2023-04-05 15:07:15
9ኙ.ሚስጥሮች.tt
ቁርኣንን ለመሓፈዝ 9 ሚስጥሮች 1ኛው ሚስጥር : ለቁርኣን ሒፍዝ ከፍተኛ የሆነ ጉጉት ፣ ፍላጎትና ተነሳሽነት ሊኖርህ ይገባል ፣
2ኛው ሚስጥር : ኢኽላስ (ለአሏህ ብቻ ብሎ መሐፈዝና) አሏህ ቁርኣን ሂፍዝን እንዲያገራልህ ሁሌም ዱዓ ማድረግ ፣
3ኛው ሚስጥር : ሀላፊነቱን ራስህ ውሰድ ፣ ምክንያት አታብዙ (እድሜህ ቢገፋ ፣ የማስታወስ አቅምህ ቢያንስ...)
4ኛው ሚስጥር : በአቅምህ ልክ ሀፍዝ እንዲሁም በአንድ ሙስሓፍ (አንድ ተመሳሳይ ገፅ ያለው የቁርኣን እትም) ብቻ ተጠቀም።
5ኛው ሚስጥር : ለሒፍዝ ተስማሚማ ተዛማች ጊዜና ቦታ ምረጥ (ስሁርና ፈጅር ወቅቶች የተሻሉ ሲሆኑ ማታ አይመከርም ፣ ቦታም ፀጥታ ያለበት ብዙ ቀልብን ሳቢ የሆኑ ነገራቶች የሌሉበት ቢሆን ይመከራል)
6ኛው ሚስጥር : 3ቱንም ዋና የሒፍዝ ሞተሮችን አንቃቸው - አይንህን ጆሮህንና ልብህን ክፍትና ንቁ አድርገህ መሓፈዝ ይኖርብሀል ፣ አንድኛቸውንም ከተውካቸው መሀፈዝህ ትርጉም አልባ ይሆናል።
7ኛው ሚስጥር : በተደጋጋሚ ማጥናትና ሙራጀዓ ማድረግ አትዘንጋ ፣ (ቀኑን ሙሉ እና ከመኝታ በፊት በኦድዬ በማዳመጥ ፣ እንዲሁም በየ ትርፍ ሶላቶች ላይ በመቅራት ሙራጀዓ ላይ ተጠባከር)
8ኛው ሚስጥር : ቋሚማ ወጥ የሆነ ፕሮግራም ይኑርህ ፣ በየቀኑ ምን ያክል ተሀፍዛለህ? ምን ያክሉን ሙራጀኣ ታደርጋለህ? መቼ ሂፍዝ ትጨርሳለህ? ወጥ የሆነና ቋሚ ፕሮግራምና እቅድ ይኑርህ
9ኛው ሚስጥር : ከወንጀል ራስህን አርቅ እንዲሁም አሏህ እንዲያገራልህ ሁሌም ዱዓ በማድረግ ላይ አትስነፍ።
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል
በOnline ተመዝግቦ ቁርኣን ለመማር በዚህ ሊንክ ያመልክቱ
@FurqanOnlineQuran
ስለ ቁርኣንና የመሳሰሉ ፅሁፎችን ፣ ምስሎችንና ቪዲዬዎችን ለመከታተል ይቀላቀሉን ፣ ለሌሎችም በማካፈል የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!!
https://t.me/furqan_school
335 viewsFurqan Online Quran, 12:07