Get Mystery Box with random crypto!

የተሸከመህን አልጋ ተሸክመህ ሂድ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን የዓብይ ፆሞ 4ኛ ሳምንት #መ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

የተሸከመህን አልጋ ተሸክመህ ሂድ

እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን የዓብይ ፆሞ 4ኛ ሳምንት #መጻጉዕ ይባላል።
መፃጉዕ ማለት፦ ድውይ, ህመምተኛ ማለት ነው። በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ የተያዘ ማለት ነው።
ይህ ሳምንት ጌታ ኢየሱስ ህሙማን መፈወሱን ሙት ማስነሳቱን የሚዘክር ሳምንት ነው።
በኢየሩሳሌም በበሮች አጠገብ በእብራይስጥ ቤተሳይድ የምትባል አንዲት መጥመቂያ ነበረች አምስትም መመለሻ ነበረባት በዚህ ውስጥ የውሃውን መነረቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞች እውራኖችና አንካሶች ሰውነታቸው የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር።

አንድ አንድ ጊዜ የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውሃውን ያናውጠው ነበር። እንግዲህ ከውሃ መናወጥ በኋላ በመጀመርያ የገባ ከማናቸውም ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆናል።

በዚያም ከሰላሳ ስምንት አመት በላይ የታመመ አንድ ሰው ነበር እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲህ እንደነበር አውቆ የኢየሱስም ይህን ሰው ተኝቶ ባየ ጊዜ ቀርቦ ልትድን ትወዳለህ አለው?

ደውይውም ጌታ ሆይ ውሃ በተናወጠ ጊዜ ወደ መጠመቂያው ደስዶ የሚያኖረኝ ሰው የለም አለው ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት። ኢየሱስም ተነስና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው።ወዲያውኑ ሰውየውም ዳነ አልጋውን ተሸክሞ ሄደ።

ያም ቀን ሰንበት ነበር አይሁድም የተፈወሰውን ሰው ሰንበት ነው አልጋህንም ልትሸከም አልተፈቀደልህም አሉት።

እርሱ ግን ያዳነኝ ያለው ሰው አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ ብሎ መለሰላቸው። እነርሱም አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ያለህ ያለ ሰው ማነው ብለው ጠየቁት ዳሩ ግን በዚያ ስፍራ ሕዝብ ስለነበሩ ኢየሱስ ፈቁቅ ብሎ ነበርና የተፈወሰው ሰውማን እንደሆነ አላወቀም። ዮሐ, 5፡2-13

እግዚአብሔር እኛንም ከተያዝንበት የክፋት ህመም በያለንበት ይፈውሰን አሜን!!!