Get Mystery Box with random crypto!

ሲህር ከሺርክ ይመደባልን? አዎ ሲህር ከሺርክ ይመደባል ! ምክንያቱም ጂኖችን | ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

ሲህር ከሺርክ ይመደባልን?


አዎ ሲህር ከሺርክ ይመደባል ! ምክንያቱም ጂኖችን ወይንም ሰይጣናትን ማምለክ ና መታገዝ አለበት። ያውም ይሄ #ሺርክ በጣም የሚያስጠላው ሰዎችን ለመጉዳት ታስቦ ነው።

ሰዎችን ለመጉዳት ٠٠ አላህ ላይ ማጋራት!٠٠ እንዴት ያስጠላል። አላህ ይጠብቀን

ደጋሚ ማለት ሰዎችን ለመጉዳት በማይታየው ጂን አማካኝነት የሚታገዝ ነው። ጂኖች (ሰይጣኖች) ደግሞ ለእነርሱ የሚታዘዙት በአላህ ሲክድ ፣ ዚና ሲሰራ ፣ ከአላህ ውጭ ላለ ሲያርድ፡ ሲሰግድ ፣ ቁርአንን ሲረጋግጥ ፣ ንፅህናውን ሳይጠብቅ ሲቀር ፣በአጠቃላይ ሃራም ነገራቶችን ና ፀያፍ ተግባራትን ሲፈፅም ነው ። እርሱን ሊታዘዙት የሚችሉት።

በሙስሊም ሃገር( በሸሪአ የሚመራ ሃገር) ላይ ደጋሚዎች(ሳሂሮች) ተውበት አድርጉ ተብለው ሳይጠበቁ ሊገደሉ ይገባል።
በዚህ እርምጃ ላይ ደግሞ ሰሃቦች ፈፅመውታል።

ለዚህም እንደማሳያ በቡኻሪ እንደፀደቀው ታላቁ የሙእሚኖች መሪ ኡመር (ረዲየላሁ አንሁ) በእርሱ አመራር ውስጥ ለነበሩት የሻም(የሶሪያ) አመራሮች የወንድ ደጋሚም ይሁን የሴት ደጋሚ ሳይቀር እንዲገደሉ ጥብቅ ትእዛዝ በደብዳቤ ፅፎ ልኮ ነበር።

وقد ثبت عن عمر  أمير المؤمنين  أنه كتب إلى أمرائه في الشام وغيره: "أن يقتلوا كل ساحر وساحرة" لعظم شرهم وخطرهم.

ለከባድ አደገኝነታቸውና ለግዙፍ ክህደታቸው በዱኒያ ላይ ዋጋቸው ይሄ ነው! በአኼራ ደግሞ አላሁ አዘወጀለ የሚገባቸውን ይሰጣቸዋል።

ምክንያቱም የደጋሚዎች በህይወት መኖርና መብዛት የሰው ልጅ በሰላም የመኖር እድሉ እጂግ በጣም አናሳ ነው።

https://t.me/As_Sunah_Yeruqa_telegramgroup