Get Mystery Box with random crypto!

ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam

የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የቴሌግራም ቻናል አርማ wdasemaryam — ውዳሴ ማርያም/wdasemaryam
የሰርጥ አድራሻ: @wdasemaryam
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 18
የሰርጥ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን።
በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
መራግብራችን👇👇
✅የበገና መዝሙሮች
✅ የንስሐ መዝሙሮች
✅ ያሬዳዊ ዜማ
✅ ስብከቶች
✅ መፅሐፍ ሀይማኖት....የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
አስተምህሮትን በተመለከተ፤ ስለ መላእክት፤ስለ ቅዱሳን፤ ያገኙበታል።

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-11-14 21:43:17 አብሬሽ ልመለስ ድንግል አዛኝቱ እንኳን ለእመቤታችን ለጉስቋም ማርያም ለዓመት ክብሯ በሰላም አደረሳቹ
አደረሰን
ህዳር 6 በዚህች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ አንዲሁም ከዮሴፍና ሶሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ6 ወር በስደት ከተንላታች በኋላ ወደ አገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው፤

ከግብጽ ሲመለሱ ጌታችን በእመቤታችን ጀረባ ላይ ሆኖ እነዚያ እውራንን ባበሩ ጣቶቹ ወደ ኢትዮጵያ ይጠቁም ያመለክት ነበር፤

እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን የምታመለክተው ብትለው"ያቺ የተባረከች አገር ናት እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ናት፤

ያንቺ ዘመዶች ሰቅለው ይገድሉኛል በዚህች አገር ያሉ ግን ሳይዩኝ ያመኑኛል፤አስራት በኩራትሽ ትሁን ብሎ ሰጥቷታል።

በቃል ኪዳን እግራቸውም ጣና ሐይቅን፣ ዋልድባንና ሌሎችንም ቦታዎች ዞረው እንደባረኩ ድርሳነ ኡራኤልና ተአምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል።

እመቤታችንን ከሐና ማህጸን ፈጥሮ ከፍጥረተ ዓለም ለይቶ ከሁሉ አልቆ የእናት አማላጅ ትሁናችሁ ብሎ የሰጠን እግዚአብሔር ይመስገን።ዳግመኛም በዛሬዋ ቀን በኢትዮጵያ ምድር ታላቅ አምድ ወደቀ ይህም የመናገሻው ባህታዊ አባ ኤልያስ ነው፤

በ400 ዓመት እድሜው ህዳር 6 1874 ዓ/ም አረፈ፤በአጼ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ማለት ነው፤ የቅርብ ጊዜ ነው ፤ ይህ አባት በግራኝ መሐመድ ወረራ ጊዜ የነበረ ነው፤

በዚያን ጊዜ በተለይ ከመናገሻ እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት እየተመላለሰ ሱባኤ እየገባ ፀሎት ያደርግ ነበር፤ በዛሬዋ ቀን ይህ አባት ሲሞት በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ከዋክብት ሲበታተኑ ሲራወጡ ታየ የተጉለቱ አባ በላይነህም ይህንን ምልክት አይቶ የአባ ኤልያስን መሞት ተረዱ ወደ መናገሻ ቢመጡ ሞቶ ተቀብሮ አገኙት፤


T.me/wdasemaryam

https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw
1.4K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 08:43:31 ጥቅምት 27 #መድኃኔ_ዓለም_የስቅለት_በአል

ጥቅምት ሃያ ሰባት በዚህች ዕለት የአምላካችን የመድኃኒታችን #የመድኃኔዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ አመታዊ ክብረ በአል ነዉ እንኳን አደረሰን

መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለኹላችን ድኅነት ሲል ራሱን ወድዶ ፈቅዶ ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅሩን አሳይቶናል። በቅዱስ ወንጌልም እርሱም መድኃኒታችን " ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" ብሎ ነግሮናል። እውነት ነው፣ ራስን ነፍስን ስለጠላት ነፍስ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ድንቅ ነገርና ምን ድንቅ ፍቅር አለ?

ቸሩ አምላካችንን የአስቆሮቱ ይሁዳ ሊያስይዘው የሊቃነ ካህናቱን አገልጋዮች እየመራ አመጣቸው። እነርሱንም ማንን ትፈልጋላችሁ ሲላቸው የናዝሬቱ ኢየሱስን አሉት፣ እኔ ነኝ ቢላቸው የቸሩን አምላክ ድምጽ ሰምቶ አይደለም መቆም በሕይወት መጽናት የሚቻለው የለምና ወደ ኋላቸው ተስፈንጥረው ወደቁ። ደጋግሞም እንዲህ ኾነ። በኋላ ግን እኔ ነኝ ብሎ በፈቃዱ ይሁዳ ስሞ አሳልፎ ሰጣቸው።

ከያዙት በኋላ እያዳፉና እየጎተቱ በሰንሰለት አስረው ወደ ቀያፋና ሐና ግቢ ወሰዱት፣ እስከ ሦስት ሰዓትም አላሳረፉትም ሲያሰቃዩት አድረዋል፣ በራሱም ላይ ሰባ ሦስት ስቊረት ያለው ወደ ሦስት መቶ እሾኾችን የያዘ የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ቢያደርጉበት የራስ ቅሉን ቀዶ ገብቶ እስከ ልቡ ዘልቋል። እንደምን ጭንቅ ነው? እንዲህም አድርገው ደግሞ እያፌዙ ርኲስ ምራቃቸውን ይተፉበትና በዘንግም ደጋግመው ይመቱት ነበር። እየተፈራረቁ ያለ ምንም ርኅራኄ ቸሩን አምላክ ሥጋው እየተቆረጠ እስኪወድቅ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጽኑዕ ግርፋትን ገርፈውታል። የገረፉበትም ጅራፍ በላዩ ላይ ሥጋን እየጎመደ የሚጥል፣ ሕመሙ አንጀት ሰርሥሮ የሚገባ በስለት የተያያዘበት ነበር።

በኋላም አላሳረፉትም እንዲህ አድርገውትም በሊቶስጥራ አደባባይ ያንን ዕርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። እርሱ ግን ይህን ኹሉ ግፍ ሲያደርሱበት አንድም አልተናገረም ነበር። በቀራንዮም በአምስት ጽኑዕ ቅንዋት (ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ እና ሮዳስ) ቸንክረው ዕርቃኑን ሰቀሉት።

በዚህች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተሰበረ መጽናናትንም አልፈለገች ነበር፤ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ እናቱንም እናት ትሆነው ዘንድ በእግረ መስቀሉ አደራን ተቀበለ። ቅዱሳት አንስት በፍጹም ሀዘንና በዋይታ ዋሉ። በስልጣኑም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። ሰባት ድንቅ የኾኑ ተአምራትንም አድርጎ አምላክ መኾኑን ገለጠ። ይህም ጽኑዕ የኾነ ለሰማይ ለምድር የከበደ ነገር ሲከሰት ፀሐይ አምላኬን ዕርቃኑ እንዴት አያለሁ ብላ ጨለመች። ጨረቃ ደም ኾነች፣ ከዋክብቱም ረገፉ፣ ንዑዳን ክቡራን ንጹሐን መላእክትም ትዕግስቱን እያደነቁ በጽኑዕ ሐዘንና መደነቅ ከቅዱስ ዕፀ መስቀሉ ፊት እንደሻሽ ተነጠፉ።

አስራ አንድ ሰዓት በሆነም ጊዜ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር ቅድስት ሥጋውን ከመስቀሉ አውርደው በክብር ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት በሦስተኛውም ቀን እንደተናገረ ተነሳ።

በዛሬዋ ቀን ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔለምን የስቅለት በዓል በደማቁ ታከብራለች፤ ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ስጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ቀን ነው፤ ይህ በዓል ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለና በዓል ማክበር ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሰርታልናለች፡፡

በሞቱ ሞታችንን ወስዶ ህይወቱን ለሰጠን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ ክብርና ምስጋና አምልኮና ዉዳሴ ይሁን አሜን የተዋህዶ ልጆች እንኳን አደረሰን

የተባረከ እለተ #ሰንበት ይሁንልን "አሜን"

T.me/wdasemaryam

https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw


710 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 08:30:44
609 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 05:54:26
ጥቅምት 24 #ፃድቁ_ተክለሃይማኖት

ለፃድቁ አባታችን #ለአቡነ_ተክለሃይማኖት ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

የስማቸው ትርጉም የሃይማኖት መሰረት ፍሬ የሆነው አባታችን ከእናታቸው እግዚሐርያ ከ አባታቸው ፀጋዘአብ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታህሳስ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ

አባታችን የሃይማኖት ተክል ናቸው ጻድቁ አባታችን ገና እንደተወለዱ በሶስተኛው ቀናቸው ከእናታቸው እቅፍ በመውረድ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ እያሉ በመስገድ የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነዋል

እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ መርጧቸዋል ጻድቁ አባታችን ክብረ በዓላቸው እንደሚከተለው ነው

ህዳር 24 ቀን ሃያ አምስተኛ ካህናተ ሰማይ ሆነው በሰማይ የስላሴን መንበር ያጠኑበት እለት ነው

ታህሳስ 24 ቀን የአባታችን ልደት ነው

ጥር 24 ቀን የአባታችን ሰባረ አፅሙ ነው

መጋቢት 24 ቀን የአባታችን ፅንሰታቸው ነው

ግንቦት 12 ቀን የአባታችን ፍልሰተ አፅሙ ነው

ነሐሴ 24 ቀን የአባታችን እረፍታቸው ነው

የፃድቁ አባታችን #የቅዱስ_ተክለሃይማኖት ቡራኬ ይድረሰን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚዉሉ ቅዱሣን የከበረዉ ቃል ኪዳናቸዉ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን "አሜን"



T.me/wdasemaryam

https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw


134 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 02:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 07:26:09
#አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ተመለሺ ተመለሺ እናይሽ ዘንድ ተመለሺ''(መኃ 5:12)
905 viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 04:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-27 07:21:50 እንኳን_አደረሳቹሁ ሰማእቱ እስጢፋኖስ

, ጥቅምት 17 በዚህ ቀን የዲያቆናት አለቃ የሰማዕታት መጀመሪያ ቅዱስ እስጢፋኖስ ለተሾመበት ቀን መታሰቢያ ነው።
እስጢፋኖስ የግሪክ ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም «አክሊል» ማለት ነው።

ቅዱስ እስጢፋኖስ በግሪክ ሀገር እንደተወለደ የሚነገርለትና ከክርስቶስ እርገት በኋላም አስራ ሁለቱም ሐዋርያት በጋራ ተሰብስበውና ለአገለግሎት ከመረጡዋቸው ሰባት ዲያቆናት አንዱና ዋነኛው ነበር። ሕዝቡን በማዕድ ያገለግሉ ዘንድ ሰባት ዲያቆናት ተመርጠዋል።

ከእነዚህ መካከል ቅዱስ እስጢፋኖስ አንዱ ሲሆን ለስድስቱ ዲያቆናት ደግሞ አለቃ ሊቀ ዲያቆን ሆኖ ተሹሟል። ቅዱስ እስጢፋኖስ በማዕድ አገልግሎት ሕዝቡን ከማገልገሉ በተጨማሪ ወንጌልን ይሰብክ ነበር ። ተዐምራትን የማድረግ ጸጋም ተሰጥቶት ነበር በዚህም አገልግሎቱ ብዙዎችን ወደ ክርስትና መልሷል።

በዚህም አይሁድ በቅናት ተነሳስተው በሐሰት ከሰሱት ከከተማውም ወደ ውጭ አውጥተው ቄዳር በተባለ ቦታ በድንጋይ ወገሩት በሚወግሩትም ጊዜ ሰማያት ተከፍተው ምሥጢረ ሥላሴን እግዚአብሔርን በሦስትነቱ ተመለከተ።
ኢየሱስ ክርስቶስንም በአብ ቀኝ ተቀምጦ አየ ። ለሚወግሩትም ሰዎች ከአምላኩ እንዲህ በማለት ምሕረትን ለመነ «ጌታ ሆይ ይህንን ኃጢአት አትቁጠርባቸው» በመጨረሻም «ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል»ብሎ ነፍሱን ሰጠ።
ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት። ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ። እስጢፋኖስም። ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር። ተንበርክኮም። ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት

አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር። 《የሐ ሥራ 7፥58—60》

የቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት በረከትና ምልጃው አይለየን ለዘለዓለሙ አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን ይቆየን



T.me/wdasemaryam

https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw
1.9K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-27 07:21:17
1.4K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 20:28:56
እንኳን አደረሳችሁ ጥቅምት 5
ፃዲቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ
#አቡነ_ገብረመንፈስቅዱስ ሀገራቸው ንሂሳ (ግብጽ ) ነው አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌያስ ይባላሉ ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል
➬አንድ ቀን አቅለያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ሥላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን "" ንስኢ ወልደ ዘይትሌአል ቅርኑ አምኑኅ ሰማይ ... ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ "" የሚል ድምጽ ሰማች :: በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ ::

አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው "" ስብሐት ለአብ , ስብሐት ለወልድ , ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን >> ብለው በማመስገናቸውና ሀላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ : ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መልአክትን ይመስላሉ

ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው :: አበመኔቱም አባ ዘመድብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ ፍሱሐ ገጽ ሆነ አግኝተዋቸዋል :: አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአረገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል ::

ከዚህ ቡሐላ ሐብተ ፈውስ ተሰጥቷቸውል :: በአንድ ቀን እልፍ እውራንን እና እልፍ አንካሳ ፈውሰዋል :: በዋላ ግን ኤጲስ ቆጶሳትና ካህናቱ ዝናቸውን ሰምተው እየመጡ ግብር የሚያስፈቱአቸው ቢሆን ቅዱስ ገብርኤል ነጥቆ ከጌታ ፊት አቀረባቸው ::

በገድለህ : በትሩፋትህ : ከሞት ነፍስ ክርደት ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ :: ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው :: ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? "ዘኬድከ ጸበለ - እግረከ ይልህሱ ወበ ውእቱ ይጽግቡ ... የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ :: ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው : ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ :: ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ : አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር :

በዚህ መልኩ 30 አመት ከቆዩ ቡሐላ ጌታ በአንድነት በሶስትነት ተገልጾ ምን ላደርግልህ ትሻለህ ? አላቸው :: መጀመሪያ ላሉበት መጸለይ ይገባልና የምድር ገቦታን ሰዎች ማርልኝ አሉት :: 3000 ሐጥአንን ከሲኦል አውጥቶ ገነት አግብቶላቸዋል :: ከዚህ ቡሐላ ሁር ምድረ ኢትዮጵያ ወበህኒ አልውከ ነፍሳት ወታወጽኦሙ .... ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው :: ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ ምድረ ከብድ አድርሷቸዋል :: ዳግመኛም ወደ ዝቁዋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጽልዩ ነበር :: 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ ዘገብረ ተዝካርከ ወዘጽውአ ስምከ እምህር ለከ ብሎሀል አላቸው :: እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ ከባህሩ አልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል :: ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ ተንስእ ወጽእ መሀርኩ ለከ ኩሎ ኢትዮጵያ ... ምሬልሀለው ውጣ ብሏቸው ወጥተዋል ::

ከዚህ ቡሐላ ምድረ ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7አመት እንደ ትኩል አምድ ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ሳይከድኑ ቆመው ጸልየዋል :: ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው :: 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አድነዋቸዋል :: ከዚያ ተነስተው ወደ ዝቁዋላ ሲሄዱ ሥላሴን በአምሳሌ አረጋውያን ከጥላው ስር አርፈው አገኙዋቸው :: በእግዚአብሔር ዙፋን ተማጽነንሀል አዝለክ አንድ አንድ ምህራፍ ሸኘን አሉዋቸው :: አዝለው ከሸኙዋቸው ቡሐላ በአንድነት በሶስትነት ሆኖ ታያቸው :: ድንግጠው ወደቁ : እግዚአብሔር ግን አንስቷቸው ሂድ ዝቁዋላ ሄደህ ጠላቶችህን ተበቀላቸው አላቸው :: በዛበነ መብረቅ ደርሰው 7 ቱን ሊቃነ መላእክት አጋዥ አድርገው እልፍ አእላፍ አጋንንትን አጭደዋል ::

ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር የመጋቢት 27 ስቅለት ደግሞ ጥቅምት 27 ቀን እንዲከበር ተደረገ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ስርዓት ሆነ፤

አሜን አሜን አሜን
#ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር

T.me/wdasemaryam

https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw


2.5K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 13:35:44 ጥቅምት 4 #ወንጌላዊዉ_ዮሐንስ

ቅዱስ #ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ_ፍቊረ_እግዚእ ለወርሐዊ በአሉ እንኳን አደረሰን

የከበረና የተመሰገነ ዮሐንስ በዚህ ዓለም ዘጠና ዓመት ኖረ እጅግም ሸመገለ ግን እንደ ባልንጀሮቹ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አልቀመሰም

ስለ ድንግልናውና ስለ ንጽሕናው ይህ ሆነ ሁሉም በክብር ይስተካከሉ ዘንድ እርሱም ወንጌልን ቀለምሲስ የሚባለውን ራእይ ሦስት መልእክታትን የጻፈ ነው

ራት ሲበሉ በጌታ ኢየሱስ አጠገብ የተቀመጠውና አቤቱ የሚያሲዝህ ማነው ያለው ይህ እርሱ ነው

ጌታችንም በተሰቀለ ጊዜ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር በመስቀሉ አጠገብ የቆመ እናቱንም እነሆ ልጅሽ ያላት እርሱን ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው

ጴጥሮስም እርሱን ሲከተለው በአየው ጊዜ ስለርሱ ጌታ ኢየሱስን አቤቱ ይህስ እንዴት ነው ብሎ የተናገረ ጌታ ኢየሱስም እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ከወደዱኩ አንተ ምን አለህ አንተ ግን ተከተለኝ ያለለት ይህ ነው

የፍቁረ እግዚእ #ቅዱስ_ዮሐንስ ረድኤት በረከት ምልጃ ፀሎት ሁላችንንም ይጠብቀን "አሜን"

በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የምናስባቸው ቅዱሳን ቃል ኪዳናቸው ይጠብቀን "አሜን"



T.me/wdasemaryam

https://youtube.com/channel/UCzj1rOCD7-WVTFN7VU8RmZw

2.0K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 08:12:06
1.8K viewsDesalegn Dagne ✥ድንግል ሆይ ሁሉን ከሚያስብ ሁሉን ከማይዘነጋ ከልጅሽ አሳስቢ✥, 05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ