Get Mystery Box with random crypto!

ቁርኣንን የመሐፈዝ ትሩፋት ===================== ክፍል ሁለት  የዐውኑል መዕቡ | ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

ቁርኣንን የመሐፈዝ ትሩፋት
=====================
ክፍል ሁለት 

የዐውኑል መዕቡድ (ሸርሕ አቢዳዉድ) ኪታብ ባለቤት የሆኑት ሸይኽ ሙሐመድ አሽረፍ ኢብን አሚር ኢብን ዐሊይ ኢብን ሐይደር "ከዚህ ሐዲስ እንደምንረዳው ይህን ክብር የአላህን ቃል የሐፈዙት እና አሳምረው የሸመደዱት እንጂ አያገኙትም።" ብለዋል። [ዐውኑል መዕቡድ፡4/237]

"በቁርኣን ማሂር የሆነ ግለሰብ በአኺራ 'ሰፈረቲ ኪራሚል በረራ' ከተባሉት መላኢካዎች ጋር ነው።" [አልቡኻሪ፡4937፣ሙስሊም፡798]

ኢማሙ ነወዊይ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦

"'ማሂር' ማለት ሒፍዙ እጅግ ያማረ እና ባማረ መልኩ ቁርኣንን የሸመደደ ነው።" [ሸርሑ ሙስሊም፡6/85]

"በሁለት ነገሮች ቅናት ይፈቀዳል። አላህ ቁርኣንን እንዲሐፍዝ ረድቶት በሱ ቀንና ለሊት ሰላት የሚቆምበት በሆነ ሰው...." [አልቡኻሪ፡7529፣ ሙስሊም፡815]

"ፆም እና ቁርኣን በመጨረሻው ቀን አማላጅ ሆነው ይመጣሉ። ፆሙ ጌታዬ ሆይ! በቀኑ ክፍለጊዜ ከምግብ እና ከተለያዩ ስሜቶች ከልክዬዋለሁ እባክህ ይቅር በለው ይለዋል። ቁርኣኑም አምላኬ ሆይ! እኔም በለሊቱ ክፍለጊዜ ከእንቅልፍ ከልክዬው ላንተ እንዲቆም አድርጌዋለሁ እባክህ ማረው ይለዋል።" ብለዋል። [አሕመድ ጠበራኒና ሓኪም ዘግበውታል] ሸይኹል አልባኒ [ሰሒሑል ጃሚዕ፡3882] ላይ ሰሒሕ ብለውታል።

ሸይኹል አልባኒ እንዲህ ይላሉ፦
"ቁርኣን የሐፈዘ ሰው ሲባል የአላህን ፊት ፈልጎ የሐፈዘ ነው። የሰዎችን ክብር እንዲሁም ገንዘብና ጥቅማጥቅም የፈለገ እንደሆነ ከከሳሪዎች ነው።" [ሲለሲለቱ አስሰሒሓህ፡5/284

ጥቆም :  : በኦንላይን ቁርኣን ለመማር በዚህ ይመዝገቡ
@FurqanOnlineQuran
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
ጆይን :   ሼር  ፣ ሼር ፣ ሼር
بـــارك الـلــه  فـــــيــــــكـــم ، وجــزاكـــم اللـه
https://t.me/furqan_school
https://t.me/furqan_school