Get Mystery Box with random crypto!

ትኩረት የነፈግነው ሐቅ ~~ 'ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን ተምሮ ያስተማረ ነው' ብለዋል ነብያችን ( | ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

ትኩረት የነፈግነው ሐቅ
~~
"ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን ተምሮ ያስተማረ ነው" ብለዋል ነብያችን (ﷺ)። [ቡኻሪ]
ይሁን እንጂ ብዙ ቁርኣን ያልቀራ ወገን እያለን ለጉዳዩ የሰጠነው ትኩረት ግን ለችግሩ የሚመጥን አይደለም። ስለሆነም ችግሩን በመቅረፍ ላይ ከራሳችን ልንጀምር ይገባል። እና
* ቁርኣን ካልቀራን ለምን አንቀራም?
* ያልቀራ ቤተሰብ ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት፣ ወዘተ. ካለ ለምን አናቀራም?
* ይህም ካልሆነልን የሚያቀሩትን በምንችለው አቅም ለምን አናግዝም?
ዛሬ ዛሬ ቁርኣን ማስተማር የሰነፎች ወይም እውቀታቸው የደከሙ ሰዎች ስራ እየመሰለ ነው።
ቁርኣን ያልቀራህ ወገኔ ሆይ! የትኩረት ማነስ እንጂ እውነት ቁርኣን ማንበብ መቻል ይህን ያክል ከባድ ነገር ሆኖ ነው ወይ? እስከ መቼ ነው 28 የዐረብኛ ፊደላትን አገጣጥሞ ማንበብ ተራራ የሚሆንብህ? ወላሂ! ተገቢ ትኩረት ብንሰጠው ቁርኣን ፈፅሞ ዛሬ በሃገራችን የሚወስደውን የጊዜ መጠን የሚጠይቅ አልነበረም። ከልብ ካለቀሱ እምባ አይገድም ይባላል።
እና ወንድሜ ሆይ! በነፃ የሚያስተምርህ ካገኘህ እሰየው። ካልሆነ ግን በክፍያ የሚያስተምሩ ወንድም/እህቶች ካሉም ደስ እያለህ ከፍለህ ተማር። ለሚያሳንፉ ሰዎች ጆሮ አትስጥ። ቁርኣን መማር ዲግሪና ዲፕሎማ ከመማር በታች ነውንዴ? ቁርኣን መማር ቋንቋ፣ ኮምፒተር፣ ... ከመማር በታች ነውንዴ? እነዚህን ነገሮች ለመማር ስንትና ስንት እያወጣን ቁርኣን ለመማር የሚወጣው ላይ ለቅሶ ማብዛት ምንድነው?
ይልቅ በጊዜ ቁርጠኛ ውሳኔ ወስን። ከዜሮም ብትነሳ እሩቅ አይደለም ትደርሳለህ። ማረም ማስተካከል ከሆነም በአጭር ጊዜ ትጋት ሁነኛ ለውጥ ታያለህ። አላህ ያግዘን።
~
ኮፒ
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
በOnline ተመዝግቦ ቁርኣን ለመማር
@FurqanOnlineQuran
ለበለጠ መረጃ ይቀላቀሉን
https://t.me/furqan_school