Get Mystery Box with random crypto!

ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የሰርጥ አድራሻ: @wdasemaryam
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18
የሰርጥ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን።
በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
መራግብራችን👇👇
✅የበገና መዝሙሮች
✅ የንስሐ መዝሙሮች
✅ ያሬዳዊ ዜማ
✅ ስብከቶች
✅ መፅሐፍ ሀይማኖት....የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
አስተምህሮትን በተመለከተ፤ ስለ መላእክት፤ስለ ቅዱሳን፤ ያገኙበታል።

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-11-29 18:48:12 ✞________«ሰው እናታችን ጽዮን ይላል»________✞
«እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ፥ ወብእሲ ተወልደ በውስቴታ፤ ወውእቱ ልዑል ሣረራ። ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጧም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።» ይላል። መዝ ፹፮፥፭። ቅዱስ ዳዊት ጽዮንን እናት ብሏታል። እናት፦ ወላጅ፥ መገኛ፥የአባት ሁለተኛ ናት። እግዚአብሔር በአሠርቱ ትእዛዛት፦ «አክብር አባከ ወእመከ፤ ከመ ይኩንከ ጽድቀ፥ ወይኑኅ መዋዕሊከ በውስተ ምድር ዘይሁበከ እግዚአብሔር አምላክከ። አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ (ቸርነቱ ረድኤቱ ይደረግልህ ዘንድ) ፥ እግዚአብሔር አምላክህ በሚስጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም፤ » እንዳለ፦ እናት ከአባት እኲል ክብር ይገባታል። ዘጸ ፳ ፥፲፪። ጽዮን ማለት ደግሞ አምባ መጠጊያ ማለት ነው።
ጽዮን ማርያም ፤
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም «ጽዮን» ተብላ ትጠራለች። ምክንያቱም ጽዮን ማለት አምባ መጠጊያ ማለት እንደ ሆነ ሁሉ እመቤታችንም፦ ለነፍስና ለሥጋ ፥ለኃጥአንና ለጻድቃን፥ አምባ መጠጊያ ናትና። ቅዱስ ዳዊት፦ «እስመ ኀረያ እግዚ አብሔር ለጽዮን ፥ ወአብደራ ከመ ትኩኖ ማኅደሮ ፥ ዛቲ ይእቲ ምእራፍየ ለዓለም፤ ዝየ አኅደር እስመ ኅረይክዋ። እግዚአብሔር ጽዮን መርጧታልና ፥ ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና ፥ ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።» ያለው እመቤታችንን ነው። መዝ ፩፻፴፮ ፥ ፲፫። ምክንያቱም ፦ ለእናትነት መርጦ ያደረው በእርሷ ማኅፀን ነውና። «ለ ዘላለም መረፊያዬ ናት፤» ማለቱም፦ እርሱ የዘለዓለም አምላክ እንደሆነ ፥ እርሷም ለዘለዓለም ወላዲተ አምላክ ተብላ እንደምትኖር የሚያመለክት ነው። በሌላ ምዕራፍም፦ « ደብረ ጽዮን ዘአፍቀረ ፥ ሐነፀ መቅደሶ በአርያም ፥ወሳረረ ውስተ ምድር ዘለዓለም። የወደ ደውን የጽዮንን ተራራ ፥ መቅደሱን እንደ አርያም ሠራ። ለዘለዓለምም በምድር ውስጥ መሠረታት።» ብሏል። መዝ ፸፯፥፷፰።
ጽርሐ አርያም ከሰባቱ ሰማያት አንዱ ነው። በዚያ፦ ኪሩቤል የሚሸክሙት ፥ ሱራፌል የሚያጥኑት የእግዚአብሔር የእሳት ዙፋን አለ። ዙፋኑም በሰባት የእሳት መጋረጃዎች የተጋረደ ነው። ኢሳ ፮፥፩ ፣፪ኛ ሳሙ ፬፥፬ ፣ ሕዝ ፩፥፭-፲፰ ፣ ራእ ፬፥፮-፱። ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን ድርሰቱ፦ እመቤታችንን፦ «በሰማይ ባለ ጽርሐ አርያም ፈንታ በምድር ላይ አርያምን ሆንሽ፤» ብሏታል። ከ ዚህም፦ ቅዱስ ዳዊት «የወደደውን የጽዮንን ተራራ፥ መቅደሱን እንደ አርያም ሠራ፤» ያለው ለእመቤታችን እንደሆነ እንረዳለን።
ድንግልናዋን በተመለከተም፦ «ትሴብሖ ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ፥ ወሰብሒዮ ለአምላክኪ ጸዮን ፥ እስመ አጽንዐ መናግሥተ ኆኃትኪ ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ እግዚአብሔርን አመስግኚ ፥ ጽዮንም ሆይ አምላክሽን አመስግኚ ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፤» ብሏል። መዝ ፩፻፵፯፥፩። ይህም ፦ ለጊዜው ለከተማይቱ ሲሆን ለፍጸሜው ለእመቤታችን ነው። ይኸውም ይታወቅ ዘንድ ኢየሩሳሌም ፥ ጽዮን ፥ የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፦ በመንፈስ ቅዱስ ግብር አምላክን በድንግልና በፀነ ሰች ጊዜ፦ «ሰውነቴ እግዚአብሔርን ታከብረዋለች። ልቡናዬም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች።» በማለት አመስግናለች። ሉቃ ፩፥፵፮። የእርሷ ሰውነት፦ የሥጋን ንጽሕና ፥ የልብን ንጽሕና ፥ የነፍስን ንጽሕና ፥ አስተባብራ አንድ አድርጋ ይዛ የተገኘች ናት። «የዶጆችሽን መወርወሪያ አጽንቷልና፤» የተባለውም ዘለዓለማዊ ድንግልናዋን ነው። እመቤታችን፦ ቅድመ ወሊድ ፥ ጊዜ ወሊድ ፥ ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና። ይኽንንም ነቢዩ ኢሳይያስ፦ «እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ፤ ወንድ ልጅም (ወልድን) ትወልዳለች ፤ ስሙ ንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።» በማለት ተናግሯል። ኢሳ ፯፥፲፬። ነቢዩ ሕዝቅኤልም፦ «ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በስ ተውጭ ወዳለው በር መለሰኝ፤ ተዘግቶም ነበር። እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ ይህች በር ተዘግታ ትኖራለች እንጂ አትከፈትም፤ (ድንግል ማር ያም ለዘለዓለም በድንግልና ጸንታ ትኖራለች)። ሰውም አይገባባትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶባታልና ተዘ ግታ ትኖራለች። (አምላክ በማኅፀኗ ተፀንሶ፥ ከእርሷ ተወልዷልና በድንግልና ጸንታ ትኖራለች)።» ብሏል። ሕዝ ፵፬፥፩-፪።
ደብረ ጽዮንና ታቦተ ጽዮን ምሳሌዋ የሆኑላት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ዳዊት እንደተናገረላት፦ ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላታል። ይህም ይታወቅ ዘንድ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፥ ድኅነተ ዓለምን በመስቀል ላይ በፈጸመ ጊዜ ፥ ወዳጁን ቅዱስ ዮሐንስን፦ «እነኋት እናትህ፤» ብሎታል። ዮሐ ፲፱፥፳፭።
✞✞✞✞✞ሰናይ ሚዲያ✞✞✞✞✞

Share


https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw
611 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 18:48:00
507 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-27 13:19:55

228 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 07:01:51 #ጾመ_ነቢያት

እግዚአብሔር አምላካችን ዓለምን ለማዳን ሲል የሰውን ሥጋ መልበሱን፣ ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ወደ ግብጽ ግብር መሰደዱን፣ በባሕረ ዮርዳኖስ መጠመቁን፣ በትምህርቱ ብርሃንነት ጨለማውን ዓለም ማብራቱን፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ሲል ልዩ ልዩ ዓይነት መከራ መቀበሉን፣ መሰቀሉን፣ መሞቱን፣ ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን፣ ማረጉንና ዳግም ለፍርድ የሚመጣ መኾኑን በአጠቃላይ የማዳን ሥራውን በየዘመናቱ የተነሡ ቅዱሳን ነቢያት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው አስቀደመው በትንቢት ተናግረዋል፡፡ ትንቢቱ ተፈጽሞ ለመመልከትም ‹‹አንሥእ ኃይለከ ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሣ፤ እጅህን ላክ›› እያሉ በጾም በጸሎት ተወስነው አምላክ ሰው ኾኖ ዓለምን የሚያድንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት እያሰሉ ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ የእግዚአብሔርን ሰው መኾን ሲጠባበቁ የኖሩት የነቢያት ትንቢትና ጸሎትም በእግዚአብሔር ሰው መኾን ፍጻሜ አግኝቷል፡፡

ይህን ምሥጢር በማሰብ በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ቀን ጀምሮ እስከ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት ዋይዜማ ድረስ እንድንጾም አባቶቻችን መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሠርተውልናል፡፡ ይህ ጾም፣ ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ሲኾን፣ በስያሜም #ጾመ_ነቢያት (የነቢያት ጾም) እየተባለ ይጠራል፡፡ ወቅቱ ለአዳም የተነገረው የድኅት ተስፋ የተፈጸመበት ስለ ኾነም #ጾመ_አዳም (የአዳም ጾም) ይባላል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ሰው መኾን በስፋት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ወቅት በመኾኑም #ጾመ_ስብከት (የስብከት ጾም) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት በመኾኑ ደግሞ #ጾመ_ልደት (የልደት ጾም) በመባል ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም #ጾመ_ሐዋርያት እየተባለ ይጠራል፤ ምክንያቱም ቅዱሳን ሐዋርያት "በዓለ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብረዋለን፤ በዓለ ልደትንስ ምን አድርገን እናከብረዋለን?" በማለት ነቢያት በጾሙበት ማለት ከልደተ ክርስቶስ በፊት ባለው ወቅት ጾመዋልና፡፡

በሌላ አጠራር ይኸው ጾመ ነቢያት #ጾመ_ፊልጶስ (የፊልጶስ ጾም) በመባል ይታወቃል፤ ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአፍራቅያ እና አውራጃዋ ዅሉ እየተዘዋወረ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወንጌልን በማስተማር፣ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን በማድረግ ብዙዎችን ወደ አሚነ እግዚአብሔር ሲመልስ ቆይቶ ትምህርቱን በማይቀበሉ የአፍራቅያ ሰዎች አማካይነት በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሥጋውን ሊቀብሩ ሲሉም ተሰወረባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ በዓት ዘግተው፣ ሱባዔ ገብተው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው የሐዋርያውን ሥጋ ይመልስላቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ቢለምኑት ልመናቸውን ተቀብሎ ሱባዔ በያዙ በ፫ኛው ቀን የቅዱስ ፊልጶስን ሥጋ (በድን) መልሶላቸው በክብር አሳርፈውታል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ የሐዋርያውን ሥጋ ካገኙ በኋላ እስከ ጌታችን ልደት ድረስ ጾመዋል፡፡ ስለዚህም ጾመ ነቢያት 'ጾመ ፊልጶስ' እየተባለ ይጠራል፡፡

ከዚሁ ዅሉ ጋርም ወልደ አምላክ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንሰው፣ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካበሠራት በኋላ "ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ?" በማለት ጌታችንን ከመውለዷ አስቀድማ እመቤታችን ጾማዋለችና ይህ ጾም #ጾመ_ማርያም በመባልም ይታወቃል፡፡ በአጠቃላይ በዚህ በጾመ ነቢያት፣ ነቢያትም ሐዋርያትም፣ ቀደምት አባቶቻችንም ጾመው በረከት አግኝተውበታል፡፡ እኛ ምእመናንም የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት አምላክ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከቅዱሳን ነቢያትና ሐዋርያት በረከት እንዲያሳትፈን በዚህ በጾመ ነቢያት ወቅት በጾም በጸሎት ተወስነን እግዚአብሔርን ልንማጸነው ይገባናል፡፡

ጾሙን ጾመ ሥርየት ፤ ጾመ መድኃኒት ያድርግል!

ምንጭ፡–
-ማኅበረ ቅዱሳን ብሎግ
ፍትሐ ነገሥት ንባቡና ትርጓሜው፣ አንቀጽ ፲፭

Share


https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw
521 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 07:01:37
480 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 13:50:20 ✙✙✙ እንኳን ለቅዱስ #ሚካኤል ዓመታዊ #በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ✙✙✙

✙ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል፡፡

(ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በሚባለው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡)

#የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡

✙ እንዲሁም ይህ ዕለት ቅዱስ ሚካኤል ሕዝበ እስራኤልን ከግብፅ ምድር ጀምሮ ከነዓን እስኪገቡ ድረስ እየመራ እየጠበቀ አብሯቸው በመጓዝ ምድረ ርስት እንዲገቡ ያደረገበት መታሰቢያ ነው:: በዚሁ ዕለት በመጽሐፈ ኢያሱ 5:13 በተጠቀሰው መሠረት ቅዱስ ሚካኤል የተመዘዘ ሰይፍ በመያዝ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ ለኢያሱ ተገልጦለታል:: ኢያሱም አይቶ ሰግዶለታል:: በ እርሱ ላይ? እንዲህ ይላል:- "ሁልግዜ ከ እግዚአብሔር ዙፋን ፊት ቆሞ ለሰው ሁሉ የሚማልድ መልአክ ነው:: የነዌ ልጅ ኢያሱ በንጉሥ የጦር ቤት ወዳጅ፣ አምሳል፣ ክቡር፣ ገናና ሆኖ ያየው ይህ ሚካኤል ነው:: ባየውም ጊዜ ከግርማው የተነሣ ደነገጠ:: በግንባሩም ከምድር ላይ ወድቆ ሰገደለት:: ጌታዬ ሆይ ከሰማይ ሠራዊት ወገን አንዱ ከአለቆች አንዱ ነኝ"፡ብሎ ቅዱስ ሚካኤል መለሰለት::


✙✙✙ ተራዳኢው መልአክ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ህዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት እየመራ ወደ ከነአን እንዳስገባቸው በስደት በባዕድ ሃገር የሚሰቃዩትን ወገኖቻችንን እየመራ ወደ ሃገራችን ያስገባልን! ጥላ ከለላ ሆኖ ይጠብቅልን! እኛንም ዛሬ ከተያዝንበት የመለያየት እና የመከፋፈል ባርነት ወደ አንድነት፣ ወደ ሰላም ፣ ወደ ፍቅርና ዘላለማዊ ህይወትን ወደምንወርስበት ወደ ንስሃ ህይወት ይምራን!!! አማላጅነቱ እና ጥበቃው አይለየን!!!

Share


https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw
640 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 13:50:08
544 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 17:46:11
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ሥላሴ መጠጊያ ቦታዬ ሥላሴ መታመኛዬ ነው ከእናቴ ማኅፀን ጀምሮ በሥላሴ ጸንቼ እኖራለሁ። ይህን ላደረገልኝ ለሥላሴ ምን ወሮታ እከፍላለሁ። በልዩ ችሎታው ለፈጠረኝ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል። በቸርነቱ ላሳደገኝ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል። በመሐሪነቱ ጠብቆ እስከዚች ሰዓት ላደረሰኝ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል። በማዳን ችሎታው ላዳነኝ ሥላሴ ምስጋና ይገባል። እንደበደሌ ላልፈረደብኝ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል። ለጌታዬ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል። ለንጉሤ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል። ለአምላኬ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል።አሜን!
✥ሰይፈ ሥላሴ✥


T.me/wdasemaryam

https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw
802 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 06:21:10 አብሬሽ ልመለስ ድንግል አዛኝቱ እንኳን ለእመቤታችን ለጉስቋም ማርያም ለዓመት ክብሯ በሰላም አደረሳቹ
አደረሰን
ህዳር 6 በዚህች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ አንዲሁም ከዮሴፍና ሶሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ አገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው፤

ከግብጽ ሲመለሱ ጌታችን በእመቤታችን ጀረባ ላይ ሆኖ እነዚያ እውራንን ባበሩ ጣቶቹ ወደ ኢትዮጵያ ይጠቁም ያመለክት ነበር፤

እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን የምታመለክተው ብትለው"ያቺ የተባረከች አገር ናት እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ናት፤

ያንቺ ዘመዶች ሰቅለው ይገድሉኛል በዚህች አገር ያሉ ግን ሳይዩኝ ያመኑኛል፤አስራት በኩራትሽ ትሁን ብሎ ሰጥቷታል።

በቃል ኪዳን እግራቸውም ጣና ሐይቅን፣ ዋልድባንና ሌሎችንም ቦታዎች ዞረው እንደባረኩ ድርሳነ ኡራኤልና ተአምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል።

እመቤታችንን ከሐና ማህጸን ፈጥሮ ከፍጥረተ ዓለም ለይቶ ከሁሉ አልቆ የእናት አማላጅ ትሁናችሁ ብሎ የሰጠን እግዚአብሔር ይመስገን።ዳግመኛም በዛሬዋ ቀን በኢትዮጵያ ምድር ታላቅ አምድ ወደቀ ይህም የመናገሻው ባህታዊ አባ ኤልያስ ነው፤

በ400 ዓመት እድሜው ህዳር 6 1874 ዓ/ም አረፈ፤በአጼ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ማለት ነው፤ የቅርብ ጊዜ ነው ፤ ይህ አባት በግራኝ መሐመድ ወረራ ጊዜ የነበረ ነው፤

በዚያን ጊዜ በተለይ ከመናገሻ እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት እየተመላለሰ ሱባኤ እየገባ ፀሎት ያደርግ ነበር፤ በዛሬዋ ቀን ይህ አባት ሲሞት በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ከዋክብት ሲበታተኑ ሲራወጡ ታየ የተጉለቱ አባ በላይነህም ይህንን ምልክት አይቶ የአባ ኤልያስን መሞት ተረዱ ወደ መናገሻ ቢመጡ ሞቶ ተቀብሮ አገኙት፤


T.me/wdasemaryam

https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw
1.1K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 03:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-14 21:43:28
980 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ