Get Mystery Box with random crypto!

ቁርኣንን የመሐፈዝ ትሩፋት ===================== ክፍል አንድ በአላህ ስም እጅግ | ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

ቁርኣንን የመሐፈዝ ትሩፋት
=====================
ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። እንግዲህ ቁርኣን የታላቁ አምላካችን የተከበረ ቃል እንደሆነ እኛ ሙስሊሞች እናምናለን። በውስጡ ከጫፍ እስከ ጫፍ ስህተትን ብንፈልግም ልናገኝ እንደማንችልና ከስህተት ሙሉ በሙሉ የጠራ አስደናቂ መፅሐፍ ስለመሆኑም ያለጥርጥር እንቀበላለን። "ታዲያ ይህን ተአምረኛ መፅሐፍ መሐፈዝ (በቃል መሸምደድ) ትሩፋቱ ምን ይሆን¿" የሚለውን እንመልከት።

1)ቁርኣንን የመሐፈዝ ትሩፋት
የክብር እና የልእልና ባለቤት የሆነው አላህ በክቡር ቃሉ እንዲህ ይላል፦

(بَلْ هُوَ آيَاتٌ بَيِّنَاتٌ فِي صُدُورِ الَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ ۚ وَمَا يَجْحَدُ بِآيَاتِنَا إِلَّا الظَّالِمُونَ) [العنكبوت:٤٩]

"አይደለም እርሱ (ቁርኣን) በእነዚያ ዕውቀትን በተሰጡት ሰዎች ልቦች ውስጥ (የጠለቀ) ግልጾች አንቀጾች ነው፡፡ በአንቀጾቻችንም በዳዮቹ እንጂ ሌላው አይክድም፡፡" [አልዐንከቡት፡49]

በዚህች አንቀፅ አላህ ቁርኣንን የሐፈዙ ሰዎችን እውቀትን የተሰጡት ብሎ እንዳወደሳቸው መመልከት እንችላለን።

መልዕክተኛው (ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም) በጣፋጭ አንደበታቸው የሚከተሉትን ሐዲሶች ተናግረዋል፦

"ለአላህ ከሰዎች መካከል ቤተሰብ አሉት። እነማን ናቸው ተብለው ሲጠየቁ የቁርኣን ባልተቤቶች ለአላህ የተነጠሉ ቤተሰቦች ናቸው።" [ሱነን ኢብኑማጃህ፡215] አልባኒ [ሰሒሑል ጃሚዕ፡2165] ላይ ሰሒሕ ብለውታል።

"የሸበተ ሙስሊምን፣ ቁርኣንን የሐፈዘን ሰው፣ ፍትሀዊ የስልጣን ባለቤትን ድንበር ሳያልፉ ማክበር አላህን ከማክበር ነው።" [ሱነን አቢዳዉድ፡4843] ሸይኹል አልባኒ [ሰሒሑል ጃሚዕ፡2199] ላይ ሰሒሕ ብለውታል።

"ሰዎችን በኢማምነት ሊመራ የሚችለው በቁርኣን ሒፍዝ በላጫቸው ነው።" [ሰሒሕ ሙስሊም፡673]

"ለቁርኣን ባልተቤት በመጨረሻው ቀን 'አንብብ፣ አስተንትን፣ አሳምረህም ቅራ ያንተ ማረፊያ መጨረሻ ላይ በምትቀራት አንቀፅ ይሆናል' ይባላል።" [ሱነን አቢዳዉድ፡1464] ሸይኹል አልባኒም ሰሒሕነቱን አረጋግጠዋል። [ሰሒሑል ጃሚዕ፡8122]

ጥቆም : 
በኦንላይን ቁርኣን ለመማር በዚህ ይመዝገቡ
@FurqanOnlineQuran
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
ጆይን :   ሼር  ፣ ሼር ፣ ሼር
بـــارك الـلــه  فـــــيــــــكـــم ، وجــزاكـــم اللـه
https://t.me/furqan_school
https://t.me/furqan_school