Get Mystery Box with random crypto!

✙✙✙ እንኳን ለቅዱስ #ሚካኤል ዓመታዊ #በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ✙✙✙ ✙ እንደ ቅዱሳን አባቶ | ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

✙✙✙ እንኳን ለቅዱስ #ሚካኤል ዓመታዊ #በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ✙✙✙

✙ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል፡፡

(ይህን ሁለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በሚባለው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡)

#የቅዱስ ሚካኤል ሹመት በነገደ መላእክት ላይ ብቻ ግን አይደለም ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በሆኑት ላይም ጭምር ነው ፡፡

✙ እንዲሁም ይህ ዕለት ቅዱስ ሚካኤል ሕዝበ እስራኤልን ከግብፅ ምድር ጀምሮ ከነዓን እስኪገቡ ድረስ እየመራ እየጠበቀ አብሯቸው በመጓዝ ምድረ ርስት እንዲገቡ ያደረገበት መታሰቢያ ነው:: በዚሁ ዕለት በመጽሐፈ ኢያሱ 5:13 በተጠቀሰው መሠረት ቅዱስ ሚካኤል የተመዘዘ ሰይፍ በመያዝ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ ለኢያሱ ተገልጦለታል:: ኢያሱም አይቶ ሰግዶለታል:: በ እርሱ ላይ? እንዲህ ይላል:- "ሁልግዜ ከ እግዚአብሔር ዙፋን ፊት ቆሞ ለሰው ሁሉ የሚማልድ መልአክ ነው:: የነዌ ልጅ ኢያሱ በንጉሥ የጦር ቤት ወዳጅ፣ አምሳል፣ ክቡር፣ ገናና ሆኖ ያየው ይህ ሚካኤል ነው:: ባየውም ጊዜ ከግርማው የተነሣ ደነገጠ:: በግንባሩም ከምድር ላይ ወድቆ ሰገደለት:: ጌታዬ ሆይ ከሰማይ ሠራዊት ወገን አንዱ ከአለቆች አንዱ ነኝ"፡ብሎ ቅዱስ ሚካኤል መለሰለት::


✙✙✙ ተራዳኢው መልአክ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ህዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት እየመራ ወደ ከነአን እንዳስገባቸው በስደት በባዕድ ሃገር የሚሰቃዩትን ወገኖቻችንን እየመራ ወደ ሃገራችን ያስገባልን! ጥላ ከለላ ሆኖ ይጠብቅልን! እኛንም ዛሬ ከተያዝንበት የመለያየት እና የመከፋፈል ባርነት ወደ አንድነት፣ ወደ ሰላም ፣ ወደ ፍቅርና ዘላለማዊ ህይወትን ወደምንወርስበት ወደ ንስሃ ህይወት ይምራን!!! አማላጅነቱ እና ጥበቃው አይለየን!!!

Share


https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw