Get Mystery Box with random crypto!

ዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት 'ደብረ__ዘይት' ይህ ሳምንት የዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት እሁድ ነው | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

ዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት "ደብረ__ዘይት"
ይህ ሳምንት የዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት እሁድ ነው።
#ደብረ__ዘይት

ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ዛፍ ያለበት ተራራ ማለት ሲሆን ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ ጥቂት ኪ.ሜ ራቅ ብሎ የሚገኝ ተራራ ነው ።

በብሉይ ኪዳን ዘመን ዳዊት ከአቤሴሎም በሸሸ ጊዜ የደብረ ዘይትን አቀበት እንደ ወጣ እናነብባለን 《2ሳሙ 15 ፥ 30》 ።

ዘሩባቤል ከሠራው ቤተ መቅደስ አደባባይ ደብረ ዘይት ሰባ አምስት ሜትር ገደማ ከፍ ብሎ ይገኛል ። ቤተ ፋጌና ቢታንያ የሚባሉት ታሪካውያን ቦታዎች ከደብረ ዘይት ግርጌ ይገኛሉ ።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሆሣዕና ዕለት ከደብረ ዘይት ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ገባ እናነብባለን ። 《ማር 1 ፥ 11》 ።
ጌታችን የጸለየበት ጌቴሴማኒ የሚባለው ቦታም ከደብረ ዘይት ሥር ይገኛል ። 《ማቴ 26 ፥ 30-36》።
ጌታችን ወደ ሰማይ ያረገው በደብረ ዘይት ላይ ነው ።《ሉቃ 24 ፥52》 ። 《ሐዋ 1 ፥ 12》
መድኃኒታችን በደብረ ዘይት ተራራ በዓለም ፍጻሜ ዓለሙን ለማሳለፍ እንንደሚመጣ ተተንብዮአል ።《ዘካ 14 ፥ 4》
መድኃኒታችንም ነገረ ምጽአቱን《ዳግም ምጽአቱን》በደብረ ዘይት ተራራ ላይ በሰፊው አስተምሯል ።《ማር 13 ፥ 3》።
በመሆኑም 5ኛው የዓቢይ ጾም ሰንበት የክርስቶስ ነገረ ምጽአት የሚታሰብበት ፥ የሚሰበክበት ፥ የሚዘመርበት፣ ዕለት ስለ ሆነ በደብረ ዘይት ተሰይሟል ። ስያሜው የቅዱስ ያሬድ ነው በዚህ ዕለት የሚነበበው የወንጌል ክፍል《ማቴ 24 ፥ 1-36》ነው ።

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከመቅደስ ወጥቶ ወደ ደብረ ዘይት በሄደበት ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ አጠገቡ ቀርበው ዘሩባቤል ያሳነጸውን የመቅደስ ግንቦች እያሳዩት ሳለ ‹‹እውነት እላችኋለሁ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም›› አላቸው፡፡ ከዚህ በኋላ የኢየሩሳሌምን መፍረስ የእርሱን ዳግም መምጣት አስፍቶ አምልቶ ከነምልክቱ አስተማራቸው ።