Get Mystery Box with random crypto!

የአረበኛ ፊደላቶች ባህሪያት ሀምስ #ሀምስ ማለት :- በፊደሉ መውጫ ቦታ ላ | ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

የአረበኛ ፊደላቶች ባህሪያት



ሀምስ

#ሀምስ ማለት :- በፊደሉ መውጫ ቦታ ላይ
ያለው መደገፍ ደካማ በመሆኑ ምክንያት
በምንናገር ጊዜ የአየር ፍሰት (መለቀቅ) ማለት ነው
እንደዚሁም የድምፅ አውታሮች
አለመንቀጥቀጥ ማለት ነው

የሀምስ ፊደላቶች ف ح ث ه‍ ش خ ص س ك ت በአጭሩ ሀምስ ማለት የአየር ፍሰት ማለት ነው

አል ጀህር (ْ ألْجَهْر ) ማለት ምን ማለት ነው

ጀህር ማለት በፊደሉ መውጫ ቦታ
ላይ ያለው መደገፍ ብርቱ በመሆኑና
የድምፅ አውታሮች በመጣበባቸው
ምክንያት ፊደሉን ስንናገር አየር ወደ
ውጭ አለመውጣት (መገታት) እና
የድምፅ አውታሮች መንቀጥቀጥ
ጀህር ይባላል ።
በአጭሩ ጀህር ማለት የድምፅ አውታሮች
መርገብገብና የድምፅ መገታት ማለት
ነው
የጀህር ፊደላቶች ናቸው እነሱም :

ا ب ج د ذ ر ز ض ط ظ ع غ ق ل م ن و ي ء
እነዚህን ፊደሎች ስናነብ ነው ይህ ጀህር
የሚባለውን ባህሪ የምናገኘው

የሀምስ ና የጀህር ልዩነታቸው በሀምስ ጊዜ
የድምጵ አውታሮች ይከፈታሉ
በጀህር ጊዜ ግን ይጣበባሉ

ይቀጥላል...

┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል

የመመዝገቢያ ሊንክ : ↶ @FurqanOnlineQuran
ግሩፓችንን ይቀላቀሉ ↶
https://t.me/furqan_school