Get Mystery Box with random crypto!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ሥላሴ መጠጊያ ቦታዬ ሥላሴ መታመኛዬ ነው | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ሥላሴ መጠጊያ ቦታዬ ሥላሴ መታመኛዬ ነው ከእናቴ ማኅፀን ጀምሮ በሥላሴ ጸንቼ እኖራለሁ። ይህን ላደረገልኝ ለሥላሴ ምን ወሮታ እከፍላለሁ። በልዩ ችሎታው ለፈጠረኝ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል። በቸርነቱ ላሳደገኝ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል። በመሐሪነቱ ጠብቆ እስከዚች ሰዓት ላደረሰኝ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል። በማዳን ችሎታው ላዳነኝ ሥላሴ ምስጋና ይገባል። እንደበደሌ ላልፈረደብኝ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል። ለጌታዬ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል። ለንጉሤ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል። ለአምላኬ ለሥላሴ ምስጋና ይገባል።አሜን!
✥ሰይፈ ሥላሴ✥


T.me/wdasemaryam

https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw