★ ሰለፎችና ቁርኣን ~ ክፍል : 1 ※ በዚህ ክፍል የምንመለከተው ቁርኣን (የአላህ ንግግር) ሰለፎች ዘንድ ያለውን ትልቅና የተከበረ ቦታ ይሆናል። ~ ኸባብ ኢብኑል አረት እንዲህ ይላሉ : "በቻልከው ሁሉ ለመቃረብ ጥረት አድርግ... ከንግግሩ (ቁርአን) በላይ እሱ ዘንድ በሆነ ነገር ልትቃረብ ፈፅሞ አትችልም።" ~ ነያር ኢብኑ ሙከረም አስሰለሚይ እንዲህ ይላሉ: የሚለው አንቀፅ በወረደ ጊዜ አቡበክር "የጌታዬ ንግግር! የጌታዬ ንግግር! " እያለ ይወጣ ነበር። አስማእ ቢንት አቡበክርም ቁርኣን ሲነበብ ስትሰማ "የጌታዬ ንግግር! የጌታዬ ቃል! ትል ነበር። ~ አቡ አብዱሮህማን አስሰለሚይ እንዲህ ብለዋል : "ቁርኣን ከሌሎች ንግግሮች አኳያ ያለው ብልጫ ጌታ ከፍጡራን ጋር እንዳለው ብልጫ ያክል ነው። ይቀጥላል ~ ~ ~ ጥቆም : በኦንላይን ቁርኣን ለመማር በዚህ ይመዝገቡ @FurqanOnlineQuran ◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈ ጆይን : ሼር ፣ ሼር ፣ ሼር بـــارك الـلــه فـــــيــــــكـــم ، وجــزاكـــم اللـه https://t.me/furqan_school https://t.me/furqan_school 66 viewsFurqan Online Quran, 11:03