2023-04-16 14:13:06
ሯእ (ر) ፊደል መቼ ነው የምትወፍረውና የምትቀጥነው?
#ክፍል_አንድ
አብዛሀኛዎቻችን ቁርአን በምንቀራ ሰአት የማይፈወፍረውን እናስወፍራለን የማይቀጥነውን እናቀጥናለን በተለይ ደግሞ በ (ራ) ፣በኢኽፋእ ፣በኢድጋም ፣ በላሙል ጀላላህ ላይ
ከነዝህ ውስጥ ራ #አራት ሑክም ይኖራታል
1 #ራኡን መፍቱሕ(ፈትሐ የሆነችው ራ)
2 #ራኡን መክሱር (ከስራ የሆነችው ራ)
3 #ራኡን መድሙም(ደማ የሆነችው ራ)
4 #ራኡን አሳኪናህ (ስኩን የሆነችው ራ)
#ራኡን_መፍቱሕ_እሷ_ፈትሀ_ስትሆን
#ራ ፈትሐ ስትሆን በየትኛውም ቦታ ትሁን መጨረሻ ላይ ትሁን መጀመሪያ ላይ መሀከል ላይም ብትሆን ሙሉ በሙሉ (#ተፍኺም) ትወፍራለች
ለምሳሌ {{ ألم تَرَ }}
በዝህ ቦታ ላይ #ራ ፈትሀ ናት ወፍራምም ናት
#ራኡን_መክሱር_እሷ_ከስራ_ስትሆን
#ራ ከስራ ከሆነች በየትኛውም ቦታ ብትሆን የሷ ሑክም ሙሉ በሙሉ #ተርቂቅ (መቅጠን) ነው።
ለምሳሌ {{ ومن شرِّ غاسقً }}
#ራ እዝህ ላይ ቀጭን ናት የምትሆነው
#ራኡን_መድሙም_ራ_ዶማ_ስትሆን
በዝህም ጊዜ እንደ ራኡን መፍቱሕ ትወፍራለች ማለትም #ተፍኺም ትሆናለች ማለት ነው በየትኛውም ቦታ ብትሆን ።
ለምሳሌ፦ {{ إنَّ قارُون }}
#ራ በዝህ ቦታ ላይ ዶማ ናት ሑክሟም ወፍራምነት #ተፍኺም ነው ።
#ራኡን_አሳኪናህ_ራ_ሱኩን_ስትሆን
#ራ ሱኩን ስትሆን ከበስተፊትለፊቷ ባለው ፊደል ሀረካ ላይ ትንጠለጠላለች ።
ከበፊቷ ያለው ፊደል ሀረካው ፈትሀ ወይም ዶማ ከሆነ ሙሉ በሙሉ ትወፍራለች
ለምሳሌ ከበፊቷ ፈትሀ ሲመጣ ፦
{{ وقَرْنَ في بيوتكن}}
ከፊቷ ዶማ ሲመጣ ደግሞ ፦
{{ أُرْسِلَ }}
እነዝህን ምሳሌዎች መመልከት ይቻላል እንደ ናሙና ያክል
#ራ ከፊቷ ያለው ፊደል ሀረካው ከስራ ከሆነ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ትቀጥናለች ።
እዝህ ላይ ማስገንዘቢያ ፦ #ራ ስኩን ሁና ከሷ ኋላ ያለው ፊደል #የእስቲዕላእ ፊደል ከሆነ ፊደሉ ከስራ ቢሆንም እሷ ትወፍራለች ።
ከፊቷ ከስራ ሲመጣ ለምሳሌ ፦
{{ فِرْعَوْنَ }}
#ራ ሱኩን ሁና ከኋላዋ #የኢስቲዕላእ ፊደል ሲመጣባት
{{ قِرْطاسٍ }} {{ مِرْصاَد }}
በነዝህ ሰአት #ራ ትወፍራለች ሙሉ
በሙሉ እሷን ማቅጠን ይጠላል
#ማስገንዘቢያ፦ #ራኡን_ስኩን #ወቅፍ ላይ ከመጣች ራሷን የቻለ ሀረካ ቢኖራትም ከፊቷ ባለው የፊደሉ ሀረካ ላይ ትመረኮዛለች። ፈትሀና ዶማ ከሆና #ትወፍራለች። ከስራ ከሆነ ደግሞ ትቀጥናለች
ለምሳሌ በፈትሀ ስትመጣ ፦
{{ ونشق القَمَر }}
በዶማ ስትመጣ
{{ وإلی الله ترجعو الأُمُور }}
በከስራ ስትመጣ
{{ مُدَّكِرْ }} {{ مُنْقَعِر }}
ይቀጥላል ኢንሻ አላህ። ሼር እናድርግ ባረከሏሁ ፊኩም
አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን
ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
ጆይን : ሼር ፣ ሼር ፣ ሼር
بـــارك الـلــه فـــــيــــــكـــم
https://t.me/furqan_school
https://t.me/furqan_school
431 viewsFurqan Online Quran, 11:13