Get Mystery Box with random crypto!

አብሬሽ ልመለስ ድንግል አዛኝቱ እንኳን ለእመቤታችን ለጉስቋም ማርያም ለዓመት ክብሯ በሰላም አደረሳ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

አብሬሽ ልመለስ ድንግል አዛኝቱ እንኳን ለእመቤታችን ለጉስቋም ማርያም ለዓመት ክብሯ በሰላም አደረሳቹ
አደረሰን
ህዳር 6 በዚህች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ አንዲሁም ከዮሴፍና ሶሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ አገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው፤

ከግብጽ ሲመለሱ ጌታችን በእመቤታችን ጀረባ ላይ ሆኖ እነዚያ እውራንን ባበሩ ጣቶቹ ወደ ኢትዮጵያ ይጠቁም ያመለክት ነበር፤

እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን የምታመለክተው ብትለው"ያቺ የተባረከች አገር ናት እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ናት፤

ያንቺ ዘመዶች ሰቅለው ይገድሉኛል በዚህች አገር ያሉ ግን ሳይዩኝ ያመኑኛል፤አስራት በኩራትሽ ትሁን ብሎ ሰጥቷታል።

በቃል ኪዳን እግራቸውም ጣና ሐይቅን፣ ዋልድባንና ሌሎችንም ቦታዎች ዞረው እንደባረኩ ድርሳነ ኡራኤልና ተአምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል።

እመቤታችንን ከሐና ማህጸን ፈጥሮ ከፍጥረተ ዓለም ለይቶ ከሁሉ አልቆ የእናት አማላጅ ትሁናችሁ ብሎ የሰጠን እግዚአብሔር ይመስገን።ዳግመኛም በዛሬዋ ቀን በኢትዮጵያ ምድር ታላቅ አምድ ወደቀ ይህም የመናገሻው ባህታዊ አባ ኤልያስ ነው፤

በ400 ዓመት እድሜው ህዳር 6 1874 ዓ/ም አረፈ፤በአጼ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ማለት ነው፤ የቅርብ ጊዜ ነው ፤ ይህ አባት በግራኝ መሐመድ ወረራ ጊዜ የነበረ ነው፤

በዚያን ጊዜ በተለይ ከመናገሻ እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት እየተመላለሰ ሱባኤ እየገባ ፀሎት ያደርግ ነበር፤ በዛሬዋ ቀን ይህ አባት ሲሞት በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ከዋክብት ሲበታተኑ ሲራወጡ ታየ የተጉለቱ አባ በላይነህም ይህንን ምልክት አይቶ የአባ ኤልያስን መሞት ተረዱ ወደ መናገሻ ቢመጡ ሞቶ ተቀብሮ አገኙት፤


T.me/wdasemaryam

https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw