ሯእ (ر) ፊደል መቼ ነው የምትወፍረውና የምትቀጥነው? #ክፍል_አንድ አብዛሀኛዎቻችን ቁርአን በምንቀራ ሰአት የማይፈወፍረውን እናስወፍራለን የማይቀጥነውን እናቀጥናለን በተለይ ደግሞ በ (ራ) ፣በኢኽፋእ ፣በኢድጋም ፣ በላሙል ጀላላህ ላይ ከነዝህ ውስጥ ራ #አራት ሑክም ይኖራታል 1 #ራኡን መፍቱሕ(ፈትሐ የሆነችው ራ) 2 #ራኡን መክሱር (ከስራ የሆነችው ራ) 3 #ራኡን መድሙም(ደማ የሆነችው ራ) 4 #ራኡን አሳኪናህ (ስኩን የሆነችው ራ) #ራኡን_መፍቱሕ_እሷ_ፈትሀ_ስትሆን #ራ ፈትሐ ስትሆን በየትኛውም ቦታ ትሁን መጨረሻ ላይ ትሁን መጀመሪያ ላይ መሀከል ላይም ብትሆን ሙሉ በሙሉ (#ተፍኺም) ትወፍራለች ለምሳሌ {{ ألم تَرَ }} በዝህ ቦታ ላይ #ራ ፈትሀ ናት ወፍራምም ናት #ራኡን_መክሱር_እሷ_ከስራ_ስትሆን #ራ ከስራ ከሆነች በየትኛውም ቦታ ብትሆን የሷ ሑክም ሙሉ በሙሉ #ተርቂቅ (መቅጠን) ነው። ለምሳሌ {{ ومن شرِّ غاسقً }} #ራ እዝህ ላይ ቀጭን ናት የምትሆነው #ራኡን_መድሙም_ራ_ዶማ_ስትሆን በዝህም ጊዜ እንደ ራኡን መፍቱሕ ትወፍራለች ማለትም #ተፍኺም ትሆናለች ማለት ነው በየትኛውም ቦታ ብትሆን ። ለምሳሌ፦ {{ إنَّ قارُون }} #ራ በዝህ ቦታ ላይ ዶማ ናት ሑክሟም ወፍራምነት #ተፍኺም ነው ። #ራኡን_አሳኪናህ_ራ_ሱኩን_ስትሆን #ራ ሱኩን ስትሆን ከበስተፊትለፊቷ ባለው ፊደል ሀረካ ላይ ትንጠለጠላለች ። ከበፊቷ ያለው ፊደል ሀረካው ፈትሀ ወይም ዶማ ከሆነ ሙሉ በሙሉ ትወፍራለች ለምሳሌ ከበፊቷ ፈትሀ ሲመጣ ፦ {{ وقَرْنَ في بيوتكن}} ከፊቷ ዶማ ሲመጣ ደግሞ ፦ {{ أُرْسِلَ }} እነዝህን ምሳሌዎች መመልከት ይቻላል እንደ ናሙና ያክል #ራ ከፊቷ ያለው ፊደል ሀረካው ከስራ ከሆነ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ትቀጥናለች ። እዝህ ላይ ማስገንዘቢያ ፦ #ራ ስኩን ሁና ከሷ ኋላ ያለው ፊደል #የእስቲዕላእ ፊደል ከሆነ ፊደሉ ከስራ ቢሆንም እሷ ትወፍራለች ። ከፊቷ ከስራ ሲመጣ ለምሳሌ ፦ {{ فِرْعَوْنَ }} #ራ ሱኩን ሁና ከኋላዋ #የኢስቲዕላእ ፊደል ሲመጣባት {{ قِرْطاسٍ }} {{ مِرْصاَد }} በነዝህ ሰአት #ራ ትወፍራለች ሙሉ በሙሉ እሷን ማቅጠን ይጠላል #ማስገንዘቢያ፦ #ራኡን_ስኩን #ወቅፍ ላይ ከመጣች ራሷን የቻለ ሀረካ ቢኖራትም ከፊቷ ባለው የፊደሉ ሀረካ ላይ ትመረኮዛለች። ፈትሀና ዶማ ከሆና #ትወፍራለች። ከስራ ከሆነ ደግሞ ትቀጥናለች ለምሳሌ በፈትሀ ስትመጣ ፦ {{ ونشق القَمَر }} በዶማ ስትመጣ {{ وإلی الله ترجعو الأُمُور }} በከስራ ስትመጣ {{ مُدَّكِرْ }} {{ مُنْقَعِر }} ይቀጥላል ኢንሻ አላህ። ሼር እናድርግ ባረከሏሁ ፊኩም አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል ◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈ ጆይን : ሼር ፣ ሼር ፣ ሼር بـــارك الـلــه فـــــيــــــكـــم https://t.me/furqan_school https://t.me/furqan_school 431 viewsFurqan Online Quran, 11:13