አሽ - ሺዳህ ማለት ምን ማለት ነው ሸዲድ ማለት፡ የፊደሉ መውጫ ቦታ ሙሉ በሙሉ በመዘጋቱ ምክንያት ፊደሉን በምንናገር ጊዜ ድምፅ ወደ ውጭ አለመውጣት (መገታት ) ማለት ነው የሺዳ ባህሪ ያላቸው ፊደሎች ናቸው ا ج د ق ط ب ك ت አር -ረኻዋ ፦ ማለት የፊደሉ የመውጫ ቦታ ሙሉ በሙሉ በመከፈቱ ምክንያት ፊደሉን በምናወጣ ጊዜ ድምፅ ወደ ውጭ መውጣት ወይም (መፍሰስ ) ማለት ነው ። ረኻዋ ማለት ባጭሩ የድምፅ ፍሰት ማለት ነው ። የረኻዋ ባህሪ ያላቸው ፊደሎች ከ ቱ የሺዳህ ባህሪ ካላቸው ውጭ ያሉት የረኻዋ ባህሪ ያላቸው ናቸው እነርሱም ፦ ናቸው ا ث ح خ ذ ز س ش ص ض ظ غ ف و ي هـ አል-በይኒያህ ፦ ማለት የፊደሉ መውጫ ሙሉ በሙሉ ባለመዘጋቱ ና ሙሉ በሙሉ ባለመከፈቱ ምክንያት የሚፈጠረው የድምፅ ፍሰት በይኒያ ይባላል ። የበይኒያ ባህሪ ያላቸው ፊደላቶች ናቸው እነርሱም ፦ ل ن ع م ر ┄┄┉┉✽» ✿ »✽┉┉┄┄ ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል የመመዝገቢያ ሊንክ : ↶ @FurqanOnlineQuran ግሩፓችንን ይቀላቀሉ ↶ https://t.me/furqan_school 2.3K viewsFurqan Online Quran, 03:36