Get Mystery Box with random crypto!

ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

የቴሌግራም ቻናል አርማ yeilmkazna — ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል
የቴሌግራም ቻናል አርማ yeilmkazna — ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል
የሰርጥ አድራሻ: @yeilmkazna
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.91K
የሰርጥ መግለጫ

በየቀኑ የተለያዩ ኢስላማዊ እውቀቶችን ይሸምቱበታል። ይቀላለቀሉ፣ ለሌሎችም ያሰራጩ።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 61

2022-07-06 16:23:50 የፊደላት ባህሪያት ክፍል : 03

አል- ኢስቲዕላእ ፦ ማለት ፊደሉን በምናወጣ
ጊዜ ሩቁ የምላሳችን ክፍልና ድምፅ ወደ
ላይኛው ላንቃ ከፍ ማለት " ማለት ነው ።

የኢስቲዕላእ ባህሪ ያላቸው ፊደላቶች
ናቸው خ ص ض غ ط ق ظ
በአጭሩ ቱም ወፍረው የሚነበቡ
ፊደላቶች ናቸው

ልብ በሉ ብዙ ጊዜ የሚወፍሩ ፊደሎች
የሚቀጥኑብን ቀጥታ ወደ ምላሳችን
ስለምናወጣቸው ነው
ይህም ማለት ወደ ላይኛው ላንቃ ከፍ
አናደርጋቸውም ያን ጊዜ ይቀጥኑብናል

ስናወጣቸው ግን ወደ ላይኛው ላንቃ ከፍ
ካደረግነው ሙሉ በሙሉ ወፍሮ ይወጣል
ማለት ነው

አል- ኢስቲፋል ፦ ማለት ፊደሉን በምንናገር
ጊዜ ድምፅ ወደ ታችኛው ክፍል ዝቅ ማለት
ኢስቲፋል ይባላል ።
ከ ቱ የኢስቲዕላእ ፊደሎች ውጭ
ያሉት የኢስቲፋል ባህሪ ያላቸው ፊደሎች ናቸው

ማሳሰቢያ
ኢስቲዕላእ እና ኢስቲፋል ተቃራኒ ናቸው
ይህ ማለት ኢስቲዕላእ ባህሪ ያላቸው ፊደሎች
ድምጳቸው ወደ ላይኛው ላንቃ ይሄዳል
ፊደሎቹም ወፍረው የሚነበቡት ቱ ናቸው

ኢስቲፋል ግን ድምጳቸው ወደላይ ሳይሆን
ወደ ታችኛው ክፍል ነው የሚወጣው

በአጭሩ ኢስቲዕላእ ከፋታ ነው ኢስቲፋል
ደግሞ ዝቅታ ነው

ምሳሌ ፡( ك ) ካፍን በምናነብ ጊዜ ድምፁን
ስናወጣ ወደ ላይኛው ላንቃ ሳይሆን ወደ
ታች ዝቅ ብሎ ይወጣል
ስለዚህ ካፍ ك (የኢስቲፋል ) ባህሪ ያለው
ፊደል ነው ማለት ነው

ቃፍ ( ق ) ግን ስናወጣው ድምፁ ወደ
ላይኛው ላንቃ ይሄዳል ስለዚህ ( ኢስቲዕላእ )
ባህሪ አለው እንላለን ማለት ነው

(አል - ኢጥባቅ) ፦ኢጥባቅ ማለት በአረበኛ
ቋንቋ ማጣበቅ ( ማላጠፍ )ማለት ነው ።

በተጅዊድ ምሁራኖች ገለፃ
ደግሞ፦ፊደሉን በምንናገር ጊዜ ድምፅ
በምላስና በላይኛው ላንቃ መጣበቅ ማለት
ነው ።

የኢጥባቅ ባህሪ ያላቸው ፊደላቶች አራት
ናቸው ። እነሱም
ص ض ط ظ
ባጭሩ ኢጥባቅ ባህሪ አላቸው ስንል
እነዚህን ከላይ ያሉትን አራቱን ብቻ ነው

ለምሳሌ ፦ ( ط ) ጧ ስንል
ምላሳችን ከላይኛው ላንቃ ጋር ይጣበቃል
ያን ግዜ የኢጥባቅ ባህሪ አለው እንላለን

(አል- ኢንፊታህ )፦ ኢንፊታህ ማለት ፊደሉን
በምንናገር ጊዜ በምላሳችንና በላይኛው ላንቃ
መካከል ትንፋሽ የሚያስወጣ ክፍተት መኖር
ማለት ነው
የኢንፊታህ ፊደሎች ከላይ ከጠቀስኳቸው
ከኢጥባቅ ፊደሎች ص ض ط ظ
በስተቀር የኢንፊታህ ፊደሎች ናቸው

ልብ በሉ የኢንፊታህ ፊደሎች ሀያ አምስት
ናቸው ከ አራቱ ከላይ ካሉት ውጭ

ይቀጥላል...
.
.
.
┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል

የማመልከቻ ሊንክ : ↶ @FurqanOnlineQuran
ግሩፓችንን ይቀላቀሉ ↶
https://t.me/furqan_school
2.1K viewsFurqan Online Quran, 13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 09:07:48 ሲህር ከሺርክ ይመደባልን?


አዎ ሲህር ከሺርክ ይመደባል ! ምክንያቱም ጂኖችን ወይንም ሰይጣናትን ማምለክ ና መታገዝ አለበት። ያውም ይሄ #ሺርክ በጣም የሚያስጠላው ሰዎችን ለመጉዳት ታስቦ ነው።

ሰዎችን ለመጉዳት ٠٠ አላህ ላይ ማጋራት!٠٠ እንዴት ያስጠላል። አላህ ይጠብቀን

ደጋሚ ማለት ሰዎችን ለመጉዳት በማይታየው ጂን አማካኝነት የሚታገዝ ነው። ጂኖች (ሰይጣኖች) ደግሞ ለእነርሱ የሚታዘዙት በአላህ ሲክድ ፣ ዚና ሲሰራ ፣ ከአላህ ውጭ ላለ ሲያርድ፡ ሲሰግድ ፣ ቁርአንን ሲረጋግጥ ፣ ንፅህናውን ሳይጠብቅ ሲቀር ፣በአጠቃላይ ሃራም ነገራቶችን ና ፀያፍ ተግባራትን ሲፈፅም ነው ። እርሱን ሊታዘዙት የሚችሉት።

በሙስሊም ሃገር( በሸሪአ የሚመራ ሃገር) ላይ ደጋሚዎች(ሳሂሮች) ተውበት አድርጉ ተብለው ሳይጠበቁ ሊገደሉ ይገባል።
በዚህ እርምጃ ላይ ደግሞ ሰሃቦች ፈፅመውታል።

ለዚህም እንደማሳያ በቡኻሪ እንደፀደቀው ታላቁ የሙእሚኖች መሪ ኡመር (ረዲየላሁ አንሁ) በእርሱ አመራር ውስጥ ለነበሩት የሻም(የሶሪያ) አመራሮች የወንድ ደጋሚም ይሁን የሴት ደጋሚ ሳይቀር እንዲገደሉ ጥብቅ ትእዛዝ በደብዳቤ ፅፎ ልኮ ነበር።

وقد ثبت عن عمر  أمير المؤمنين  أنه كتب إلى أمرائه في الشام وغيره: "أن يقتلوا كل ساحر وساحرة" لعظم شرهم وخطرهم.

ለከባድ አደገኝነታቸውና ለግዙፍ ክህደታቸው በዱኒያ ላይ ዋጋቸው ይሄ ነው! በአኼራ ደግሞ አላሁ አዘወጀለ የሚገባቸውን ይሰጣቸዋል።

ምክንያቱም የደጋሚዎች በህይወት መኖርና መብዛት የሰው ልጅ በሰላም የመኖር እድሉ እጂግ በጣም አናሳ ነው።

https://t.me/As_Sunah_Yeruqa_telegramgroup
2.0K viewsMohammed Jud, 06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 07:22:01
•|የጧት ቲላዋ ግብዣ|•
┄┄┉┉✽ 024 ✽‌┉┉┄┄

┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል

የማመልከቻ ሊንክ : ↶ @FurqanOnlineQuran
ግሩፓችንን ይቀላቀሉ ↶
https://t.me/furqan_school
1.8K viewsFurqan Online Quran, 04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 06:36:03 አሽ - ሺዳህ ማለት ምን ማለት ነው

ሸዲድ ማለት፡ የፊደሉ መውጫ ቦታ ሙሉ
በሙሉ በመዘጋቱ ምክንያት ፊደሉን በምንናገር
ጊዜ ድምፅ ወደ ውጭ አለመውጣት (መገታት )
ማለት ነው
የሺዳ ባህሪ ያላቸው ፊደሎች ናቸው

ا ج د ق ط ب ك ت

አር -ረኻዋ ፦ ማለት የፊደሉ የመውጫ ቦታ
ሙሉ በሙሉ በመከፈቱ ምክንያት ፊደሉን
በምናወጣ ጊዜ ድምፅ ወደ ውጭ መውጣት
ወይም (መፍሰስ ) ማለት ነው ።

ረኻዋ ማለት ባጭሩ የድምፅ ፍሰት ማለት
ነው ።
የረኻዋ ባህሪ ያላቸው ፊደሎች ከ ቱ
የሺዳህ ባህሪ ካላቸው ውጭ ያሉት የረኻዋ
ባህሪ ያላቸው ናቸው

እነርሱም ፦ ናቸው
ا ث ح خ ذ ز س ش ص ض ظ غ ف و ي هـ

አል-በይኒያህ ፦ ማለት የፊደሉ መውጫ ሙሉ
በሙሉ ባለመዘጋቱ ና ሙሉ በሙሉ
ባለመከፈቱ ምክንያት የሚፈጠረው የድምፅ
ፍሰት በይኒያ ይባላል ።
የበይኒያ ባህሪ ያላቸው ፊደላቶች ናቸው

እነርሱም ፦ ل ن ع م ر

┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል

የመመዝገቢያ ሊንክ : ↶ @FurqanOnlineQuran
ግሩፓችንን ይቀላቀሉ ↶
https://t.me/furqan_school
2.3K viewsFurqan Online Quran, 03:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 05:58:45 ቁርአን ባማረ ድምፅ

{ ۞ لَتَجِدَنَّ أَشَدَّ ٱلنَّاسِ عَدَ ٰ⁠وَةࣰ لِّلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ ٱلۡیَهُودَ وَٱلَّذِینَ أَشۡرَكُوا۟ۖ وَلَتَجِدَنَّ أَقۡرَبَهُم مَّوَدَّةࣰ لِّلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ ٱلَّذِینَ قَالُوۤا۟ إِنَّا نَصَـٰرَىٰۚ ذَ ٰ⁠لِكَ بِأَنَّ مِنۡهُمۡ قِسِّیسِینَ وَرُهۡبَانࣰا وَأَنَّهُمۡ لَا یَسۡتَكۡبِرُونَ }

በተወዳጁ ቃሪእ

الشيخ سعود بن إبراهيم شوريم

ሸይኽ ስኡድ ቢን ኢባራሂም ሹረይም

https://t.me/furqan_school
2.2K viewsFurqan Online Quran, 02:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 10:50:03 የአረበኛ ፊደላቶች ባህሪያት



ሀምስ

#ሀምስ ማለት :- በፊደሉ መውጫ ቦታ ላይ
ያለው መደገፍ ደካማ በመሆኑ ምክንያት
በምንናገር ጊዜ የአየር ፍሰት (መለቀቅ) ማለት ነው
እንደዚሁም የድምፅ አውታሮች
አለመንቀጥቀጥ ማለት ነው

የሀምስ ፊደላቶች ف ح ث ه‍ ش خ ص س ك ت በአጭሩ ሀምስ ማለት የአየር ፍሰት ማለት ነው

አል ጀህር (ْ ألْجَهْر ) ማለት ምን ማለት ነው

ጀህር ማለት በፊደሉ መውጫ ቦታ
ላይ ያለው መደገፍ ብርቱ በመሆኑና
የድምፅ አውታሮች በመጣበባቸው
ምክንያት ፊደሉን ስንናገር አየር ወደ
ውጭ አለመውጣት (መገታት) እና
የድምፅ አውታሮች መንቀጥቀጥ
ጀህር ይባላል ።
በአጭሩ ጀህር ማለት የድምፅ አውታሮች
መርገብገብና የድምፅ መገታት ማለት
ነው
የጀህር ፊደላቶች ናቸው እነሱም :

ا ب ج د ذ ر ز ض ط ظ ع غ ق ل م ن و ي ء
እነዚህን ፊደሎች ስናነብ ነው ይህ ጀህር
የሚባለውን ባህሪ የምናገኘው

የሀምስ ና የጀህር ልዩነታቸው በሀምስ ጊዜ
የድምጵ አውታሮች ይከፈታሉ
በጀህር ጊዜ ግን ይጣበባሉ

ይቀጥላል...

┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል

የመመዝገቢያ ሊንክ : ↶ @FurqanOnlineQuran
ግሩፓችንን ይቀላቀሉ ↶
https://t.me/furqan_school
2.5K viewsFurqan Online Quran, 07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 10:53:08
( إِنَّ ٱللَّهَ ومَلَٰئِكَتَهُۥ يُصَلُّون عَلَى ٱلنَّبِىِّ ۚ يَٰأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءامَنُواْ صلُّواْ عَلَيه وسَلِّمُواْ تَسْلِيمًا )

بلبل المدينة المنورة الشيخ ⁧#محمود_خليل_القارئ⁩ رحمه الله

┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል

የመመዝገቢያ ሊንክ : ↶ @FurqanOnlineQuran
ግሩፓችንን ይቀላቀሉ ↶
https://t.me/furqan_school
2.5K viewsFurqan Online Quran, 07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ