Get Mystery Box with random crypto!

ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የሰርጥ አድራሻ: @wdasemaryam
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18
የሰርጥ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን።
በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
መራግብራችን👇👇
✅የበገና መዝሙሮች
✅ የንስሐ መዝሙሮች
✅ ያሬዳዊ ዜማ
✅ ስብከቶች
✅ መፅሐፍ ሀይማኖት....የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
አስተምህሮትን በተመለከተ፤ ስለ መላእክት፤ስለ ቅዱሳን፤ ያገኙበታል።

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-06 22:06:11 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በአርጋኖን መጽሐፉ ላይ፡-
“ከርሠ ድንግል ሰፍሐ እምሠረገላ ብርሃን ዘመልዕልተ ጌልጌል…” (የድንግል ማሕፀን በሰማይ ካለው የብርሃን ሠረገላ ሰፋ፤ የድንግል ማሕፀን ከአየራት በለጠ፤ በሱራፌልና በኪሩቤል ዘንድም ተመሰገነ፤ የድንግል ማሕፀን የሰማይ ደጃፍ ኾነ፤ ሳይከፈትም የፀሓይ መውጪያና መግቢያ ኾነ፤ የድንግል ማሕፀን ለአማናዊ የጽድቅ ገንዘብ ሣጥን ኾነ፤ የድንግል ማሕፀን አዶናይ በመባል ለሚጠራ እግዚአብሔር ማደሪያን ኾነ) በማለት “ሀገረ እግዚአብሔርነቷን በጥልቀት በማሕፀኗ ከተከናወነው ከተዋሕዶ ምስጢር በመነሣት አስተምሯል፡፡

በተጨማሪም በእንዚራ ስብሐት የነገረ ማርያም መጽሐፉ ላይ ምስጢሩን እንደ ወርቅ አንከብልሎ እንደ ሸማ ጠቅልሎ፦

“ኦ እግዝእትየ ማርያም ርግበ ተደንግሎ
እዌድሰኪ በአዕብዮ ወእባርከኪ በአልዕሎ
እስመ ኮንኪዮ እሞ ለዘእምቅድመ ዓለም ሀሎ
ዘኢያገምሮ ሰማይ ወስፍሐ ምድር ኢየአክሎ”
ጽበተ ከርሥኪ ጾረ ወአግመረ ኀይሎ”

(የድንግልና ርግብ እመቤቴ ማርያም ሆይ በማግነን አመሰግንሻለኊ ከፍ ከፍ በማድረግም አመሰግንሻለኊ ከዓለም አስቀድሞ ለነበረ አካላዊ ቃል እናቱን ኾነሻልና ሰማይ የማይችለውንና የምድር ስፋትም የማይበቃውን ጠባብ ማሕፀንሽ ተሸከመው ኀይሉንም ቻለ) በማለት ተመሳሳይ የአድናቆት ምስጋናን አመስግኗል፡፡

ሊቁ አባ ሕርያቆስም ስለዚኽ ምስጢር በቅዳሴ ማርያም መጽሐፉ በቊ ፵፭ ላይ ሲገልጽ፡- “ወሶበ ርእየ ንጽሕናኪ ለሊሁ እግዚአብሔር አብ …” (ርሱ ቅሉ እግዚአብሔር አብ ንጽሕናሽን ባየ ጊዜ ስሙ ገብርኤል የሚባል ብርሃናዊ መልአኩን ወደ አንቺ ላከ፤ መንፈስ ቅዱስ በላይሽ ይመጣል የልዑል ኀይልም ይጋርድሻል አለሽ፤ ከአባቱ አጠገብ ሳይለይ ቃል ወደ አንቺ መጣ፤ ሳይወሰን ፀነስሺው በላይ ሳይጐድል በታችም ሳይጨመር በማሕፀንሽ ተወሰነ፤ መጠንና መመርመር የሌለበት እሳተ መለኮት በማሕፀንሽ ዐደረ) በማለት መልእክተኛው ቅዱስ ገብርኤል አስቀድሞ ተልኮ ቅድስት ድንግል ማርያምን ሲያበሥራት፤ ርሷም ቃሉን በእምነት በተቀበለች ጊዜ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የአብ የባሕርይ ልጅ በማሕፀኗ የማደሩን ነገር አስተምሯል፡፡

ይኽ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት አምላክ በማሕፀነ ማርያም ያደረበትን የፅንሰቱን በዓል ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት በምስጋና፣ በቅዳሴ፣ በትምህርት መጋቢት ፳፱ ቀን ስታስብ ከጌታችን ዘጠኙ ዐበይት በዓላት ውስጥ አንደኛውና የመጀመሪያው አድርጋ ታስበዋለች፡፡
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
938 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 22:06:10 [መጋቢት 29 ወልደ እግዚአብሔር በአመቤታችን ማሕፀን የተፀነሰበት ታላቅ በዓል]
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
ቅድስት ድንግል ማርያም በአረጋዊዉ በዮሴፍ ቤት እያለች ለትሩፋት አትገበዝም ነበርና ከዕለታት ባንዳቸው ውሃ ለመቅዳት በሀገራቸው ወደሚገኝ ወደ ውሃ ጒድጓድ ኼዳ ስትመለስ “ሑር አብሥራ ለማርያም ከመ እትወለድ እምኔሃ” (ከርሷ እንድወለድ ኼደኽ ለድንግል ማርያም ንገራት) ብሎ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን በስድስተኛው ወር ወደ ርሷ ላከው (ሉቃ ፩፥፳፮)።

ምን በኾነ በስድስተኛው ወር ተላከ ብሎ ሉቃስ ጻፈ ቢሉ? ለጊዜው ዮሐንስ በመስከረም ወር ተፀንሷል የጌታ ፅንስ ደግሞ በመጋቢት ፳፱ ነውና ከመስከረም አንሥቶ እስከ መጋቢት ቢቈጥሩ ስድስት ወር ይኾናልና “በስድስተኛው ወር” አለ፤ ፍጻሜው ግን በስድስተኛው ቀን (በዕለተ ዐርብ) የተፈጠረው አዳም በድሎ ነበርና ርሱን ለማዳን በርሱ ያጣነውን ልጅነት ለመመለስ እንደመጣ ለማጠየቅ።

ዳግመኛም ፭ሺሕ ፭፻ ዘመን ተፈጽሞ በስድስተኛው ሺሕ ዘመን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከጌታ ወደ እመቤታችን ተላከ ማለቱ እንደኾነ መተርጒማን ያስተምራሉ ፡፡

ከዚያም መልአኩ ተገልጾላት ብሥራትን አሰማት፤ ርሷም አይታው ኼደች፤ ኋላም ወደ ቤት ገብታ ማድጋዋን አሳርፋ ሳለ ረቂቅ ነውና ተሰውሮ “ትፀንሻለሽ” አላት፤ ርሷም “ይኽ ነገር ደጋገመኝ ደግ ነገርን በደግ ቦታ ኹነው ሊረዱት ይገባል” ብላ፤ ወደ ቤተ መቅደስ ኼዳ በዚያ ወራት ለቤተ መቅደስ መጋረጃ ለመፍተል ከደናግለ እስራኤል ጋራ የተካፈለችውን ሐርና ወርቀ እያስማማች ስትፈትል መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለሦስተኛ ጊዜ ተገልጾላታል፡፡

የአምላክ እናት ቅድስት ድንግል ማርያም ሐርንና ወርቅን አስማምታ ስትፈትል ቅዱስ ገብርኤል ተገልጾ እንዳበሠራት ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ፡-

“ቅዱስ ገብርኤል መልአከ ፍሥሓ በእሳት ሥዑል
ሰበካ ለድንግል ምጽአቶ ለቃል
ወርቀ ወሜላተ እንዘ ትፈትል”
(በእሳት የተቀረጸ የደስታ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ወርቅንና ሐርን ስትፈትል የቃል መምጣቱን (ሥጋ መኾኑን) ለድንግል አበሠራት) በማለት ገልጾታል ፡፡

አባ ጽጌ ድንግልም ሐርንና ወርቅን አስማምታ ስትፈትል መልአኩ እንደተገለጠላት በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፉ ላይ፡-

“ፈትለ ወርቅ ወፈትለ ሜላት አመ በአጽባእትኪ ተባየጹ
አምሳለ መለኮት ወትስብእት እንዘ ኢየሐፁ
ተአምረ ብርሃን ማርያም ለፀሓየ ጽድቅ አንቀጹ
ጸገይኪዮ እንበለ አብ በሰሚዐ ቃሉ ወድምፁ
ለገብርኤል መልአክኪ ዘፍሡሕ ገጹ”
(የእውነት ፀሓይ መውጫ የብርሃን ምልክት ማርያም የትስብእትና የመለኮት ተዋሕዶ አምሳል ሳያጐድሉ የሐርንና የወርቅን ፈትሎች በጣቶችሽ በሚፈተሉበት ጊዜ ፊቱን ደስ ያለው የተላከልሽ የገብርኤል ድምፁን በመስማት ጌታን ያለ አባት ፀነስሺው) በማለት ገልጾታል፡፡

መልአኩ ስለምን ሦስት ጊዜ ታያት ቢሉ? ለጊዜው ሰይጣን የኾነ እንደኾነ አንድ ጊዜ ታይቶ ይጠፋ ነበርና ብርሃናዊ መልአክ እንደኾነ ለማጠየቅ ሲኾን ፍጻሜው ግን የሥላሴ ማደሪያ መኾኗን ሲያስረዳት ነው (ሉቃ ፩፥፴፫፤ ማቴ ፲፰፥፲፮)፡፡

ወደ እመቤታችንን ለማብሠር ብዙ መላእክት ሳሉ ቅዱስ ገብርኤል ለምን ከመላእክት ተመረጠ? ቢሉ ቀደምት መተርጒማን ምስጢሩን ጽፈዋል ይኸውም፡-

1ኛ. ቅዱስ ገብርኤልን “እስመ አብሣሬ ፅንስ ውእቱ” እንዲለው በብሉይ ኪዳን ታሪኮች ፅንስን በማብሠር የታወቀ መልአክ ነውና፤ ለምሳሌ የሶምሶንን እናትና አባትን፣ እነ ዘካርያስን ልጅ እንደሚያገኙ ያበሠረ መልአክ ነውና ጥንት በለመደው ይኹን ሲል ርሱን ልኮታል (መሳ ፲፫፥፳፩፤ ሉቃ ፩፥፲፱)፡፡

፪ኛ. የስሙ ትርጓሜ ተልእኮውን ያመለክታልና ይኸውም ሚካኤል ማለት የቃሉ ትርጉም “መኑ ከመ አምላክ” (ማን እንደ አምላክ) ማለት እንደኾነ ኹሉ ገብርኤል ማለት ሲተነተን “ገብር” ወይም “ጋቦር” የሚለው የዕብራይስጥ ትርጓሜ ሰው ወይም ጠንካራ የሚለውን ፍቺ ሲያመጣ “ኤል” ማለት ደግሞ አምላክ ማለት ነውና ባንድ ላይ “አምላክ ወሰብእ” (አምላክም ሰውም) ማለት ነው፤ ስለኾነም የአምላክ ሰው የመኾን ምስጢርን በስሙ የያዘ መልአክ ነውና እግዚአብሔር ባወቀ ሥጋዌዉን እንዲያበሥር ልኮታል፡፡

፫ኛ. የሥነ ፍጥረት መጻሕፍት እንደሚነግሩን እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ መላእክት ተፈጥረው ሳጥናኤል ባወካቸው ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል “ንቁም በበህላዌነ እስከ ነአምሮ ለአምላክነ” (የፈጠረን ይኽ አይደለምና ፈጣሪያችንን እስክናውቀው ድረስ በያለንበት እንጽና) በማለት በተናገረ ጊዜ ፺፱ኙ ነገደ መላእክት በቅዱስ ገብርኤል ቃል ጸንተው ቆመዋል፤ በዚኽ ዓለም ሳለ ጦርን ያረጋጋ መልካም ዐርበኛ ወደ ንጉሡ ዘንድ ደርሶ እንደሚሸለም ኹሉ “ወበእንተዝ ደለዎ ለገብርኤል ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም” እንዲለው ቅዱስ ገብርኤልም ይኽነን በተናገረበት አንደበቱ የአምላክን ሥጋዌ ለመንገር ለእመቤታችን ባለምሥራች ለመኾን አብቅቶታል፡፡

ጌታም ቅዱስ ገብርኤልን ሳይልክ በእመቤታችን ማሕፀን ማደር ይችላል ግን አስቀድሞ መልአኩን የላከበት ምክንያት ስለምን ነው? ቢሉ፤ ትንቢቱን ለመፈጸም ነው ይኸውም አስቀድሞ በነቢዩ ሚልክያስ ዐድሮ በምዕ ፫፥፩ ላይ፡-
“እነሆ መልእክተኛዬን እልካለኊ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይወጣል” በማለት መላው የሰው ዘር በተስፋ ይጠባበቀው የነበረው፤ ቀደምት አበው ነቢያት ሊያዩት ይፈልጉት የነበረው የአምላክ ሥጋዌን ለማብሠር ቅዱስ ገብርኤልን አስቀድሞ ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም ለብሥራት በመላክ፤ በአማናዊት መቅደስ በማሕፀነ ማርያም ፱ወር ከ፭ ቀን የማደሩን ነገር አስቀድሞ በነቢዩ ትንቢትን አናግሯል፡፡

ልዑል እግዚአብሔር ባወቀ ስለ ብሥራቷ ትንቢቱን አስቀድሞ አናግሯል፤ ምስጢሩስ ቢሉ? እነሆ ንጉሥ ወደ አዳራሹ ሊገባ ሲል አንጥፉ አሰናዱ ለማለት መልእክተኛውን አስቀድሞ እንደሚልክ ኹሉ፤ ጌታም የሰማይ የምድር ንጉሥ ነውና፤ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምም ንጽሕት መቅደሱ ናትና፤ ነገሩን አስቀድማ ጠንቅቃ ዐውቃ ተቀብላ ትቆየኝ ሲል ቅዱስ ገብርኤልን ልኮታል (ሉቃ ፩፥፳፮‐፳፰)፡፡

ሊቁ ቅዱስ አትናቴዎስም በዚኽች ዕለት ስለተከናወነው አስደናቂ ምስጢር ሲገልጽ፦ “Today is the beginning of our salvation…,” (ዛሬ የድኅነታችን መጀመሪያና እና የዘላለማዊ ምስጢር መገለጽ ነው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የድንግል ልጅ ኾነ፤ ቅዱስ ገብርኤል ሊመጣ ያለውን የስጦታውን ነገር እንደተናገረ፤ እኛም ከርሱ ጋር ኾነን ወደ አምላክ እናት በመጮኽ “ጸጋን የተመላሽ ደስተኛዪቱ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና” እንበል) በማለት በጥልቀት አስተምሯል።

ከዚኹ ጋራ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በመጽሐፈ ድጓው ላይ “ሰማይ ወምድር ዘኢያገምሮ እፎ እንጋ ማሕፀነ ድንግል ጾሮ” (ሰማይና ምድር የማይችሉትን አምላክ እንደምን የድንግል ማሕፀን ቻለው?) በማለት የጠየቀውን ጥያቄ ሊቃውንት በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት በጥልቀት አስተምረዋል፤ ይኸውም እመቤታችን በሰው መጠን ሦስት ክንድ ከስንዝር ስትኾን ርሷ ግን ከጽርሐ አርያም በላይ ርዝመቱ ከበርባሮስ በታች ጥልቀቱ ከአድማስ እስከ ናጌብ ስፋቱ ተብሎ የማይመረመር በኹሉ የመላውን አካላዊ ቃል በማሕፀኗ የተሸከመች በመኾኗ “የእግዚአብሔር ሀገር” መባሏ በጉልሕ ታውቋል፡-
791 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 22:06:04
680 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 04:52:11 የዐብይ ፆም ሰባተኛው ሳምንት ꔰኒቆዲሞስꔰ ይባላል፤ በዚህ ሳምንትም ይህ ይታሰብበታል፡፡

‹‹ኒቆዲሞስ››፤ * አይሁዳዊ ሲሆን ከፈሪሳውያን ወገን የነበረ ነው
ꔰቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያውን በንባብ ለመጀመርያ ጊዜ ጌታን ሲገንዝ የተማረ (ኃላ ዜማውን ቅዱሰ ያሬድ ደርሶታል )
ꔰምሑረ ኦሪት ነው ረቢ ይባላል ፤ በእሥራኤለውን ሕግ ረቢ የሚባለው ከ 5000 መጻሕፍት በላይ መተረጐም፤ ማንበብ ..እና ሲያውቅ ነው ፡፡

* በኢየሩሳሌም በሀብት ቢሉ በዕውቀት እንዲሁም በሥልጣን የአይሁድ አለቃ ነበር፡፡
* ማታ ማታ ጌታችን ዘንድ እየተገኘ ይማር ነበር፡፡
*ቅኔ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊተ ለረቢ ፤
አኮነ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የዓቢ ፡፡
ትርጉም ፤ መምህር ለመምህር በመንፈቀ ሌሊት ሰገደከጣት ጣት ይበልጣልና>> እንዲል ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ እንዲህ አስቀምጦልናል፦
ꔰ ‹‹ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦ ‹‹መምህር ሆይ እግዚአብሔር ከእሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህ ተዓምራቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን›› አለው፡፡
ꔰ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።
፨ ኒቆዲሞስም፦ ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? አለው።
ꔰ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።›› /ዮሐ. ፫፥ ዘ፩-፲፭//ፍ.ሕ.ሰ.ት.ቤት/
ለምን በሌሊት ይመጣ ነበር?
ꔰ አይሁድ ‹‹ማንም ከእኛ ወገን የሆነ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ከሆነ ሀብት ንብረቱ ይወሰድ፣ በቤተመቅደስ አይግባ፣ መሥዋዕት አይሥዋ›› ብለው ነበርና አይሁድን ፈርቶ፥ ሀብት ንብረቱን ወዶ እንዳይታወቅበት በሌሊት ይመጣ ነበር፡፡
ꔰ በሌላ በኩል ደግሞ የቀን ልብ ባካና ነው፤ ዓይን ብዙ ያያል፥ ሐሳብ ይበታተናል፡፡ በተሰበሰበ ልብ ለመማር፤ በተጨማሪ ‹‹ሊቅ ነኝ›› እያለ ‹‹እስከ ዛሬ ትምህርት አልጨረሰም›› እንዳይሉት በሌሊት ይመጣ ነበር፡፡
ꔰ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንኳን ለመማር የመጣውን እራሱ እየሄደ ያስተምር ነበርና ኒቆዲሞስ ምንም በሌሊት ቢመጣም ማወቅን ፈልጎ ነውና ስለዳግም መወለድ /ስለጥምቀት/ በእግዚአብሔር ልጅ ስለማመንና ስለ ጽድቅ ስራ በዝርዝር አስተምሮታል፡፡
ꔰ ኒቆዲሞስ በመጨረሻው ቀን በዕለተ ዐርብ በስቅለቱ ጊዜ፤ ከመስቀል ላይ ሥጋውን ለማውረድና ገንዞ ለመቅበር ቀድሞ ተገኝቷል፡፡ /ዮሐ. ፲፱፥፴፰/

ከኒቆዲሞስ ሕይወት የምንማረው፡-
፩. ትሕትና፦ ኒቆዲሞስ በትምህርት፣ በሹመት፣ በባለጸግነት የአይሁድ አለቃ ሲሆን አለቅነቱ ግን ከጌታ እግር ስር ቁጭ ብሎ እርሱ ተገኝቶ ለመማር አልከለከለውም፡፡ /በጽሑፉ መጨረሻ ያለውን ቅኔ ተመልከቱ/
፪. አለማመካኘት፦ ከመጀመሪያ ሰዎች ከአዳምና ከሔዋን ጀምሮ ሰዎች በምክንያተኝነት በአመፅ መንገድ ይጓዛሉ፡፡ ኒቆዲሞስም ወደ ጌታ በመቅረቡ የጸሐፍት ፈሪሳውያን አድማና ግርግር ታላቅ እንቅፋትና ምክንያት መሆን እንደሚችል ያውቃል፡፡ ነገር ግን ይህ ምክንያት በእግዚአብሔር ፊት እንደማያዋጣ አውቆ የሚያወጣውን አደረገ፡፡
፫. ጥበብ፦ በክርስትና ጉዞ ውስጥ ጥበብ የመጀመሪያ ቦታ ትይዛለች፡፡ ኒቆዲሞስም ጕዞውን በጥበብ አደረገ፡፡ በሌሊት ያደረገበት ምክንያት፡- ራሱ መምህር ሆኖ ሌላ ትምህርት አስፈለገው ብለው ሌሎች እንዳይሰናከሉበት፣ የመዓልት ልቦና ስለሚሰበሰብ በቂ ዕውቀት ለማግኘት፣ መንፈሳዊ ፍሬ ለማፍራት በመዓልትም በሌሊትም ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንዳለብን ለማጠየቅ፣ ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ያሉ ነፍሳት በሲዖል ይገኛሉ ሲል፣ በመዓልትም በሌሊትም ብትፈልጉ ትገኛለች ሲል ነው፡፡ በእውነት ግሩም ጥበብ!
፬. የተነገረውን አምኖ በመቀበሉ፡- ጸሐፍት ፈሪሳውያን ብዙ ምክንያቶች እየደረደሩ የጌታን አምላክነት አምኖ መቀበል ሲያቅታቸው እርሱ ግን ጌትነቱን ለመቀበል ጊዜ አልወሰደበትም፡፡
፭. ለእውነት መመስከር፡- እነርሱ ሲክዱ ጌታ ላይም ትርፍ ቃል ሲናገሩ፤ በድፍረት መክሰሳቸውን እየነገራቸው የጌታችን አምላክነቱን በግልጽ ይመሰክር ነበር፡፡
፮. ጽንዓት፡- ብዙዎች በመከራ ጊዜ ላይለዩት ቃል ቢገቡም መጨረሻ ላይ ያኔ በመከራ ሰዓት ከመስቀሉ ሥር ሊገኙ የቻሉ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ኒቆዲሞስም በዚች ሰዓት ያንን መከራ ታግሶ በጽነዓት ከዮሴፍ ጋር የጌታን ሥጋ ከመስቀል አውርደው በአዲስ መቃብር ቀብረውታል፡፡

ꔰ ወስብሐት ለእግዚአብሔርꔰ
735 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 01:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 02:49:37
ለዚህ አንክሮ ይገባል!
.........................
በጨለማው ዘመን ያበራች አማናዊት ጨረቃ (ጥንተ አብሶ የሌለባት)

12 ዓመት በቤተመቅደስ ሰማያዊ ምግብና መጠጥ እየተመገበች ያደገች

ዘላለማዊ ድንግል የሆነች ( ቅድመ ጸኒስ፣ጊዜ ጸኒስ፣ ድኅረ ጸኒስ ድንግል)

እመ እግዚአብሔር ተብላ የምትጠራ የአምላክ እናት

አምላክን ልጄ ብላ የምትጠራ (ልጇ ፈጣሪ የሆነ)

ወደ ሰማይ ያረገች

በማሰብ፣በመናገር፣ በማድረግ ንጽሕት

እመብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም።

#እመቤቴ ሆይ አመሰግንሻለሁ

✥ከልጅሽ አስታርቂን✥
805 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 23:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 08:54:40 ያስጥለው ነበር፡፡
“እኔ ባሪያህ የአባቴን በጎች ስጠብቅ አንበሳ ወይም ድብ ይመጣ ነበር ከመንጋውም ጠቦት ይወሰድ ነበር በኋላውም እከተለውና እመታው ነበር ከአፉም አስጥለው ነበር በተነሳብኝም ጊዜ ጉረሮውን አንቄ እመታውና እገድለው ነበር፡፡ ይህም ፍልስጥኤማዊ ከነዚያ እንደ አንዱ ይሆናል እንግዲህ እገድለው ዘንድ ከእስራኤል ተግዳሮትን አስወግድ ዘንድ ዛሬ አልሄድምን? የሕያው አምላክ ጭፍሮችን ይገዳደር ዘንድ ይህ ቆላፍ ምንድን ነው? ከአንበሳና ከድብ ያስጣለኝ እግዚአብሔር ከዚህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያስጥለኛል” አለ 1ሳሙ.17፥34፡፡
ዛሬስ ቢሆን በእስራኤል ዘነፍስ በምዕመናን ላይ የሚገዳደሩ ብዙ ፍልስኤማውያን ተሰልፈዋል እነዚህን ድል የሚነሣ በጎቹን ምዕመናን ከተኩላ ከአንበሳና፣ ከድብ አፍ የሚታደግ ታማኝ አገልጋይ ማነው ከምእመናን ተግዳሮት የሚያርቅ ፈጣሪዬ ከመከራ ያድነኛል ብሎ የሚታመን የኢአማንያን ብዛት የማያስፈራው ማን ነው? ከትንሽነቱ እስከ ታላቅነቱ የታመነ አገልጋይ ማነው? ለተሾመበት ሓላፊነት ታማኝ ማነው? አሁንም ዓለማችን ከሥጋውያን ባለ ሥልጣናትም ሆነ ከመንፈሳዊያን መሪዎች የምትሻው ታማኝ ሰው ነው በሙስና ያልተዘፈቀ ጉቦ አይኑን ያላጨለመበት ለመንጋው አርአያና ምሳሌ የሚሆን ሰው ታማኝ አገልጋይ ማለት ያ ነው፡፡ በመኀላ የተቀበለውን የአገልግሎት ሓላፊነት የማይዘነጋ ጳጳስ፣ ቄስ፣ ዲያቆን፣ ሰባኪ፣ መምህር፣ ሐኪም፣ ዳኛ፣ ነጋዴ፣ ተማሪ፣ ወታደር፣ የቤት ሠራተኛ፣ የቢሮ ሠራተኛ ታማኝ መሆን አለበት፡፡
መንጋው በክህደት ሲጠፋ ዝም ብሎ የሚያይ ጳጳስ፣ ቄስ፣ ዲያቆን፣ መምህር፣ ሰባኪ፣ ታማኝ አይደለም ታማሚው እየተሰቃየ የሚዝናና ቆይ ሻይ ልጠጣና የሚል ሐኪም ታማኝ አይደለም፡፡ ፍርድ የሚያጎድል ድሆችን የሚበድል ለደሃ አደጎች የማይፈርድ ዳኛ ታማኝ አገልጋይ አይደለም፡፡
ቅቤ በሙዝ እና በድንች ቀላቅሎ በርበሬ በገል ጨምሮ ሌሎችን አጭበርብሮ የሚሸጥ ነጋዴ ታማኝ አገልጋይ አይደለም፡፡ እየነገደ ያለው በሰው ሕይወት መሆኑን መዘንጋት የለበትም፡፡ እንደእየ አቅሙ በተሰጠው የአገልግሎት ዘርፍ ታማኝ መሆን አለበት፡፡
3. ታማኝ አገልጋይ ማን ነው? ዮሴፍ ነው፡፡
ዮሴፍ ለወንድሞቹ ምግባቸውን ተሸክሞ የእርሱ ስንቅ ቢያልቅ የወንድሞቹን ስንቅ ያልበላ በትንሽ የታመነ ሰው ነበር፡፡ ወንድሞቹ ሸጠውት በቤተ ጴጥፋራ በሚያገለግልበት ጊዜም ታማኝ ነበር፡፡ ታማኝነቱ በጲጥፋራ ቤት ጌታ አድርጎታል፡፡
“ዮሴፍ ተሸጠ አገልጋይም ሆነ እግሮቹ በእግር ብረት ስለሰሉ ሰውነቱም ከብረት አመለጠች ቃሉ ሳይደርስ የእግዚአብሔር ቃል ፈተነው ንጉሥ ላከ ፈታውም የሕዝብ አለቃ አድርጎ ሾመው የቤቱም ጌታ አደረገው በገንዘቡ ሁሉ ላይ ገዢ አደረገው፡፡ አለቆቹን እንደ እርሱ ይገስጽ ዘንድ ሽማግሌዎችን እንደ እርሱ ጥበበኞች ያደርጋቸው ዘንድ” መዝ.104፥17፡ በዚህ ሁኔታ የነበረው ዮሴፍ የጌታው ሚስት ሲወጣ ባቱን ሲገባ ደረቱን እያየች ዐይኗን ጣለችበት በዝሙት አይን ተመለከተችው፡፡
“የጌታውም ሚስት በዮሴፍ ላይ ዐይኗን ጣለችበት ከእኔም ጋር ተኛ አለችው እርሱም እምቢ አለ፡፡ ለጌታው ሚስቱ እንዲህ አላት እነሆ ጌታዬ በቤቱ ያለውን ሁሉ ለእኔ በእጄ አስረክቦኛል፡፡ በቤቱ ያለውን ምንም የሚያውቀው የለም በዚህ ቤት ከአኔ የሚበልጥ ሰው የለም፡፡ ሚስት ስለሆንሽ ከአንቺ በቀር ያልሰጠኝ ነገር የለም እንዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ? እንዴትስ በእግዚአብሔር ፊት ኀጢአትን እሠራለሁ ይህን ነገር በየዕለቱ ለዮሴፍ ትነግረው ነበር” ዘፍ.39፥7፡፡
በዮሴፍ ታማኝነት የጌታው ቤት ተባርኳል፡፡ ሀብቱ በዝቷል፡፡ በታማኝነቱ በቤቱ ያለውን ሁሉ ተረክቦ ነበር የቀረበለት ፈተና ግን ከባድ ነበር፤ ይህን በታማኝነቱ ማለፍ ችሏል፡፡ ዛሬ በእየአንዳንዱ ጓዳ እንደ እሳት የሚያቃጥሉ አገልጋዮች ናቸው ያሉት ልጅ በፈላ ውኃ የሚቀቅሉ ናቸው የሚበዙት እንኳን በሁሉ ገንዘብ ለመሾም አይደለም፡፡ በጥቃቅን ዕቃዎች እንኳን የሚታመን ጠፍቷል፡፡ ዮሴፍ ግን በታማኝ አገልጋይነቱ በመጣበት መከራ ቢታሰር እንኳ ያለ ሹመት አላደረም የእስረኞች አለቃ ነበር፡፡ ከእስር ቤት ሲወጣም ግብፅን በሙሉ መርቷታል፡፡ በግብፃውያን በሙሉ ተሾሟል በጥቂቱ ታምኗልና፡፡ “በጥቂቱ የታመነ በብዙ ይሾማል” እንዲል ማቴ.25፥24፡፡
ጌታውም መልካም አንተ የታመንህ በጎ አገልጋይ በጥቂት የታመንህ ስለሆንህ በብዙ እሾምሀለሁ” ከነዚህ ሦስት ታማኝ አገልጋዮች ሕይወት ሁሉም የሰው ልጅ ታማኝ አገልጋይነት የሚያሰጠውን ክብርና ጸጋ ተመልክቶ በታማኝነት ማገልገል ይገባዋል፡፡ ታማኝ መሆን መጀመሪያ የሚጠቅመው ለራስ ነው ከዚያ በኋላ ለሀገር ለወገን ለቤተ ክርስቲያን ላመኑት ላላመኑት ሁሉ ይጠቅማል፡፡ በመጨረሻም የጽድቅ አክሊልን ያቀዳጃል መንግሥተ ሰማያትን ያወርሳል፡፡ በሰውም በእግዚአብሔርም ፊት ያስከብራል፡፡
ጻድቃን ሠማዕታት ቅዱሳን በታማኝ አገልግሎታቸው ፈጣሪያቸውን ደስ አሰኝተው ከብረዋል፡፡ በሓላፊው ገንዘብ ያልታመኑት ይሁዳ፣ ሐናንያ፣ ሰጲራ፣ የደረሰባቸውን ጉዳት አይተናል፡፡ በአካን ወልደ ከርሚንም ተመሳሳይ ቅጣት ደርሶበታል ሐዋ.5፥1፣ 1፥25፡፡
ለዚህ ነበር ቅዱስ ዳዊት “አቤቱ አድነኝ ደግ ሰው አልቋልና ከሰው ልጆችም መተማመን ጎድሏልና” መዝ.11፥1፡፡ ስለዚህ ሁሉም በአለበት ያአገልግሎት መስክ ታማኝ አገልጋይ ሆኖ “አንተ በጎ ታማኝ አገልጋይ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሀለሁ” የሚለውን የጌታውን የምስጋና ቃል መስማት ይገባዋል፡፡
ታአማኝ አገልጋይ ሁነን እንድንገኝ እግዚአብሔር ይረርዳን
ለዚች ቀን ያደረሰን አምላክ የትንሳኤውንም ብርሀን ያሳየን አሜን፤፤
556 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 08:54:40 + ገብር ኄር ++
እንኩዋን ለአብይ ፆም 6ተኛ ሳምንት
ገብረ ሄር በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ
“መኑ ውእቱ ገብር ኄር” “ታማኝ አገልጋይ ማነው”? ማቴ.24፥45

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስያሜ የዐቢይ ጾም ስድስተኛው እሑድ ወይም ሳምንት ገብር ኄር ይባላል፡፡ ሰያሜውን የሰጠውም ኢትዮጵያዊ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ ጾመ ድጓ በተባለው ከአምስቱ መጻሕፍቶቹ አንዱ በሆነው ጾመ ድጓ መጽሐፍ ሳምንቱን የዐቢይ ጾም ሳምንታት ስያሜዎች ከነሥርዓተ ማኅሌቱ አዘጋጅቷል፡፡ ስለዚህ በስድስተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ከዋዜማው ቅዳሜ ጀምሮ በቤተ ክርስቲያን፡- የሚዘመረው ዝማሬ፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚሰጠው ትምህርት ገብርኄርን የሚያወሳ ነው፡፡ በማቴ.25፥14-25 የተገለጸውና በዕለቱ የሚነበበው ወንጌልም የሚነግረን ይህን ነው፡፡
“አንድ ባዕለ ጸጋ ሰው ባሪያዎችን ጠርቶ ለአንዱ አምስት መክሊት ሰጠው፣ ሁለት መክሊት የሰጠውም አለ፣ አንድ መክሊትም የሰጠው አለ፡፡ ከዚህ በኋላ ወደሩቅ አገር ሄደ፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለውም ወጥቶ ወርዶ ሌላ አምስት አትርፎ አስር አደረገ፡፡ ሁለት የተቀበለውም አትርፎ አራት አደረገ፡፡ አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ መሬቱን ቆፍሮ በሻሽ ጠቅልሎ የጌታውን መክሊት ቀበራት፡፡
ከብዙ ጊዜ በኋላ ጌታቸው መጥቶ ተቆጣጠራቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለው ቀርቦ ጌታዬ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር እነሆ አምስት አተረፍኩ አለው፡፡ “ገብርኄር ወምዕመን ዘበሁድ ምዕምነ ኮንከ ዲበ ብዙህ እሰይመከ ባዕ ውስተ ፍስሐሁ ለእግዚእከ” “አንተ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” አለው፡፡ ሁለት የተቀበለውም ቀርቦ ጌታዬ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር እነሆ ወጥቼ ወርጄ ሌላ ሁለት አትርፌ አራት አድርጌአለሁ፡፡ “አንተ ታማኝ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ” አለው፡፡
አንድ መክሊት የተቀበለው ግን ቀርቦ “ጌታዬ አንተ ክፉና ጨካኝ ካልዘራህበት የምታጭድ ካልበተንህበት የምትሰበስብ እንደሆንክ ስለአወቅሁ መሬቱን ቆፍሬ ቀበርኋት እነኋት መክሊትህ” አለው፡፡ “አንተ ሰነፍ ባሪያ መክሊቴን በጊዜ ልትሰጠኝ በተገባህ ነበር እኔም ወጥቶ ወርዶ ለሚያተርፍ በሰጠሁት ነበር”፡፡
ንዑ የዚህን ሀኬተኛ መክሊት ውሰዱና አስር መክሊት ላለው ስጡት፡፡ ላለው ይሰጡታል ይጨመርለታል ለሌለው ግን ያለውን ይቀሙታል፡፡ ንዑ ይህን ሰነፍና ሃኬተኛ ባሪያ እጅ እግሩን አሥራችሁ ጽኑዕ ጨለማ ወደአለበት ውሰዱት ጩኸትና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ጨምሩት” አለ ማቴ.25፥14-25፡፡
ባዕለ ጸጋ የተባለው ጌታ ነው፡፡ መክሊት የተባለው ልዩ ልዩ የአገልግሎት ጸጋ ነው፡፡ ያተረፉት በሚገባ በታማኝነት ያገለገሉ ቅዱሳን ሰዎች ናቸው መክሊቱን የቀበረው ደግሞ በታማኝነት በተሰጠው ጸጋ ማገልገል ሲገባው ያላገለገለ ነው፡፡ ጌታቸው ሊቆጣጠራቸው መጣ ማለት በዕለተ ምጽአት ለሁሉም በአገለገለው አገልግሎት ዋጋ ለመስጠት እንደሚመጣ ያሳየናል፡፡
ያገለገሉትን ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አላቸው ማለት ታማኝ አገልጋዮች መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉና፡፡ ሰነፎች ደግሞ ጥርስ ማፋጨት ስቃይ ጽኑዕ ጨለማ ባለበት ሲዖል መግባታቸውን የሚያሳይ ነው፡፡
ከላይ ያነሳነው የቅዱስ ወንጌል ቃል፡- “ታማኝ አገልጋይ ማነው”? ይህ እያንዳንዱ በአርዓያ እግዚአብሔር የተፈጠረ የሰው ልጅ ጥያቄ ነው የዚህን አምላካዊ ጥያቄ መልስ መስጠት ከሰው ልጆች ይጠበቃል፡፡
1. ታማኝ አገልጋይ ማነው? ሙሴ ነው፡፡
ሙሴ ታማኝ አገልጋይ ነበር ታማኝ አገልጋይ መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍት ይመሠክራሉ፡፡ “በመካከላችሁ ነቢይ ቢኖር እኔ እግዚአብሔር በራእይ እገለጥለታለሁ ወይም በህልም አናግረዋለሁ ባሪያዬ ሙሴ ግን እንዲህ አይደለም እርሱ በቤቴ ሁሉ የታመነ ነው” ዘኁ.12፥6፡፡ ይህ የፍጡር ምስክርነት ሳይሆን በፈጣሪው የተሰጠ ምስክርነት ነው፡፡ በዕውኑ በዘመናችን እንኳን ፈጣሪ ፍጡራን ታማኝነቱን የሚመሰክሩለት አጋልጋይ ይኖር ይሆን? እንጃ የሙሴን ታማኝ አገልጋይነት በረሃ፣ ስደት፣ መከራ፣ የፈርዖን ግርማ እና ቁጣ ያልበገረው አርባ ዓመት ስለ ወንድሞቹ በመሰደድ አርባ ዓመት ደግሞ የተሰደደላቸው ወንድሞቹን በመምራት ባሕር በመክፈል፣ ጠላት በመግደል፣ መና በማውረድ ደመና በመጋረድ ውኃ ከዓለት አፍልቆ በማጠጣት መከራውን ከወገኖቹ ጋር በመቀበል የቀኑ ሀሩር የሌሊቱን ቁር/ ብርድ/ ታግሶ በታማኝነት አገልግሏል፡፡ ታማኝነቱ እስከሞት ነበር፡፡
“ሙሴም ወደ እግዚብሔር ተመልሶ ወዮ እኒህ ሕዝብ ታላቅ ኀጢአት ሠርተዋል፡፡ ለራሳቸውም የወርቅ አማልክት አድርገዋል፡፡ አሁን ይህን ኀጢአታቸውን ይቅር በላቸው ያለዚያ ግን ከጻፍከው መጽሐፍ እባክህ ደምስሰኝ ከባለሟልነትህ አውጣኝ /ዘጸ.32፥31፡፡ አያችሁ ታማኝ አገልጋይ እኔ ልሙት ሌሎች ይዳኑ የሚል ነው አሁን የምናየው ግን ፈጽሞ ከዚህ የተለየ ነው፡፡ ሰዎች ይሙቱ እኔ ልኑር ሰዎች ጦም ይደሩ እኔ ልብላ ሰዎች ይራቆቱ እኔ ልልበስ ሰዎች ይዘኑ እኔ ልደሰት ነው፡፡ ይህ ታማኝ አገልጋይ ያለመሆን መገለጫ ነው፡፡ ታማኝ አገልጋይ ለሚያገለግላቸው ሰዎች ጥቅም ቅድሚያ የሚሰጥ እንጂ የራሱን ጥቅም የሚያስቀድም አይደለም፡፡ ዛሬ በዓለማችን የምንመለከተው ግን “ጩኸት ለአሞራ መብል ለጅግራ” የሚባለውን መሰል ነው፡፡ በታማኝ አገልጋዮች ድካም የሚሸለሙ ታማኝ አገልጋዮች በሠሩት ሪፖርት የሚያቀርቡ፣ የሚወደሱ ከጥቅሙ እንጂ ከድካሙ መክፈል የማይሹ እንቅፋት የሚመታው እግርን ነው፡፡ አክሊል የሚቀዳጀው ግን ራስ ነው፡፡ ታማኝ አገልጋይ ማለት እንደራስ አክሊል ዘውድ የሚጸፋ ብቻ ሳይሆን እንደ እግር እንቅፋቱን፣ እሾሁን፣ መከራውን ውጣ ውረዱን ድካሙን የሚቀበል ነው፡፡ በጥቅም ጊዜ ለራሱ በአካፋ የሚዝቅ ሌሎች በጭልፋ የሚቆነጥር አይደለም፡፡ ሙሴ ባሕር የከፈለው መና ያወረደው ደመና የጋረደው ውኃ ያፈለቀው ለራሱ አልነበረም ለሚመራቸው ሕዝብ ነበር እንጂ፡፡ ታማኝ አገልጋይ ያሰኘውም ይኸው ነው፡፡ በዚህ ከብሮበታል ተመስግኖበታልም፡፡
2. ታማኝ አገልጋይ ማነው? ዳዊት ነው፡፡
ዳዊት ዘመነ መሳፍንት አልፎ ዘመነ ነገሥት ሲተካ እስራኤልን በንጉሥነት እንዲያገለግል እግዚአብሔር ከበግ ጥበቃ መርጦ በተሰጠው ሥልጣን ያልተመነ የሳዖልን በትረ መንግሥት በሳሙኤል እጅ ተቀብቶ ተቀብሏል፡፡
በተሰጠው ሥልጣን በታማኝነት ሕዝበ እስራኤልን መርቷል፡፡ ታማኝነቱንም እግዚአብሔር ለሙሴ እንደ መሰከረለት ለእርሱም መስክሮለታል፡፡
“እግዚአብሔር እንደልቡ የሆነ ሰው መርጧልና” የዘይቱን ቀንድ ሞልተህ በልጆቹ መካከል ለእኔ ንጉሥ አዘጋጅቻለሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተልሔም እልክሃለሁ” 1ሳሙ.13፥13፣ 16፥2፡፡
“ወረከብክዎ ለዳዊት ገብርየ ወቀባዕክዎ ቅብዐ ቅዱስ” እንዲል መዝ.88፥20፡፡ “ባሪያዬ ዳዊትን አገኘሁት የተቀደሰ ዘይትንም ቀባሁት” ይህን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ሰዓታት በተባለው ድርሰቱ፡- “ረከብክዎ ለዳዊት ገብርየ ብዕሴ ምዕመነ ዘከመልብየ” አገልጋዬ ዳዊትን እንደ ልቤ የታመነ ሰውን ሆኖ አገኘሁት ሲል ተርጉሞታል፡፡ የተገኘው በታማኝነት ነበር ከነገሠ በኋላም ታማኝ ነበር አሁን በዚህ ዓለም የምንኖር እኛ ግን በድኅነት ታማኝ እንሆንና ሀብት ሹመት ሥልጣን ሲመጣ ታማኝነትን እናጣለን፤ እንዲያውም ታማኝነትን እንንቀዋለን፡፡ መስረቅ ጀግንነት ይመስለናል፡፡ መዋሸት ሥልጣኔ ይሆንልናል፡፡ ዳዊት ሳይሾም በጎቹን በመጠበቅ ታማኝ ነበር፡፡ በጎቹን የሚነጥቅ ተኩላ አንበሳ ቢመጣ በኋላው ተከትሎ ነብሩን በጡጫ አንበሳውን በእርግጫ ብሎ በጎቹን
596 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 20:53:49 ዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት "ደብረ__ዘይት"
ይህ ሳምንት የዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት እሁድ ነው።
#ደብረ__ዘይት

ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ዛፍ ያለበት ተራራ ማለት ሲሆን ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ ጥቂት ኪ.ሜ ራቅ ብሎ የሚገኝ ተራራ ነው ።

በብሉይ ኪዳን ዘመን ዳዊት ከአቤሴሎም በሸሸ ጊዜ የደብረ ዘይትን አቀበት እንደ ወጣ እናነብባለን 《2ሳሙ 15 ፥ 30》 ።

ዘሩባቤል ከሠራው ቤተ መቅደስ አደባባይ ደብረ ዘይት ሰባ አምስት ሜትር ገደማ ከፍ ብሎ ይገኛል ። ቤተ ፋጌና ቢታንያ የሚባሉት ታሪካውያን ቦታዎች ከደብረ ዘይት ግርጌ ይገኛሉ ።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሆሣዕና ዕለት ከደብረ ዘይት ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ገባ እናነብባለን ። 《ማር 1 ፥ 11》 ።
ጌታችን የጸለየበት ጌቴሴማኒ የሚባለው ቦታም ከደብረ ዘይት ሥር ይገኛል ። 《ማቴ 26 ፥ 30-36》።
ጌታችን ወደ ሰማይ ያረገው በደብረ ዘይት ላይ ነው ።《ሉቃ 24 ፥52》 ። 《ሐዋ 1 ፥ 12》
መድኃኒታችን በደብረ ዘይት ተራራ በዓለም ፍጻሜ ዓለሙን ለማሳለፍ እንንደሚመጣ ተተንብዮአል ።《ዘካ 14 ፥ 4》
መድኃኒታችንም ነገረ ምጽአቱን《ዳግም ምጽአቱን》በደብረ ዘይት ተራራ ላይ በሰፊው አስተምሯል ።《ማር 13 ፥ 3》።
በመሆኑም 5ኛው የዓቢይ ጾም ሰንበት የክርስቶስ ነገረ ምጽአት የሚታሰብበት ፥ የሚሰበክበት ፥ የሚዘመርበት፣ ዕለት ስለ ሆነ በደብረ ዘይት ተሰይሟል ። ስያሜው የቅዱስ ያሬድ ነው በዚህ ዕለት የሚነበበው የወንጌል ክፍል《ማቴ 24 ፥ 1-36》ነው ።

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመቅደስ ወጥቶ ወደ ደብረ ዘይት በሄደበት ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ አጠገቡ ቀርበው ዘሩባቤል ያሳነጸውን የመቅደስ ግንቦች እያሳዩት ሳለ ‹‹እውነት እላችኋለሁ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም›› አላቸው፡፡ ከዚህ በኋላ የኢየሩሳሌምን መፍረስ የእርሱን ዳግም መምጣት አስፍቶ አምልቶ ከነምልክቱ አስተማራቸው ።
651 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-12 03:43:37 የተሸከመህን አልጋ ተሸክመህ ሂድ

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን የዓብይ ፆሞ 4ኛ ሳምንት #መጻጉዕ ይባላል።
መፃጉዕ ማለት፦ ድውይ, ህመምተኛ ማለት ነው። በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ የተያዘ ማለት ነው።
ይህ ሳምንት ጌታ ኢየሱስ ህሙማን መፈወሱን ሙት ማስነሳቱን የሚዘክር ሳምንት ነው።
በኢየሩሳሌም በበሮች አጠገብ በእብራይስጥ ቤተሳይድ የምትባል አንዲት መጥመቂያ ነበረች አምስትም መመለሻ ነበረባት በዚህ ውስጥ የውሃውን መነረቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞች እውራኖችና አንካሶች ሰውነታቸው የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር።

አንድ አንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውሃውን ያናውጠው ነበር። እንግዲህ ከውሃ መናወጥ በኋላ በመጀመርያ የገባ ከማናቸውም ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆናል።

በዚያም ከሰላሳ ስምንት አመት በላይ የታመመ አንድ ሰው ነበር እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲህ እንደነበር አውቆ የኢየሱስም ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ ቀርቦ ልትድን ትወዳለህ አለው?

ደውይውም ጌታ ሆይ ውሃ በተናወጠ ጊዜ ወደ መጠመቂያው ደስዶ የሚያኖረኝ ሰው የለም አለው ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት። ኢየሱስም ተነስና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው።ወዲያውኑ ሰውየውም ዳነ አልጋውን ተሸክሞ ሄደ።

ያም ቀን ሰንበት ነበር አይሁድም የተፈወሰውን ሰው ሰንበት ነው አልጋህንም ልትሸከም አልተፈቀደልህም አሉት።

እርሱ ግን ያዳነኝ ያለው ሰው አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ ብሎ መለሰላቸው። እነርሱም አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ያለህ ያለ ሰው ማነው ብለው ጠየቁት ዳሩ ግን በዚያ ስፍራ ሕዝብ ስለነበሩ ኢየሱስ ፈቁቅ ብሎ ነበርና የተፈወሰው ሰውማን እንደሆነ አላወቀም። ዮሐ, 5፡2-13

እግዚአብሔር እኛንም ከተያዝንበት የክፋት ህመም በያለንበት ይፈውሰን አሜን!!!
656 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 00:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-04 21:06:27 #ምኩራብ"

የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሰንበት (እሑድ) ምኩራብ ይባላል፦ ስያሜውን ያገኘው ጌታችን በአይሁድ ቤተ-መቅደስ ተገኝቶ ቤተ-መቅደስ ንጹህ የእግዚአብሔር ቤት፣ የጸሎት ቤት፣ ሃይማኖትና ጽድቅ የሚነገርበት የተቀደሰ/የተለየ ቦታ መሆኑን ያረጋገጠበት ስለሆነ ነው።

ሊቁም "ቦአ ኢየሱስ ምኩራቦሙ ለአይሁድ ወመሀረ ቃለ ሃይማኖት" በማለት ጌታችን ወደ ቤተመቅደሱ የገባ ክህደትና ዓለማዊነትን አስወግዶ ሃይማኖትና ጽድቅን ለማስተማር መሆኑን ያስረዳናል።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በይፋ የታወቀ የመጀመሪያ ተአምራቱን በመግለጥ በገሊላ ቃና ክብሩን ሲገልጥ ደቀ መዛሙርቱም ሆነ ሌሎች በእርሱ አምነዋል። በቅፍርናሆም ጥቂት ቀን ከተቀመጠ በኋላ የአይሁድ ፋሲካ ቀርቦ ስለነበር በቀጥታ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ በዘሩባቤል ዘመን ተሠርቶ በሄሮድስ ዕድሳት ወደ ተደረገለት ቤተ መቅደስ ሄዷል።

በመቅደሱም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው ሲያገኝ የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ በማስወጣት የለዋጮችንም ገንዘብ በማፍሰስ ገበታዎቻቸውንም ገልብጧል፥ ርግብ ሻጪዎችንም፦ ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት ሲል ደቀ መዛሙርቱ የቤትህ ቅናት ይበላኛል የሚለው ትዝ እንዳላቸው በመጽሐፉ ተጠቅሶ አግኝተነዋል።

#በሦስተኛው ቀን የተገነባው ሕያውና ዘለዓለማዊ ቤተ መቅደስ ሲሆን፣ የ46 ዐመቱ የንግድ ቤት ግን ፈርሷል!

አይሁድም ይህን ስለምታደርግ ምን ምልክት ታሳየናለህ? ባሉት ጊዜ፣ ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ ሲላቸው፣ ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ የነበረ፥ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን? አሉት፤ እርሱ ግን ስለ ሕንጻው ሳይሆን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስነት ሲነግራቸው ነበር። እርሱ በሦስተኛው ቀን ከሞት ተነሥቶ ሕያውና ዘለዓለማዊ ቤተ መቅደሱ ሲገነባ፣ ለዕድሳት 46 ዓመት የፈጀ የእነርሱ ቤት ግን እንደተነበየው በ70 ዓ∙ም በሮማውያን እጅ እንደፈረሰ ሊቃውንት ይመሰክራሉ።

#በሦስተኛው ቀን የተገነባው ሕያውና ዘለዓለማዊ ቤተ መቅደስ #የክርስቶስ_ሰውነት (አካል) ነው።

ቤቱ የንግድ ቤት አድርገውት እንደነበረ በመጽሐፉ ተገልጿል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት ብሎ ቤቱ የጸሎት እንጂ የንግድ ቤት እንዳልሆነ ሲነግራቸው በሌላ በኩልም አማናዊ መቅደስ እርሱ ራሱ እንደሆነ ሳይናገራቸው አላለፈም። ለዚህም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ "እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር" (ዮሐ 3:21) በማለት ያረጋግጥልናል።

በተጨማሪም “ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክና በጉ መቅደስዋ ናቸውና መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም፤ ለከተማይቱም የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት መብራትዋም በጉ ስለ ሆነ፥ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር። (ራእ 21÷22-23) ሲል አሁንም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በራዕይ ያየው ጽፎልናል። በሌላ በኩልም ቤተክርስቲያን የክርስቶስ አካል ስለሆነች ሕያውና ዘለዓለማዊት ናት።

#ለእግዚአብሔር_ቤት ልባዊ ቅናት ይኑረን!

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት ሲል በመቅደሱ የነበሩትን የሥጋ ሥራዎችን ሁሉ እንዳስወገደ፣ አሁንም ከቤተ መቅደሱ የማያስፈልጉትን ሁሉ በጊዜው ማስወገድ ያስፈልጋል።

ቤተ-መቅደሱን እርሱ ብቻ ይንገሥበት። ቤቱ የመንፈስ ቅዱስ ቤት ስለሆነ አለማመን፣ ጥርጥር፣ ዝሙት፥ ርኵሰት፥ መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፣ ክህደት፣መገዳደል፣ ሐሜት ትምክህት ወዘተ ከቅዱስ ቤቱ ተወግደው ቤተ መቅደሱ ንጹሕ አምልኮ፣ ምሥጋናና ጸሎት የሚቀርብበት ሊሆን ይገባል። እንዲሁም በቅዱስ ቤቱ ፍቅር፥ ይቅርታ፣ ደስታ፥ ሰላም፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውኃት፥ ራስን መግዛትና ርህራሄም ሊነግሥ ይገባል።

ከዚህም ጋር አማኞች ሁላችን በሥጋችን እግዚአብሔርን ማክበር አለብን። የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ መሆናችንን መዘንጋት የለብንም። የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ደግሞ ንጹሕ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔርን በሥጋችን ማክበር አለብን።

ሐዋርያው ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስም "የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።"፤ ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።" በማለት ይመክረናል (1ቆሮ. 3፥16-17፤ 6:19-20)።

በሁለንተናዊ ኑሯችን አምላካችንን አክብረን እንደ ፈቃዱ እንድንኖር እርሱ ይርዳን!
414 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ