Get Mystery Box with random crypto!

የፊደላት ባህሪያት ክፍል : 03 አል- ኢስቲዕላእ ፦ ማለት ፊደሉን በምናወጣ ጊዜ ሩ | ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

የፊደላት ባህሪያት ክፍል : 03

አል- ኢስቲዕላእ ፦ ማለት ፊደሉን በምናወጣ
ጊዜ ሩቁ የምላሳችን ክፍልና ድምፅ ወደ
ላይኛው ላንቃ ከፍ ማለት " ማለት ነው ።

የኢስቲዕላእ ባህሪ ያላቸው ፊደላቶች
ናቸው خ ص ض غ ط ق ظ
በአጭሩ ቱም ወፍረው የሚነበቡ
ፊደላቶች ናቸው

ልብ በሉ ብዙ ጊዜ የሚወፍሩ ፊደሎች
የሚቀጥኑብን ቀጥታ ወደ ምላሳችን
ስለምናወጣቸው ነው
ይህም ማለት ወደ ላይኛው ላንቃ ከፍ
አናደርጋቸውም ያን ጊዜ ይቀጥኑብናል

ስናወጣቸው ግን ወደ ላይኛው ላንቃ ከፍ
ካደረግነው ሙሉ በሙሉ ወፍሮ ይወጣል
ማለት ነው

አል- ኢስቲፋል ፦ ማለት ፊደሉን በምንናገር
ጊዜ ድምፅ ወደ ታችኛው ክፍል ዝቅ ማለት
ኢስቲፋል ይባላል ።
ከ ቱ የኢስቲዕላእ ፊደሎች ውጭ
ያሉት የኢስቲፋል ባህሪ ያላቸው ፊደሎች ናቸው

ማሳሰቢያ
ኢስቲዕላእ እና ኢስቲፋል ተቃራኒ ናቸው
ይህ ማለት ኢስቲዕላእ ባህሪ ያላቸው ፊደሎች
ድምጳቸው ወደ ላይኛው ላንቃ ይሄዳል
ፊደሎቹም ወፍረው የሚነበቡት ቱ ናቸው

ኢስቲፋል ግን ድምጳቸው ወደላይ ሳይሆን
ወደ ታችኛው ክፍል ነው የሚወጣው

በአጭሩ ኢስቲዕላእ ከፋታ ነው ኢስቲፋል
ደግሞ ዝቅታ ነው

ምሳሌ ፡( ك ) ካፍን በምናነብ ጊዜ ድምፁን
ስናወጣ ወደ ላይኛው ላንቃ ሳይሆን ወደ
ታች ዝቅ ብሎ ይወጣል
ስለዚህ ካፍ ك (የኢስቲፋል ) ባህሪ ያለው
ፊደል ነው ማለት ነው

ቃፍ ( ق ) ግን ስናወጣው ድምፁ ወደ
ላይኛው ላንቃ ይሄዳል ስለዚህ ( ኢስቲዕላእ )
ባህሪ አለው እንላለን ማለት ነው

(አል - ኢጥባቅ) ፦ኢጥባቅ ማለት በአረበኛ
ቋንቋ ማጣበቅ ( ማላጠፍ )ማለት ነው ።

በተጅዊድ ምሁራኖች ገለፃ
ደግሞ፦ፊደሉን በምንናገር ጊዜ ድምፅ
በምላስና በላይኛው ላንቃ መጣበቅ ማለት
ነው ።

የኢጥባቅ ባህሪ ያላቸው ፊደላቶች አራት
ናቸው ። እነሱም
ص ض ط ظ
ባጭሩ ኢጥባቅ ባህሪ አላቸው ስንል
እነዚህን ከላይ ያሉትን አራቱን ብቻ ነው

ለምሳሌ ፦ ( ط ) ጧ ስንል
ምላሳችን ከላይኛው ላንቃ ጋር ይጣበቃል
ያን ግዜ የኢጥባቅ ባህሪ አለው እንላለን

(አል- ኢንፊታህ )፦ ኢንፊታህ ማለት ፊደሉን
በምንናገር ጊዜ በምላሳችንና በላይኛው ላንቃ
መካከል ትንፋሽ የሚያስወጣ ክፍተት መኖር
ማለት ነው
የኢንፊታህ ፊደሎች ከላይ ከጠቀስኳቸው
ከኢጥባቅ ፊደሎች ص ض ط ظ
በስተቀር የኢንፊታህ ፊደሎች ናቸው

ልብ በሉ የኢንፊታህ ፊደሎች ሀያ አምስት
ናቸው ከ አራቱ ከላይ ካሉት ውጭ

ይቀጥላል...
.
.
.
┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል

የማመልከቻ ሊንክ : ↶ @FurqanOnlineQuran
ግሩፓችንን ይቀላቀሉ ↶
https://t.me/furqan_school