Get Mystery Box with random crypto!

ሰለፎችና ቁርአን በረመዷን ውስጥ ረመዷን ውስጥ ቀደምት የዲን ሊቃውንቶቻች | ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

ሰለፎችና ቁርአን በረመዷን ውስጥ


ረመዷን ውስጥ ቀደምት የዲን ሊቃውንቶቻችን ትኩረት ከሚሰጧቸውና በብዛት ይፈፅሟቸው ከነበሩ ታላላቅ ኢባዳዎች ውስጥ አንዱና ዋናው በሶላትም ሆነ ከሶላት ውጪ ቁርአንን አብዝቶ መቅራትን ነበር። እነዚህ ቀደምቶቻችንና ሞዴሎቻችን ከቁርአን ጋር የነበራቸው ግኑኝነትና ቁርኝነት እጅግኑ የገዘፈና የጠበቀ ነበር። ከዚህም የተነሳ ቁርአንን በአግባቡ ቀርተው፣ ተረድተው፣ ተግብረውና ህይወታቸው ሙሉ ለሙሉ ከቁርአን ጋር በማቆራኘትና በማገናኘት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ፈፅመው ወደ ማይቀረው ሀገር ተሻግረዋል። ይህንን እውነታ ከሚያሳዩን ነገሮች ውስጥ፦

ኢማሙ ዙህርይ (رحمه الله تعالى)

ይህ ታላቅ ኢማም ረመዷን ውስጥ በዋናነት ትልቅ ቦታ ሊሰጠው የሚገባ ኢባዳ አስመልክቶ እንዲህ አለ፦【ረመዷን ማለት ቁርአንን በብዛት የማንበብያና ምስኪኖችን የመመገቢያ ወር ብቻ ነው።】ይል ነበር።

ኢማሙ ማሊክ (رحمه الله تعالى)

ረመዷንን በቁርአን ከሚያሳልፋ ኢማሞች ውስጥ አንዱ ናቸው። ከዚህም የተነሳ ልክ ረመዷን ሲቃረብ፦ 【የሀዲስ ቂርአትና የኢልም ሀለቃቸውን በማቆም ቁርአንን ከሙስሀፋ (ከመፅሀፋ) ይዘው ወደ መቅራት ይዛወሩ እንደነበረ ተወስቷል።】

ኢማሙ ቀታዳ (رحمه الله تعالى)

ረመዷን ውስጥም ሆነ ከረመዷን ውጪ ቁርአንን በብዛት ከሚያነቡት ተርታ የሚመደቡ ታላቅ ኢማም ናቸው። 【ከዚህም የተነሳ በሁሉም ወራቶች ቁርአንን በየ ሰባት ሰባት ቀን ያኸትሙ ነበር። ረመዷን ውስጥ ደሞ በየ ሶስት ሶስት ቀኑ ያኸትሙ ነበረ። የረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ሌሊቶች ላይ ደሞ በየቀኑ ቁርአንን ያኸትሙ ነበር።

ኢብራሂም አንነኸእዩ (رحمه الله تعالى)

ይህ ታላቅ ኢማም፦ 【በረመዷን ውስጥ በየ ሶስት ሶስት ቀን ቁርአንን ያኸትም ነበር። አሽረል አዋኺር (የረመዷን የመጨረሻ አስርት ቀናት) ውስጥ በየ ሁለት ሁለት ቀን ያኸትም ነበር።】

ኢማም አል አስወድ (رحمه الله تعالى)

ይህ ታላቅ አሊም በአመቱ ውስጥ ባሉ ወራቶች ባጠቃላይ፦ 【በየ ሁለት ሁለት ቀን ቁርአንን ያኸትም ነበር።】

لطائف المعارف (ص:٣١٨)

እኛስ?

𝐓𝐞« https://t.me/furqan_school