህን ክብር የአላህን ቃል የሐፈዙት እና አሳምረው የሸመደዱት እንጂ አያገኙትም።" ብለዋል። [ዐውኑል መዕቡድ፡4/237]

"በቁርኣን ማሂር የሆነ ግለሰብ በአኺራ 'ሰፈረቲ ኪራሚል በረራ' ከተባሉት መላኢካዎች ጋር ነው።" [አልቡኻሪ፡4937፣ሙስሊም፡798]

ኢማሙ ነወዊይ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦

"'ማሂር' ማለት ሒፍዙ እጅግ ያማረ እና ባማረ መልኩ ቁርኣንን የሸመደደ ነው።" [ሸርሑ ሙስሊም፡6/85]

"በሁለት ነገሮች ቅናት ይፈቀዳል። አላህ ቁርኣንን እንዲሐፍዝ ረድቶት በሱ ቀንና ለሊት ሰላት የሚቆምበት በሆነ ሰው...." [አልቡኻሪ፡7529፣ ሙስሊም፡815]

"ፆም እና ቁርኣን በመጨረሻው ቀን አማላጅ ሆነው ይመጣሉ። ፆሙ ጌታዬ ሆይ! በቀኑ ክፍለጊዜ ከምግብ እና ከተለያዩ ስሜቶች ከልክዬዋለሁ እባክህ ይቅር በለው ይለዋል። ቁርኣኑም አምላኬ ሆይ! እኔም በለሊቱ ክፍለጊዜ ከእንቅልፍ ከልክዬው ላንተ እንዲቆም አድርጌዋለሁ እባክህ ማረው ይለዋል።" ብለዋል። [አሕመድ ጠበራኒና ሓኪም ዘግበውታል] ሸይኹል አልባኒ [ሰሒሑል ጃሚዕ፡3882] ላይ ሰሒሕ ብለውታል።

ሸይኹል አልባኒ እንዲህ ይላሉ፦
"ቁርኣን የሐፈዘ ሰው ሲባል የአላህን ፊት ፈልጎ የሐፈዘ ነው። የሰዎችን ክብር እንዲሁም ገንዘብና ጥቅማጥቅም የፈለገ እንደሆነ ከከሳሪዎች ነው።" [ሲለሲለቱ አስሰሒሓህ፡5/284

ጥቆም :  : በኦንላይን ቁርኣን ለመማር በዚህ ይመዝገቡ
@FurqanOnlineQuran
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
ጆይን :   ሼር  ፣ ሼር ፣ ሼር
بـــارك الـلــه  فـــــيــــــكـــم ، وجــزاكـــم اللـه
https://t.me/furqan_school
https://t.me/furqan_school
482 viewsFurqan Online Quran, 13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 14:03:18 ★ ሰለፎችና ቁርኣን ~

ክፍል : 1

※ በዚህ ክፍል የምንመለከተው ቁርኣን (የአላህ ንግግር) ሰለፎች ዘንድ ያለውን ትልቅና የተከበረ ቦታ ይሆናል።

~ ኸባብ ኢብኑል አረት እንዲህ ይላሉ : "በቻልከው ሁሉ ለመቃረብ ጥረት አድርግ... ከንግግሩ (ቁርአን) በላይ እሱ ዘንድ በሆነ ነገር ልትቃረብ ፈፅሞ አትችልም።"

~ ነያር ኢብኑ ሙከረም አስሰለሚይ እንዲህ ይላሉ:      የሚለው አንቀፅ በወረደ ጊዜ አቡበክር "የጌታዬ ንግግር! የጌታዬ ንግግር! " እያለ ይወጣ ነበር። አስማእ ቢንት አቡበክርም ቁርኣን ሲነበብ ስትሰማ "የጌታዬ ንግግር! የጌታዬ ቃል! ትል ነበር።

~ አቡ አብዱሮህማን አስሰለሚይ እንዲህ ብለዋል :  "ቁርኣን ከሌሎች ንግግሮች አኳያ ያለው ብልጫ ጌታ ከፍጡራን ጋር እንዳለው ብልጫ ያክል ነው።

ይቀጥላል ~ ~ ~

ጥቆም : 
በኦንላይን ቁርኣን ለመማር በዚህ ይመዝገቡ
@FurqanOnlineQuran
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
ጆይን :   ሼር  ፣ ሼር ፣ ሼር
بـــارك الـلــه  فـــــيــــــكـــم ، وجــزاكـــم اللـه
https://t.me/furqan_school
https://t.me/furqan_school
66 viewsFurqan Online Quran, 11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 09:31:09የረመዷን ቲላዋ ግብዣ•​

በየቀኑ 1 ጁዝእበ30 ቃሪኦች

ረመዷን 22 []  ጁዝእ : 22

ቃሪእ:  ተውፊቅ አስሷኢግ

ደቂቃ : 52:38

በፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል ተመዝግቦ ለመቅራት ያመልክቱ
@FurqanOnlineQuran
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
https://t.me/furqan_school
185 viewsFurqan Online Quran, 06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 11:08:04
#ቁርአንን_አስተካክሎ_መቅራት

— የአሏህ ቃል ከሰባት ሰማይ በላይ የወረደውን የፈጣሪያችንን ንግግር በትክክል በወረደበት መልኩ መቅራት ነው የሚፈለገው።

★ይህንን ታላቅ የአላህን ቃል በትክክል ለመቅራት ደግሞ በመጀመሪያ ላይ የተለያዩ ቃዒዳዎችን ትማራለክ ከተጅዊድ ጭምር።

ይህንን ቃዒዳህ የምትማረው ወደ ላይ ስትቀራ የፊደላትን #መኻሪጅ እና #ሲፋት ለማወቅ እና ለማስተካከል ትልቅ ድርሻ ስለለው ነው።

አብዘሀኛው ህዝባችን ቁርአንን በትክክል መቅራት አይችልም ለተጅዊድ ያላቸው ቦታ በጣም ዝቅተኛ ነውና።

አብዘሀኛው ህዝብ የሚፈልገው እንደምንም ብሎ ማኽተም ብቻ እንጅ በትክክል መቀራቱን አይደለም ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም።

ቁርአን ማኽተሙ ብቻ ያለ ተጅዊድ ያለ ማስተካከል ጥቅም የለውም ወንድም እህቶች ስለዝህ በተጅዊድ ላይ ትኩረት እንስጥ።

ከፊሎች ደግሞ የተጅዊድን ት/ት የሚንቁም አሉ ግን ይዓጅብካል ስለ አንድ አሕካም ወይንም መኻሪጅ ብትጠይቀው ምንም የማይመልስልክ የተጅዊድን ት/ት ሲያጣጥልብክ ትመለከታለክ ።

ምን ማጣጣል ብቻ ይሄ ዝም ብሎ ጊዜን መጨረስ ነው ይልካልም አሏሁሙስተዓን ተጅዊድን መማርኮ #ፈርዱል_ኪፋያ ነው ፣ በሁሉም ቃሪእ ላይ ደግሞ #ፈርዱል_ዓይን ነው ይህንን አያውቁምን

እናም ወንድም እህቶች ይህንን የአሏህን ቃል በትክክል  ልንቀራ ዘንድ ሰበብ የሚሆነን እነዚህ ቃዒዳዎች የተጅዊድ ት/ቶች ስለሆኑ በጣም ትኩረት ማድረግ ይኖርብናል ።

አሏህ የሱን ቃል በትክክል ከሚያነቡትና ከሚተገብሩት ያድርገን...

◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
ጆይን :   ሼር  ፣ ሼር ፣ ሼር
         بـــارك الـلــه  فـــــيــــــكـــم ...
https://t.me/furqan_school
https://t.me/furqan_school
465 viewsFurqan Online Quran, 08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 05:43:10የረመዷን ቲላዋ ግብዣ•​

በየቀኑ 1 ጁዝእበ30 ቃሪኦች

ረመዷን 20 []  ጁዝእ : 20

ቃሪእ:  ናሲር አልቀጧሚ

ደቂቃ : 51:17

በፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል ተመዝግቦ ለመቅራት ያመልክቱ
@FurqanOnlineQuran
⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩⇩
https://t.me/furqan_school
264 viewsFurqan Online Quran, 02:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 22:07:14 ↝የቀልቀላ ሓርፎች
ـ↜ق↝ـ
ـ↜ط↝ـ
ـ↜ب↝ـ
ـ↜ج↝ـ
ـ↜د↝ـ
ሲሆኑ በአጭሩ «قطبجد» ተብለው ይጠራሉ።

~ ቀልቀላ ማለት : ከነዚህ ፊደላት መካከል አንዱ ፊደል ስኩን ሆኖ ስማገኘው ወይም የቃሉ መጨረሻ ላይ ሆኖ በስኩን ስናቆም ከሌሎች ፊደላት በተሻለ መልኩ ነጠር አድርጎ (ጎላ አድርጎ) ማንበብ ማለት ነው።

ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
ጆይን :   ሼር  ፣ ሼር ፣ ሼር
                  بـــارك الـلــه  فـــــيــــــكـــم
https://t.me/furqan_school
https://t.me/furqan_school
436 viewsFurqan Online Quran, 19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 14:31:26 ↝ምን ጊዜም የሚወፍሩ ፊደላቶች ( የኢስቲዕላእ ባህሪ) ያላቹ ፊደላቶች ሰባት ናቸው እነሱም:-
١ـ↜خ↝
٢ــ↜ص↝
٣ــ↜ض↝
٤ــ↜غ↝
٥ــ↜ط↝
٦ــ↜ق↝
٧ــ↜ظ↝

↣ከነዚህ ውስጥ ጥንካሬ ያላቸው ❨የኢጥባቅ ባሕሪ ያላቸው❩ ፊደላቶች ከሌሎቹ የበለጠ በመወፈር ደረጃ ይበልጣሉ።ጥንካሬ ያላቸው  የኢጥባቅ በሕሪ ያላቸው ፊደላቶች አራት ናቸው። እነሱም :«" ط" ض" ص" ظ» ሲሆኑ ቀሪዎቹ ❝ق" غ" خ❞ከነዚህ በመቀጠል ይሰለፍሉ።

ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
ጆይን :   ሼር  ፣ ሼር ፣ ሼር
                  بـــارك الـلــه  فـــــيــــــكـــم
https://t.me/furqan_school
https://t.me/furqan_school
563 viewsFurqan Online Quran, 11:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ